Get Mystery Box with random crypto!

የወላጅ  ሀቅ  ------------------------------ ★አላህ ፍጡራንን ከፈጠረ በኃላ | አል ሂዳያ የየቲሞች መርጃና በጎ አድራጎት ጀማአ 0993632424//0703136300አዲስ አበባ

የወላጅ  ሀቅ 
------------------------------
★አላህ ፍጡራንን ከፈጠረ በኃላ አንዱ በአንዱ ላይ ሀቅ እንዲኖረው አደረገ። ባል ሚስቱ ላይ ፣ ሚስት ባልዋ ላይ፣ ጎረቤት በጎረቤትለ ላይ ፣ ብሎም ሙስሊም በሌላው ሙስሊም ላይ ሀቅ እንዲኖረው አደረገ።

•ነገር ግን ከራሱ ሀቅ ቀጥሎ ትልቁ ሀቅ የወላጆች ሀቅ አደረገ

➩የአሏህ መልክተኛ ﷺ እንዲ አሉ አንድ ሰው በአፍንጫው አፈር ላይ ይደፋ ብለው ዱዓ አደረጉ፤ ማነው እሱ ተብለው ሲጠየቁ ወላጆችን አግኝቶ አንዳቸውን ወይም ሁለቱንም አግኝቶ ጀነት መግባት ያልቻለ ሰው ይደፋ ብለው ዱዓ አደረጉ የወላጅ በህይወት መኖር ላንተ ወደ ጀነት የተከፈተ በር ነውና እናት አባትህን ሳትሰላች ተንከባከብ ጥቅሙ ላንተ እንጂ ለነሱ አይደለም!!

አሏህ ሱ,ዐ ስለ ወላጅ ሀቅ ስናገር እንዲህ ይላል:

۞ وَقَضَىٰ رَبُّكَ أَلَّا تَعْبُدُوا إِلَّا إِيَّاهُ وَبِالْوَالِدَيْنِ إِحْسَانًا ۚ إِمَّا يَبْلُغَنَّ عِندَكَ الْكِبَرَ أَحَدُهُمَا أَوْ كِلَاهُمَا فَلَا تَقُل لَّهُمَا أُفٍّ وَلَا تَنْهَرْهُمَا وَقُل لَّهُمَا قَوْلًا كَرِيمًا

➩ጌታህም (እንዲህ ሲል) አዘዘ፡- እርሱን እንጂ ሌላን አትገዙ፡፡ በወላጆቻችሁም መልካምን ሥሩ፡፡ በአንተ ዘንድ ኾነው አንዳቸው ወይም ሁለታቸው እርጅናን ቢደርሱ ፎህ አትበላቸው፡፡ አትገላምጣቸውም፡፡ ለእነርሱም መልካምን ቃል ተናገራቸው፡፡

وَاخْفِضْ لَهُمَا جَنَاحَ الذُّلِّ مِنَ الرَّحْمَةِ وَقُل رَّبِّ ارْحَمْهُمَا كَمَا رَبَّيَانِي صَغِيرًا

➩ለሁለቱም ከእዝነትህ የመዋረድን ክንፍ ዝቅ አድርግላቸው፡፡ «ጌታዬ ሆይ! በሕፃንነቴ (በርኅራኄ) እንዳሳደጉኝ እዘንልላቸውም» በል፡፡

(ሱረቱል ኢስራዕ 23__24)

★ታዲያ የእናት ትርጉም የሁላችንም ቤት ነው ያለው ፣ለምን በእናት ያልተውለደ የለምና።

★ እናታችን ወይም እህታችን ነፍሰጡር በሆነች ጊዜ የምታየው ስቃይ ማየት ብቻ በቂ ነው የእናትን ትልቅነት ለመረዳት ።
አንድ ፀሐፊ ምን ይላል « እኔ ስለ እናት አንብቤም አዳምጬም አውቃለሁ ።ነገር ግን በጣም የተረዳሁት ባለቤቴ ነፍሰጡር ሆና ታየው የነበረው ስቃይ ደረጃ በደረጃ እከታተል ነበር ።የባለ ቤቴ ስቃይ 8 ኛው ወር ላይ እየከፋ ሄደ እንደፈለኩ ልተኛ፣ልብላ፣ ልጠጣ አትችልም ። አሟት ሀኪም ቤት ብወስዳት የሚያስታግስ እንጂ የሚያሽል መድሀኒት  አይሰጧትም ለምን ፅንሱ እንዳይጎዳ።
#የርግዝናው ስቃይ ያለ ሆኖ የቤትም ውጣውረድ እሷንም ይመለከታል ።

★ ይህ ሁሉ ግን ለሷ ምንም አይደለም፣ እንኳን ልትበሳጭ/ ኡፍ ልትል ይቅርና ልጄን መች ይሆን የማቅፈው ብላ ያለየችው ትናፍቃለች ። ይህም ላይሆንም ይችላል  ። ይህ ናት እናት ። ታድያ ለዚች እናት ትልቅ ሀቅ አላት ።

★ አንድ ሰው ዑመር رضى الله عنه  ዘንድ መጣና « እኔ እናቴ በጣም ከማርጀቷ የተነሳ ሽንት ቤት የምወስዳት ተሸክሜያት ነው ድሮ እኔ በጀርባዋ እሸና እንደነበረወ አሁን እሷ ትሸናብኛለችና ሀቋ ተወጥቻለሁኝ»  ብሎ ጠየቃቸው  { አልተወጣህም} { አልተወጣህም}  {አተውጣምም} አሉት ።ምክንኛቱም ያኔ እሷ ያ! ሁሉ ታደርግልህ የነበረው ማደግህን የተመኘች ነበር ። አንተ ይህ ብታደርግም ሞቷን የተመኘህ ነው አሉት ይባላል።


☞ ስለዚህ ይህ ትልቅ ሀቅ በቻልነው አቅም ልንውጣው እንሞክር

☞ በሀያት ካሉ ተውሂድን በማስተማር ከሽርክ እንዲሪቁና ዱንያ አኼራች እንዲያስተካክሉ እንርዳችው

☞ ከሞቱ ዱዓ እናድርግላቸው።

:የወላጅ ሐቅ እና እናት አባትን የማክበር ሲባል …

:ድምፅህን ከድምፃቸዉ በላይ ከፍ አታድርግ፣
:አጉል ክርክር አትከራከራቸው፣
:እነሱ ሣይጨርሱ አትናገር፣
:በሥማቸው አትጥራቸው፣
:እንቅልፋቸዉን ሣይጨርሱ አትቀስቅሣቸው፣
:ለምክኒያት ካልሆነ በስተቀር (አደጋ እንዳያገኛቸዉን ለመሣሠሉት) ከፊት ለፊታቸው አትቅደም፣
:እነርሱ ሣይቀመጡ ቀድመህ አትቀመጥ ፣
:ባሪያ ለጌታዉ እንደሚተናነሰው ሁሉ ተናነስላቸው፣
:ጠርተዉህ ሣይጨርሱ ‘ አቤት ’ በላቸው፣
:ከቤት ወጥተህ በመዘግየት እንዲያስቡ አታድርጋቸው፣
:በሀሳብ ተጨንቀህ አታስጨንቃቸው፣
:በእይታህ አታፍጥባቸው፣
:በንግግርህ አትዳፈራቸው፣
:በቁጣቸው መልሰህ አትቆጣ፣
:በንግግራቸው አትሣቅ, ሙድ አትያዝ፣
:መላና ሀሣባቸዉን አታናንቅ፣
:ሲጨንቃቸዉ አማክራቸው፣
:ሲቸግራቸው እርዳቸው፣
:ሲታመሙ አሣክማቸው፣
:ሲታረዙ አልብሣቸው፣
:ጉዳይቸዉን ሁሉ ጉዳዬ በል፣
:እቅድ ሀሣባቸዉን ተካፈል፣
:ዓላማህን አትደብቃቸው፣
:የሥጋ ዘመዶቻቸዉን ቀጥል፣
:ወዳጆቻቸን አክብርላቸው፣
:ጉዞ ስትወጣ ንገራቸው፣
:የሚወዱትን ዉደድላቸው፣
:እርግማናቸዉን ተጠንቀቅ፣
:እነርሱን ከማስከፋት ፈፅሞ እራቅ፣
:ነገሮችን ቀስ ብለህ አስረዳቸው፣
:በሚገባቸዉ ሁኔታና ቋንቋ ንገራቸው፣
:ዱዓኣቸዉን ፈልግ፣
:ከምርቃታቸው ተሽቀዳደም፣
:ለወላጆችህ  ‘ ጌታዬ ሆይ ! በህፃንነቴ እንዳሳደጉኝ ሁሉ እዘንላቸው ’ የዘወትር ዱዓእህ ይሁን ።

★ አላህ ሆይ ! ጀነት በእግሮቿ ስር እንዳደረከው መኖሪያዋም ጀነት አድርገው ። 

አሚንንን  አላሁመ አሚንንን

ولله أعلم
https://t.me/ALHidayaTv