Get Mystery Box with random crypto!

ፋሲል ከነማ ከሜዳ ምደባ ጋር ተያይዞ ቅሬታዉን አቅርቧል !! የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ | Alpha Sport

ፋሲል ከነማ ከሜዳ ምደባ ጋር ተያይዞ ቅሬታዉን አቅርቧል !!

የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ2014 የዉድድር ዘመን ሊገባደድ የቀናት እድሜ ብቻ እንደቀሩት ይታወሳል። ከዚህ ጋር ተያይዞ የ30ኛ ሳምንት ጨዋታዎችን በተለይ የዋንጫ ባለቤቱን እና ቀሪ ወራጅ የሆነዉ ቡድን ለመለየት ሳኝነት ያላቸውን ጨዋታዎች በተመሳሳይ ሰዓት በሶስት ስታዲየሞች ለማካሄድ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማህበር ፕሮግራም ማዉጣቱ ይታወሳል። በዚህም ክለቦች ጨዋታዎቻቸውን እንዲያካሂዱ የተመደበላቸው ስታዲየም አግባብነት የጎደለዉ ስለመሆኑ እና አክሲዮን ማህበሩ በዚህ ጉዳይ ማብራሪያ እንዲሰጥ ሲሉ ጠይቀዋል። ሙሉ ደብዳቤው ከታች በምስሉ ተያይዟል።