Get Mystery Box with random crypto!

1.0 ዒድ ሶላት ሑክሙ(ብይኑ) ምንድነው? እዚህ ውስጥ የዒድ ሶላት ብለን ካልን ሁለቱንም ዒዶ | ¶ ፊቅሁል ኢስላም ¶

1.0 ዒድ ሶላት ሑክሙ(ብይኑ) ምንድነው?

እዚህ ውስጥ የዒድ ሶላት ብለን ካልን ሁለቱንም ዒዶችን ግንዛቤ ውስጥ እንክተት(ዒድ አልአድሀ እና ዒድ አልፊጥር)፡፡ አህመድ ከሁለት በአንድ ንግግራቸው፣ ሻፍዒይ ከሁለት በአንድ ንግግራቸው እና አቡ ሀኒፋ ፈርድ(ትዕዛዝ የመጣባት ቅሮት የሌላት) ናት ብለዋል፡፡ ለዚህም ንግግራቸው ያቀረቡት ሀዲስ፦ መልእክተኛው ለሶላተል ዒድ ሴቶችን ሳይቀር ዒድን እንዲጣዱ፣ ሀይድ ላይ ያለች ሴት ሳትቀር ተጥዳ የዒድን ክንውን ከመስገጃዋ ራቅ ብላ እንድትመለከት አዘዋል፡፡[ቡኻሪይ እና ሙስሊም].

1.1 የዒድ ቀን የሚወደዱ ተግባሮች፦
1ኛ፦ለዒድ መጋጌጥ እና መዋብ
ከአብደሏህ ኢብን ዑመር በፀደቀው ኢብን ኡመር የዒድ ዕለት ከኢማም ጋር መስጂድ ፈጅርን ከተጣደ በሗላ ወደ ቤቱ ይመለስና ልክ ለጀናባ እንደሚታጠበው ገላውን ታጥቦ፤ እርሱ ዘንድ ባለው ንፁሁን ልብሱን ለብሶና ሽቶን ተቀብቶ ወደ መስገጃ ቦታ ይመጣ ነበር፡፡[ኢብን አቢ ሸይባህ 181/2].

2ኛ፦ የዒድ አል አድሀ ጊዜ በባዶ ሆድ ወደ ሶላት መስገጃ ቦታ መውጣት
ቡረይዳህ ባስተላለፈው ሀዲስ መልእክተኛው የዒድ አል ፊጥር በሆነ ጊዜ አንዳችን ነገር ሳይበሉ አይወጡም ነበር፡፡ የኡድሒያ(አድሃ) ጊዜ ግን ከሶለት እስኪመለሡ አንዳችንም ነገር አይበሉም ነበር፡፡[ኢብን ማጃህ 1754].
ሰዒድ ኢብን ሙሠይብ እንዲህ ይላል፦ ሙስሊሞች የኢድ አል ፊጥር ጊዜ ከሶላት በፊት ይበሉ ነበር፡፡ ይህን ድርጊታቸውን ግን ለኢድ አል አድሃ አይፈፅሙም ነበር፡፡[ማሊክ ሙወጧ ላይ 128/1 ዘግቦታል].

የዒድ አል አድሃ ጊዜ ምግብ ሳይመገቡ ወደ ሶላት መውጣት የተፈለገው ለምንድነው?
ኢብን ሀጀር አሏህ ይዘንለትና እንዲህ ይላል፦ የኢድ አል አድሃ ጊዜ መመገብ መዘግየት የተፈለገበት ጥበብ(ምክንያት) በቀኑ እርድ የሚደረግበት ስለሆነ ከዛ ካዘጋጀው ኡድሂያ(እርድ) እንዲበላ ተፈልጎ ነው፡፡
[ፈትሁል ባሪ 518/2].

3ኛ፡ የዒድ ሶላትን ከመስጂድ ውጪ መስገድ

አቢ ሰዒድ አልኹድሪይ አሏህ መልካም ስራውን ይውደድለትና እንዲህ ይላል፦ መልእክተኛው የፊጥር ቀንና የአድሃ ቀን ለሶላት ወደ ሙሶላ(ወደ መስገጃ ቦታ) ይወጡ ነበር፡፡
[ ቡኻሪይ እና ሙስሊም]
ሐፊዝ ኢብን ሀጀር እንዲህ ይላሉ፦ እዚህ ሀዲስ ላይ ለዒድ ሶላት ወደ መስገጃ ቦታ መውጣት እንዳለ እናያለን፡፡ ለዶሩራ(ለአሳሳቢ ጉዳይ) ካልሆነ በስተቀር ሶላቷን በመስጂድ መስገድ አይበቃም፡፡ በሌላም ቦታ ላይ እንዲህ ይላል፦ በዚህ ሀዲስ ለጥ ወዳለ ቦታ(ሜዳ) የዒድን ሶላት መስገድ የተወደደ ነው ብለው ማስረጃ አደረጉ፡፡ መልእክተኛው መስጂድ ትልቅ ትሩፋት ገመኖሩም ጋር መስጂድን ትተው ከመስጂድ ውጪ መስገዳቸው ሜዳ ላይ መስገድ መስጂድ ከመስገድ በላጭ መሆኑን ያሳያል፡፡[ፈትሁል ባሪ 449/2]. ነገር ግን ዝናብ ወይም ሌላ ምክንያት ካለ መስጂድ ብትሰገድ አትጠላም፡፡

4ኛ፡ ወደ መስገጃ ቦታ በእግር መጓዝ

ዒራቂይ ለዒድ ሶላት ወደ መስገጃ ቦታ በእግር መጓዝ የተወደደች ናት ይላል፡፡ ለዚህም ንግግሩ ያቀረበው ማስረጃ ጥቅል የሆነው የአቢ ሁረይራን ሀዲስ ሲሆን መልእክተኛው እንዲህ አሉ፦ ወደ ሶላት በመጣችሁ ሰዓት በእግራቹ ተጓዦች ሆናችሁ ምጧት፡፡[ቡኻሪይ እና ሙስሊም].

1.2 ለዒድ ሶላት ከቤቱ ወደ መስገጃ ቦታ መቼነው የሚወጣው?

ይህንን አስመልክቶ የመጣ ታማኝ ሀዲስ ስላልተዘገበ እንደ ሰዎች አወጣጥ ሊለያይ ይችላል፡፡ ነገር ግን ከአንዳንድ ሶሀቦችና ታብእዮች ከሱብሒ ሶላት በሗላ ለዒድ ሶላት እንደሚወጡ ዘገባዎች ተገኝተዋል፡፡ ከነዚህም፦
ዘይድ ኢብን አቢ ዑበይድ እንዲህ ይላል፦ ከሰለማህ ኢብን አክዋዕ ጋር በመልእክተኛው መስጂድ የሱብህ ሶላትን አብሬው ሰገድኩ፡፡ ከዚያም እሱ ወጣ እኔም ተከትዬው የመስገጃው ቦታ እስክንደርስ ድረስ ወጣሁኝ፡፡ ከዚያም ኢማሙ እስኪመጣ ድረስ ተቀመጠ እኔም ተቀመጥኩኝ፡፡[ፈርያቢ/29/ ሶሂህ በሆነ ሰነድ ዘግቦታል].
አብዱራህማን ቢን ሀርመላህ ከሰዒድ ኢብነል ሙሰይብ ጋር ሱቢህን ከኢማም ጋር ካሰላመቱ በሗላ ወደ መስገጃ ቦታ የዒድ ለት ይሄድ ነበር፡፡[ኢብን አቢ ሸይባህ 123/2]


ሼር
••••••••••••¶•••••••••••
T.me/alfiqhulmuyser
••••••••••••¶•••••••••••c