Get Mystery Box with random crypto!

MFN TEACHING 🌍 FOUNDATION CLASS. SINCE 2012.

የቴሌግራም ቻናል አርማ almgenamfn — MFN TEACHING 🌍 FOUNDATION CLASS. SINCE 2012. M
የቴሌግራም ቻናል አርማ almgenamfn — MFN TEACHING 🌍 FOUNDATION CLASS. SINCE 2012.
የሰርጥ አድራሻ: @almgenamfn
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 148
የሰርጥ መግለጫ

አገልግሎታችን እንደ አዲስ ሳይሆን እንደ ቀደሙት አባቶቻችን ትውልዳችንን አገልግለን ማለፍ ነው።

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-02 14:52:29
44 viewsDaniel Getahun Alemu (0919), 11:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 09:21:09 https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid02iaYpTS6VDq2REzTLK8yAcMRSt8v9Hpx6xuxVJoFE3VU9PduGTA3C6b2RZn8yPtZ5l&id=100075986020900&sfnsn=mo
444 viewsDaniel Getahun Alemu (0919), 06:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-28 11:55:08
''የመጨረሻው ዘመን'' ማንቂያ ደውል
በምንወደው ወንድም ጋዜጠኛ መሳይ አለማዮ ይደወላል።
ግንቦት 20/2014 ዓም. ድሬደዋ ተልዕኮ ለትውልድ ቤተክርስቲያን።
125 viewsDaniel Getahun Alemu (0919), 08:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-05 09:54:11 Watch "VISION #26 የኪዳን አይነቶች #3 እና የጨው ኪዳን ታሪክ #1" on YouTube


1.2K viewsDaniel Getahun Alemu (0919), 06:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-05 09:53:49 Watch "VISION #25 የኪዳን አይነቶች እና ትርጓሜዎች // ክፍል-2" on YouTube


1.3K viewsDaniel Getahun Alemu (0919), 06:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-05 09:53:33 Watch "Vision #24 ራዕይና ኪዳን ክፍል-አንድ '' ዘላለማዊ እና የሁለትዮሽ''" on YouTube


1.4K viewsDaniel Getahun Alemu (0919), 06:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-05 09:52:26 Watch "VISION #23 7 spirit // The Meanings of Seven spirit /last" on YouTube


273 viewsDaniel Getahun Alemu (0919), 06:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-05 09:51:51 Watch "Vision #22 የመልአኩ እና የ7ቱ መንፈስ አንድነት በመጨረሻው ዘመን እንቅስቃሴ ውስጥ." on YouTube


1.7K viewsDaniel Getahun Alemu (0919), 06:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-05 09:51:06 Watch "VISION #21 እንዴት ኢትዮጲያ ትታጠቃለች? how ethiopian eqiuped" on YouTube


1.0K viewsDaniel Getahun Alemu (0919), 06:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-16 15:20:12 4ቱ የትዳር አላማዎች ?

በመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ ካሉ ሰዎች መካከል በትዳር ህይወታቸው እና በቤተሰቦቻቸው መልካም የህይወት ምስክርነት ያላቸው አሉ። ለምሳሌ ቆርኔሊዎስን ብንመለከት ይህ ሰው ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን አልተቀበለውም ዳግመኛም አልተወለደም ነገር ግን አንድ ቀን ጌታ ተገልጦለት እንዲህ ሲለው እንመለከታለን "፤ እርሱም ትኵር ብሎ ሲመለከተው ደንግጦ። ጌታ ሆይ፥ ምንድር ነው? አለ። መልአኩም አለው። ጸሎትህና ምጽዋትህ በእግዚአብሔር ፊት ለመታሰቢያ እንዲሆን አረገ። " (የሐዋርያት ሥራ 10: 4)

ለቆርኔሊዎስ ፀሎት መልስ ምክንያት ከቤተሰቡ ጋር የነበረው መንፈሳዊ ትስስር ነበር ብቻውን የሚፀልይ ብቻውን የሚተጋ አልነበረም። የሚገርመውም ነገር በእርሱ ምክንያት ሙሉ ቤተሰቡ ብቻም ሳይሆን ለአእዛብም ጭምር መፈወስ ምክንያት መሆኑ ነዉ።
ቤተሰባዊ የሆነ የክርስትና የህብረት ህይወት ድንበር ተሻጋሪ ከመሆኑም ባለፈ ዘመን ተሻጋሪነትንም የተሞላ የትውልድ መልህቅ ነዉ።
በሰማይ 100 ግላዊ ከሆኑ መንፈሳዊ ሰዎች ይልቅ 10 የህብረት ልብ ያላቸው መንፈሳዊ ሰዎች ሰማያዊ የሆነውን ፍቃድ መፈጸም ይችላሉ ለዚህም የሐዋርያት ህይወት ድንቅ ምሳሌ ነዉ።
በቤተሰብ ዉስጥ የትዳር አላማ አለመታወቁ በባህር ላይ ለመጓዝ የመኪና መናሀሪያ ስፍራ ሄዶ ትኬት እንደ መቁረጥ ይቆጠራል ስለዚህ መናሀሪያ ከመሄዳችን በፊት የት እና በምን መሄድ እንዳለብን ለማሰብ መጀመሪያ  እነዚህን የትዳርን #አላማዎች እንመልከት ።

1, ትዳር አንዳችን የአንዳችንን ክፍተት ፣ ጉድለት መሙላት ነዉ።

    አሁን ላይ ብዙ ሰዎች የሚጋቡት ለጥቅም ወይም በዉጨኛዉ ህይወት ላይ ያተኮረ ጊዜአዊ ግንኙነት ላይ ነዉ። ከዚያም ከተጋቡ ቡሀላ ያ በነገሮች የተሸፈነው ማንነት እየተገለጠ ሲመጣ ዉስጣቸዉን ማሸነፍ ያቅታቸዋል ያኔ ስልቹነት ፣ ብስጭት እና ጭቅጭቅ ይፈጠራል። ሞትኩልሽ ሲል የነበረዉ ምነው በሞትሽ በሚለው ቃል ይሻርና የትዳራቸዉ መርከብ መሪ ይበጥሳል ። መጨረሻቸውም መስመጥ ይሆናል ።
የትዳርን ጅማሬ ከዉስጥ መጀመር ለዘላቂ የደስታና የሠላም ህይወት ምንጭ ነዉ።
ክፍተት የሚሞላው በመመካከር ፣ በመታገስ እና በመቻቻል ሲሆን መፅሐፍም እንዲህ በማለት ይደግፈናል ።"፤ እንዲሁም፥ እናንተ ሚስቶች ሆይ፥ ከባሎቻችሁ አንዳንዱ ለትምህርት የማይታዘዙ ቢኖሩ፥ በፍርሃት ያለውን ንጹሑን ኑሮአችሁን እየተመለከቱ ያለ ትምህርት በሚስቶቻቸው ኑሮ እንዲገኙ ተገዙላቸው። "1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 3: 1-2
ባል ያለውን ጉድለት ሚስቱ ስትሞላለት ሚስትም ያላትን ጉድለት ባል ሲሞላላት ያኔ ፍፁም ህይወትን ወደ መግለጥ ይመጣሉ ።
ጴጥሮስ ስለ ሴቶች ሲናገር በትዳር ላይ የራሳቸው ድክመት እንዳለባቸው ተናግሯል ድክመታቸው ግን ወደ ጥንካሬነት የሚቀየረው በባሎቻቸው የማስተዋል ህይወት ነዉ ።
(1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 3 ) 7፤ እንዲሁም፥ እናንተ ባሎች ሆይ፥ ደካማ ፍጥረት ስለ ሆኑ ከሚስቶቻችሁ ጋር በማስተዋል አብራችሁ ኑሩ፤ ጸሎታችሁ እንዳይከለከል አብረው ደግሞ የሕይወትን ጸጋ እንደሚወርሱ አድርጋችሁ አክብሩአቸው።

   2, ፍቅር

"፤ ወደ ወይን ጠጁም ቤት አገባኝ፥ በእኔ ላይ ያለው ዓላማውም #ፍቅር ነው። "መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን 2: 4) ወንዶችም ሴቶችም ወደ ትዳር ስንገባ አላማችን ምንድን ነዉ? አላማችን ፍቅር ካልሆነ ተስፋ ያደረግነው ያ ነገር ሲጠፋ አብረን እንጠፋለን ።
መፅሐፍ ደግሞ ስለ ፍቅር እንዲህ ብሎ ያስተምረናል (1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 13 )4፤ ፍቅር ይታገሣል፥ ቸርነትንም ያደርጋል፤ ፍቅር አይቀናም፤ ፍቅር አይመካም፥ አይታበይም፤
5፤ የማይገባውን አያደርግም፥ የራሱንም አይፈልግም፥ አይበሳጭም፥ በደልን አይቆጥርም፤
6፤ ከእውነት ጋር ደስ ይለዋል እንጂ ስለ ዓመፃ ደስ አይለውም፤
7፤ ሁሉን ይታገሣል፥ ሁሉን ያምናል፥ ሁሉን ተስፋ ያደርጋል፥ በሁሉ ይጸናል።
በትዳር ዉስጥ አላማ ያስፈልጋል አላማዉም ፍቅር ነዉ።

3, ትዳር የተሾመ ሰው የሚገባበት ነዉ።

      በሰማይ ትዳር ሹመት እንጂ በሰዉ ፍላጎት የሚመጣ ነገር አይደለም ።ሹመት ደግሞ ስልጣን ነዉ። ምክንያቱም በሰማይ ትዳር ኪዳን ነዉ ።
     ሰዎች የሚጋቡት እግዚአብሔር ሾሟቸዉ እንጂ በራሳቸው ወይም በሰዉ ፍቃድ አይደለም ። "፤ ክርስቶስ ደግሞ የቤተ ክርስቲያን ራስ እንደ ሆነ እርሱም አካሉን የሚያድን እንደ ሆነ ባል የሚስት ራስ ነውና። " ወደ ኤፌሶን ሰዎች 5: 23
     የሰዉ ትዳር በክርስቶስ እና በቤተ ክርስቲያን ይመሰላል ለዚህም ነዉ መፅሐፍ የትዳራችንን ትርጉም እንደ እርሱ እንድናደርግ የሚነግረን ።
     ባል ለሚስቱ ሹመት መገዛት ሲኖርበት ሚስት ደግሞ ለባሏ ሹመት መገዛት አለባት ። መገዛት መዉረድ ነዉ እግር መተጣጠብ ነዉ። ይህንን ከጌታ ኢየሱስ እና ከደቀመዛሙርቱ ተምረናል ።

4,   ልጆች

  ልጆች የእግዚአብሔር ስጦታዎች ናቸው ። የስጦታን እቃ እንደፈለግን አናደርገውም እንጠነቀቅለታለን ። ከዚህ በላይ ልጆች ይህ ያስፈልጋቸዋል ምክንያቱም የሰው ስጦታ አይደሉም  የእግዚአብሔር እንጂ ።
ልጆች የእግዚአብሔር ንብረት ወይም ዕቃ ናቸው ። ባለቤትነታቸው በእግዚአብሔር እንጂ በእኛ አይደሉም ማንኛውም ዕቃ ደግሞ ሲገዛ የዕቃዉ አጠቃቀም manual ይሰጣል ። ልክ እንደ ዕቃዉ ልጆችን እንዴት ማሳደግ ወይም መጠቀም እንዳለብን እግዚአብሔር manual ሰጥቶናል ።
ልጆችን ለስጋቸዉ የተመጣጠነ ምግብ እንደምናቀርብላቸዉ ሁሉ የተመጣጠነም የእግዚአብሔር ቃል ለነፍሳቸው ያስፈልጋል ። ይህ ሲሆን አይቀጭጩም፣አይጠወልጉም ንቁ ሆነዉ በመልካም ያድጋሉ ።

"፤ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና። " (የዮሐንስ ወንጌል 3: 16) እግዚአብሔር ጋር የልጅ ዋጋ ትልቅ ነዉ። ለዚህም ነዉ የሚወደዉን ልጁን ጨክኖ እኛን ለማዳን የላከዉ።

ባጠቃላይ እነዚህን 4 የትዳር #አላማዎችን ማወቅ ለጠንካራ እና ለጤናማ የትዳር ህይወት የማይናወጡ አምዶች ናቸው እርሶም እነዚህን በመተግበር ትዳርዎን ይታደጉ።
1.8K viewsDaniel Getahun Alemu (0912), 12:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ