Get Mystery Box with random crypto!

የምናባዊው የ'ስኳድ' ሰነድ ደራሲዎች... እዳ እኮ ነው ጎበዝ። ደግሞ በሽታቸው አገርሽቷል። ተ | Amde Ezra

የምናባዊው የ"ስኳድ" ሰነድ ደራሲዎች...


እዳ እኮ ነው ጎበዝ። ደግሞ በሽታቸው አገርሽቷል። ተነስቶባቸዋል። አየር ላይ ወይም ምንብ ላይ የፈጠሩትን "በበሬ ወለደ" ትርክት መሬት ላይ ለማወረድ እየተጋጋጡ ነው። ጥቁሩን በረጅም ምላሳቸው ፍቀው ነጭ ለማድረግ እየተጉ ነው።

የምናባዊው የ"ስኳድ" ሰነድ ደራሲዎች የፖለቲካ ኃይል አሰላለፉ መልኩን በቀየረበት በዚህ ወቅት የሰነዱን አቧራ አራግፈው ከተፍ ብለዋል። የተቀናጄ ዘመቻ ጀምረዋል።

እንዳልኩት የፖለቲካዊ ኃይል አሰላለፉ በተቀያየረበት ወቅት ምናባዊ ድርሰታቸውን ለምን ሰሞኑን እንደ አዲስ ይዘውት ከች አሉ? ለምን እንደ አዲስ እንድን አካባቢ ታርጌት አድርገው የተቀናጀ ዘመቻ ጀመሩ? የአሁኑ ዘመቻ ዓላማውና ግቡ ምንድን ነው?

ወዳጄ "ጠርጥር ከገንፎ አይጠፋም ስንጥር" እንዲል የሰነዱ ደራሲዎች ያውም በዚህ ወቅት የጀመሩትን የተቀናጀ ዘመቻ፣ በቅጥፈት ዘመቻው ታርጌት የተደረክ የአንድ የአካባቢ ተወላጅ ሁሉ መርምር። ከተሳለብህ ሰይፍ የምትተርፍበትን ብልሃት ቀምር።

መልዕክቴ ይሄው ነው።