Get Mystery Box with random crypto!

ሼክ ኸሊፋ ቢን ዛይድ አል ናህያን ማን ነበሩ ? አቡዳቢን ለረጅም ዓመታት በመምራት የሚታወቁት ሼ | بيت النحو

ሼክ ኸሊፋ ቢን ዛይድ አል ናህያን ማን ነበሩ ?

አቡዳቢን ለረጅም ዓመታት በመምራት የሚታወቁት ሼክ ኸሊፋ ቢን ዛይድ አል ናህያን የተወለዱት እ.አ.አ በ 1948 መሆኑን የህይወት ታሪካቸው ያስረዳል።

በአል ዐይን ከተማ በሚገኘው አል ሙዋጅ ቤተ መንግስት የተወለዱት ሼክ ኸሊፋ ቢን ዛይድ አል ናህያን የሼክ ዛይድ የመጀመሪያ ልጅ ናቸው።

ሼክ ኸሊፋ ቢን ዛይድ አል ናህያን ትምህርታቸውን የተከታተሉት በአባታቸው ሼክ ዛይድ በተመሰረተውና በትውልድ ከተማቸው በሚገኘው አል ናህያን ትምህርት ቤት ነው።

ሼክ ኸሊፋ ቢን ዛይድ አል ናህያን በአውሮፓውያኑ ጥቅምት 1966 በምስራቅ የሀገሪቱ ግዛት፤ የአቡዳቢ ገዥ ተወካይና የሕግ ስርዓት ሃላፊ በመሆን መሾማቸው ይታወሳል።

ሼክ ኸሊፋ ቢን ዛይድ አል ናህያን በ1969 የአቡዳቢ አልጋወራሽ መሆናቸው የሚታወስ ሲሆን፤ በ 1974 ደግሞ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን አገልግለዋል።

al-ain

ወደ ወራቤ ታይምስ ቻናል ይቀላቀሉ

t.me/WorabeTimes

«ሚዲያን መቆጣጠር ሀገርን መቆጣጠር ነው»