Get Mystery Box with random crypto!

ኡስታዝ አቡበከር አህመድ ፦ ' . . . ልክ ወደ መጨረሻው ፕሮግራም ላይ ልንገባ ስንል ነው ድን | بيت النحو

ኡስታዝ አቡበከር አህመድ ፦

" . . . ልክ ወደ መጨረሻው ፕሮግራም ላይ ልንገባ ስንል ነው ድንገት ድምፅ ሰማን፤ እየተረበሸ እንደሆነ ተነገረን።

ምንድነው ? ብዬ የሚመለከተው የመንግስት የስራ ኃላፊ ከፀጥታ መዋቅር ውስጥ አንዱ አመራር ጋር ደውዬ ስጠይቅ ያለው ነገር ' ሀያት ሬጀንሲ አካባቢ ጭስ ነው ' ይረጋጉ አሉኝ።

ሰው ይረጋጋ ብዬ ለመድረክ አስተባባሪው ነገርኳቸው ፤ ሰውን አረጋጋነው ፤ መልሶ ግን ቀጠለ ረብሻው ፣ ድምፁም የሚረብሽ ስለነበር ትንሽ ጥሩ አልነበረምና ምንድነው በሚል ጉዳዮችን ለመከታተል ሞከርን።

መልሼ ስጠይቅ ፤ ' አይ አስለቃሽ ጋዝ ከአንድ ፖሊስ በአጋጣሚ አምልጦት ፤ ድንገት ባርቆበት ' ተባለ ፤ ይህንን የሰማሁት ከፀጥታ መዋቅሩ ነው።

...በጣም ደስ የሚል እና ያማረ ፣ በጣም በጥሩ ሁኔታ ያሳለፍንበት ኢድ ነበር ነገር ግን ይሄ ክስተት መጥቶ ትንሽ ነገሮችን ረባበሻቸው።

በትክክል ለማጣራት ሞክሪያለሁ አንድ የፀጥታ ኃላፊ ከሚመለከታቸው ኮሚሽነር ጋር ተነጋግሬ የነገሩኝ ' ፌዴራል ፖሊሱ ባርቆበት ነው ' አሉ።

ከዛም ደግሞ በትክክል አካባቢው ላይ የመደብናቸው የእኛ አስተናጋጆች በአጋጣሚ ሴቶች ያሉበትና የሚሰግዱበት ቦታ ነበር።

የ 'ሰማዕታት ሀውልት' አካባቢ ላይ ነው፤ ሚኒስትሮች ሳይቀሩ የመንግስት ሙስሊም ሴት ሚኒስትሮች ቦታው ላይ የነበሩ አግኝቻቸው ያዩትን ክፍተት ነግረውኛል።

ከአንድ የ 'ፌዴራል ፖሊስ' ነው ተወርውሯል የሚሉት ምክንያቱም ፤ የሚባርቅ ነገር ዝም ብሎ የሚወድቅ አይደለም ፤ ተፈቶ መለቀቅ አለበት አስለቃሽ ጭሱ ፤ ተፈቶ ነው የተለቀቀው ወደ ሰው ነው የተጣለው።

ሴቶችና ህፃናቶች ወዳሉበት ቦታ ነው የተወረወረው።

ሰው በዛ ሰዓት ወደ መራባበሽ ስሜት ውስጥ ገባ ፤ ሴቶችም በድንጋጤ መሮጥ፤ መነሳት ያፍናል አይነት ሁኔታ ተፈጠረ።

በዚህ ሂደት ላይ እያሉ ሰውን አትውጣ ወደዛ አትሂድ የሚለው ግፊት መጣ ፤ በዚህ መካከል ሰውየውንም ይዘውት ነበር ፤ የእኛ አስተባባሪዎች ከያዙት በኃላ ሌሎች ፌዴራል ፖሊሶች ልቀቁት ብለው ያስለቀቁት፤ እሱም ይቅርታ ጠይቋል ' እኔ ባርቆብኝ ነው፤ ሳላስብ ነው ' ብሎ ደንግጦ የተናገረበት ሂደት ነበር የነበረው።

ያ ሁኔታ ተከሰተ ሰው ስሜት ውስጥ ገባ ፤ እንደገና መገፋት ፣ ወደዛ አትሄድም ወደዚህ አትመጣም ፣ ሶላት አልሰገደም በዚህ አይነት ነገር ውስጥ ሲገባ ተኩስ ተጀመረ ወደ አየር ፤ አስለቃሽ ጭሶች መሰል ነገራቶች እየተደረጉ ሲሄዱ አቅጣጫ ስተው ረብሻዎች ደስ የማይል ነገር ተከስቷል።

እስካሁን ባለኝ መረጃ የሞተ ሰው የለም። የተጎዱ ሰዎች አሉ።

የተለያዩ ሆስፒታሎች ውስጥ የገቡ አይናቸው አካባቢ ተመተው...በተለያየ ነገር የተመቱ ሰዎች ሆስፒታል የገቡ አሉ። ይሄ ነው ክስተቱ።

መጣራት አለበት ለምን ?፤ ማን ?፤ እንዴት ? የሚሉት ነገሮች መታየት አለባቸው። ይሄ በጣም ትልቅ የሆነ ታሪካዊ የሆነ፣ እንደ አትዮጵያ ያለ ሙስሊም የውጭ እንግዳ ጠርተን ፣ በልዩ ሁኔታ ያከበርነው ኢድ ስለነበር እነዚህ ነገሮች ከባድ ናቸው። "

: Tikvah

@WorabeTimes