ኢብኑል ቀይም "አላህ ይዘንለትና" እንዲህ ብሏል። ዱአ (ይበልጥ) ተቀባይነት የሚያገኙባቸው ጊዜያቶች ስድስት ናቸው። ①) የሌሊት የመጨረሻው አንድ ሶስተኛ ላይ ②) በአዛን ጊዜ (አዛኑ እንዳለቀ) ③) በአዛንና በኢቃማ መካከል ④) ከፈርድ ሶላት በኋላ (የመጨረሻው አተህያቱ ብለን ከማሰላመታችን በፊት) ⑤) የጅሙአ ቀን ኢማሙ ለኹጥባ ሚምበር በሚወጣበት ጊዜና ⑥) የጁሙአ ቀን የመጨረሻው ሰአት ላይ ናቸው الداء و الدواء (١٢). 33 views12:31