Get Mystery Box with random crypto!

የታላቁ አዛኝ የአለም ነብይ ጣፋጭ ታሪክ የፉጅጃር ጦርነትና የፈዱል ስምምነት | Alif media

የታላቁ አዛኝ የአለም ነብይ ጣፋጭ ታሪክ



የፉጅጃር ጦርነትና የፈዱል ስምምነት

[ክፍል3]

ነብዩ ﷺ እድሜያቸው 14 ሲሞላ "ሐርበል ፉጅጃር" በተባለው ጦርነት ላይ ተሳተፉ።

የኪናናህና የቁረይሽ ጎሳ በአንድ ወገን፣የቀይስ ጎሳ በሌላ ወገን ተሰልፈው ያደረጉት ጦርነት ነው።ለአረቦችም እጅግ አስፈሪ ጦርነት ነበር።

የተቀደሰችውን የመካን ከተማ ክብር የገረሰሰ ስለነበር እለቱ"የውመል ፉጅጃር"(የአመፅ ቀን) ተባለ።

የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ ሲሉ ተናግረዋል፡-በዚህ ጦርነት ላይ ለአጎቶቼ ቀስት እየሰበሰብኩ አቀብል ነበር።"ያኔ የ 14 ወይም የ15 አመት ልጅ እንደነበሩ ከፊል ዘገባዎች ያመላክታሉ።

ሌሎች ደግሞ የ20 አመት ልጅ መሆናቸውን ዘግበዋል።የመጀመሪያው ሀሳብ ሚዛን ይደፋል። ምክንያቱም በጦርነቱ ወቅት የነበራቸው ሚና ቀስት እየሰበሰቡ ማቀበል መሆኑ ልጅ እግር እንደነበሩ ያመለክታል። ይህ ተሳትፎ ከልጅነታቸው ጀምሮ ጀግንነትን እንዲማሩና የውጊያ ልምድ እንዲቀስሙ አደረጋቸው። ይህ ጦርነት እንደሌሎች የአረብ ጦርነቶች ሁሉ በኢምንት ምክንያት የተነሳ ነው።ከዚያም የዘረኝነት እሳት አቀጣጠለው።የኢስላም ብርሀን ልቦናዎቻቸውን አስማምቶ ይህን ጥመት እስኪያስወግድላቸው ድረስ እንደዚሁ ነበሩ።

ቁረይሾች ከፉጅጃር ጦርነት እንደተመለሱ "ፈዱል" የተባለውን ስምምነት ለማድረግ ተጠራሩ። ስምምነቱ ከቁረይሽ ባለቤቶች መካከል አንዱ በነበረው በጀድአን ቢን ተይሚ ቤት ውስጥ ተፈፀመ።የስምምነቱ ይዘት መካ ውስጥ ተበድሎ ያገኙትን ማንኛውም ሰው የከተማዋ ነዋሪ ይሁንም አይሁን ከጎኑ ቆመው በደሉን ለማካካስ የተስማሙበት ነበር።የአላህ መልዕክተኛ ﷺ ከአጎቶቻቸው ጋር በመሆን በስምምነቱ ላይ ተስማምተዋል።

አላህ በመልዕክተኝነት ከላካቸው በኋላ እንዲህ ሲሉ ተደምጠዋል፡-

لقد شهدت مع عمومتي حلفا في دار عبدالله بن جدعان ما أحب ان لي به حمر النعم ولو دعيت به في الإسلام لأجبت

《"በአብደላህ ኢብን ጀድአን ቤት ውስጥ
በተደረገው ስምምነት ላይ ተገኝቻለው።ከዚያ ሳልገኝ ቀርቼ በልዋጩ ቀይ ግመል ቢሰጠኝ የምመርጥ አይደለሁ።በእስልምና ውስጥ ሆኜም ወደዚያ ስምምነት ብጋበዝ ግብዣውን እቀበላለሁ።"》

ምክንያቱም እርሳቸው የተላኩት መልካም ስነ-ምግባራትን ለማሟላት ነው።የስምምነቱ ይዘቱም የመልካም ስነ-ምግባር አካል ነው።ኢስላም የስምምነቱን አብይ ይዘት ያፀድቃል።ይህ ስምምነት በርካታ ሰዎችን ከበደል ታድጓል።

ከ"ሒልፈል ፉዱል" ስምምነት ከምናገኛቸው ትምህርቶች መካከል ዋነኛው፡- "ከተበዳይ ጎን መቆምና በደሉን ማካካስ ነው"።

ውድ አንባቢያን!!!! በዚህ ረገድ የሚወሳ የግል ተሞክሮ አለህን???????

የምን አንብቦ ዝም ነው ፤

🅢🅗🅐🅡🅔 🅛🅘🅚🅔 🅙🅞🅘🅝

በማድረግ ላላወቁት እናሳውቅ።

@𝙋𝘼𝙍𝙏
---------------ይ --------------------ቀ -------------------------ጥ -------------------------------ላ -------------------------------------ል

ክፍል 3 #ይቀጥላል.........


@Alif_media_1 @Alif_media_1
@Alif_media_1

ይ ላ ሉን

@Alif_media_1