Get Mystery Box with random crypto!

ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 28ኛ ሳምንትን የዲሲፕሊን ውሳኔዎች። ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕ | Alpha Sport

ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 28ኛ ሳምንትን የዲሲፕሊን ውሳኔዎች።

ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2014 በ28ኛ ሳምንት በየተደረጉ 8 ጨዋታዎች ላይ 17 ጎሎች በ14 ተጫዋቾች ሲቆጠሩ 39 ቢጫ ካርድ በተጫዋቾች ላይ ተመዘዋል ፥ በሳምንቱ የተመዘገበ ቀይ ካርድ የለም።

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ቅዳሜ ሰኔ 18 2014 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የተደረጉ ፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያ(ዎች)ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ የተለያዩ የዲሲፕሊን ውሳኔዎችን አስተላልፏል።

ፍሪምፖንግ ሜንሱ(ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ ሪችሞንድ ኦዶንጐ(አዲስ አበባ ከተማ)፣ ፍሬው ጌታሁን(ድሬደዋ ከተማ) ፣ ክሌመንት ቦዬ(መከላከያ) በተለያዩ 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ የተመለከቱ ሲሆን ተጫዋቾቹም ለፈፀሙት ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገዱና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 /አንድ ሺ አምስት መቶ/ ሲወሰን አሰልጣኝ ሳምሶን አየለ(ድሬዳዋ ከተማ) ክለቡ ከባህር ዳር ከተማ ጋር ባደረገው ጨዋታ ግጥሚያው ከተጠናቀቀ በኃላ የድህረ ጨዋታ ቃለመጠይቅ አለመስጠታቸው ሪፓርት የተደረገባቸው ለፈፀሙት ጥፋት በፕሪምየር ሊግ የውድድር ደንብ መሰረት ብር 3000 /ሶስት ሺህ/ እንዲከፍሉ ወስኗል::

@Alphasportet