Get Mystery Box with random crypto!

¶ ፊቅሁል ኢስላም ¶

የቴሌግራም ቻናል አርማ alfiqhulmuyser — ¶ ፊቅሁል ኢስላም ¶
የቴሌግራም ቻናል አርማ alfiqhulmuyser — ¶ ፊቅሁል ኢስላም ¶
የሰርጥ አድራሻ: @alfiqhulmuyser
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.37K
የሰርጥ መግለጫ

▋ 📚 የፊቅህ ትምህርቶች 📚
▋ ጦሀራ
▋ ሰላት
▋ ጀናዛ
▋ ዘካ
▋ ፆም
▋ ሀጅ
▋🔖አላማችን
▋📌ፊቅህን በቀላል አቀራረብ ማቅረብ፡፡
▋📌 ቁርዓን እና ሱናን መሰረት ባደረገ መልኩ ከኡለሞች አቋም ለመረጃ የቀረበዉን መለየት፡፡
╭─┅──══──┅──══──┅─╮
๏ተግባራዊ እውቀት
╰─┅──══──┅──══──┅─╯
ለአስተያየት @alfiqhulmuyserBot

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0

የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-06 20:51:15 ዐሹራ (عاشوراء)
.
➊ አሹራ ሚባለው ምን ቀን ነው?
.
➪ አብዛኛዎቹ ኡለሞች ባሉበት አቋም መሰረት አሹራ የሚባለው ከሙሀረም አስረኛው ቀን ነው። አሹራም የተባለበት ምክንያት አስረኛው ቀን ለማለት ተፈልጎበት ነው።ልክ እንደዚሁ ዘጠናኛው ቀን ታሱአ ይባላል።
.
➦አንዳንድ ኡለሞች የሙሀረምን ዘጠነኛው ቀን ነው አሹራ ሚባለው ቢሉም ከቋንቋ አንፃር እንኳን ስናየው ትክክል አለመሆኑን እንረዳለን።

. የዘንድሮ የዐሹራ ቀን (ሙሐረም 10) ነገ እሁድ 9 ሲሆን ሰኞ 10 ነው በመሆኑም ዓሹራእ ሰኞ ስለሆነ እሁድና ሰኞን መፆሙ የተወደደ ነው አላህ ይወፍቀን ።አሏህ በሰላም ያድርሰን።
.
❷ አሹራ ሚፆመው ለምንድነው?
.
➪ የአሹራ ቀን የሚፆምበት ዋነኛ ምክንያት አላህ ሙሳን እና በኒ ኢስራኢሎችን ከፊርአው ነፃ ያወጣበት ቀን ስለሆነ ነው።
.
▩ ማስረጃው
.
ኢብን አባስ እንዲህ ይላል
(( የአላህ መልእክተኛ ﷺ መዲና ሲገቡ አይሁዶች የአሹራን ቀን ሲፆሙ አዯቸውና
"ይህ ምንድነው?" ብለው ጠየቋቸው
ከዛም የሁዶች ሲመልሱ
" ይህ ደግ ቀን ነው አላህ በኒ ኢስራኢሎችን ከጠላታቸው ነፃ ያወጣበት ቀን ነው። ሙሳ ለምስጋና ፆሞታል" አሉ
የአላህ መልእክተኛም ﷺ
"እኔ በሙሳ ከናንተ ይበልጥ ተገቢ ነኝ" አሉና ፆሙት በመፆምም አዘዙ
(ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)
.
❸ የአላህ መልእክተኛ ﷺ ፆመውታል?
.
➩ አዎ የአላህ መልእክተኛ ﷺ የአሹራ ፆምን ይፆሙት ነበር
.
▩ ማስረጃው
.
አኢሻ እንዲህ ትላለች
(የአሹራ ቀን ቁረይሾች በጃሂሊያ ግዜ ይፆሙት ነበር የአላህ መልእክተኛም ﷺ ይፆሙት ነበር...)
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል
.
❹ ከሙስሊሞች ውጪ ይህን ቀን ሚፆሙት አሉ?
.
➪ አዎ ከሙስሊሞች ውጪም ይህን ቀን ሚፆሙት ነበሩ እነሱም
.
➀ ሙሽሪኮች ፦ማስረጃው ከላይ በተራ ቁጥር ❸ ላይ ያሳለፍነው የአኢሻ ሀዲስ ነው
.
➁ አይሁዶች ፦ማስረጃው ከላይ በተራ ቁጥር ❷ ላይ ያሳለፍነው የኢብን አባስ ሀዲስ ነው
❺ ግዴታ ነው ወይስ ሱና?
.
➪ ረመዳን ከመደንገጉ በፊት የአሹራ ፆም ሙስሊሞች ላይ በግዴታነት መልኩ ተደንግጎ እንደነበር የሚጠቁሙ ሀደሶች አሉ ከነዛህ መሀከል ኢማም ቡኻሪ የዘገቡት የሰለማ ቢን አውከአ ሀዲስ አንዱ ነው። በዛ ሀዲስ ላይ መልእክተኛው ﷺ ሳያቅ ጠዋቱን የበላ ሰው የተቀረውን የቀን ክፍለ ግዜ እንዲፆም አዘዋል።
.
➪ ይህ የግዴታነት ትእዛዝ ግን በሗላ ላይ ተሽሮ በበርካታ ሀዲሶች ላይ እንደመጣው የአላህ መልእክተኛ ﷺ የፈለገ ሰው ይፁም ብለው ተናግረዋል።
.
▩ በመሆኑም የአሹራ ፆም የጠነከረ ሱና እንጂ ግዴታ አደለም።
.
❻ አስረኛው ቀን ብቻ ነው ሚፆመው?
.
➪ የአሹራን ቀን ብቻውን ነጥሎ ከመፆም ይልቅ ከሱ በፊት አንድን ቀን አስቀድሞ ፆሞ የአሹራንም ቀን አንድ ላይ መፆሙ የተወደደ ነው።
.
➦ ይህ ማለት ዘጠነኛውንና አስረኛውን ቀን ማለት ነው።
.
➦ ወይ ደግሞ አስራ አንደኛውንም ቀን አስከትሎ መፆሙ ይወደዳል።
.
▩ ማስረጃውም
.
አብደላህ ኢብን አባስ ባወራው ሀዲስ የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል
"አላህ ካለ የሚመጣው አመት ዘጠነኛውን ቀን እንፆማለን"
ነገር ግን የሚቀጥለው አመት ሳይመጣ መልእክተኛው ሞቱ
ሙስሊም ዘግቦታል
.
▤ አንድ ቀን አስቀድሞ ወይም ደግሞ አንድ ቀን አስከትሎ መፆሙ የተደነገገበት ምክንያትን ኡለሞች ሲያብራሩ ብዙ የሚጠቅሷቸው ነገሮች ቢኖሩም በዋነኝነት ግን ከአህለል ኪታቦች ለመለየት ሲባል የሚለው ይበልጥ ሚዛን ይደፍል።ምክንያቱም የአላህ መልእክተኛ ሚቀጥለው አመት ብደርስ ዘጠነኛውን ቀን ጨምሬ እፆማለው ያሉት አስረኛውን ቀን አህለል ኪታቦች እንደሚያልቁት ሲነገራቸው ነው።
.
➪ አንዳንድ ኡለሞች አስረኛውን ቀን ብቻ ነጥሎ መፆሙ የተጠላ እንደሆነ ይገልፃሉ።
.
➦ ነገር ግን ሸይኹል ኢስላም ዘጠነኛውን ወይም አስራ አንደኛውም መፆም ላልቻለ ሰው አስረኛውን ብቻ ቢፆምም እንደማይጠላ ይገልፃል። የሚችል ሰው ግን አስረኛውን ብቻ መነጠሉ ተገቢ እንዳልሆነ ይጠቅሳል።
.
❼ የሚወደደው አፇፇም
.
➪ የሚወደደው አፇፇም በቅደም ተከተል ሲቀመጥ
.
⓵ ዘጠነኛውን አስረኛውንና አስራ አንደኛውን ቀን ሶስቱን በተከታታይ መፆም (3 ቀኖች)
.
⓶ ዘጠነኛውንና አስረኛውን መፆም (2 ቀኖች)
.
⓷ አስረኛውን ቀን ብቻ መፆም (1 ቀን)
.
ይህንን ቅደም ተከተል ኢብኑል ቀይም ዛደል መአድ ላይ እንዲሁም ኢብን ሀጀር ፈትሀል ባሪ ላይ መርጠውታል። ኢብን ተይሚያም ኢቅቲዳ ኪታቡ ላይ ከኢማም አህመድ የዚህን አምሳያ ጠቅሷል።
.
➦ በርግጥ ሌሎች ኡለሞች የመረጣቸው ሌሎች ቅደም ተከተሎች ቢኖሩም ከመጡ ሀዲሶች አንፃር ከላይ የጠቀስነው ቅደም ተከተል ይበልጥ አመዛኙ አቋም ነው።
.
❽ የአሹራ ፆም ያለው ትሩፍት
.
➪ ኢማሙ ነሳኢ በዘገቡት ሀዲስ የአላህ መልእክተኛ የአሹራ ፆም ያለፈውን አመት ወንጀል ያስምራል ብለዋል።
.
ኻሊድ ሙሀመድ (አቡ ሱለይማን)

#ሼር
¶ https://t.me/alfiqhulmuyser ¶
1.3K viewsedited  17:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-04 22:21:29 ዝናብ በሚዘንብበት ወቅት የሚባል

اَللَّهُمَّ صَيِّبًا نَافِعًا.

‘አልሏሁምመ ሰይበን ናፊዐን

አላህ ሆይ! ጠቃሚ ዝናብ (አድርገው)፡፡

ዝናብ ከዘነበ በኋላ የሚባል ዚክር

مُطِرْنَا بِفَضْلِ اللهِ وَرَحْمَتِهِ.

‘ሙጢርና ቢፈድሊልላሂ ወራሕመቲሂ

በአላህ ትሩፋትና እዝነት ዝናብ ለማግኘት በቃን፡፡
@alfiqhulmuyser
700 viewsedited  19:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-27 12:35:37                      አስተውሉ!!

▧ قَـالَ الشَّـيخ العلّامـة ابنُ بَاز -رَحِمَهُ الله-

قـراءة القـرآن من دون تحريك الـشفتين

« لا يعـتبر قـارئا ولا يحصل لـه فضل قـراءة الـقرآن إلا إذا تلفظ »
| [ الفتاوى (8/363) ] |

❖አንድ ሰዉ ቁርአንን ሲቀራ ከንፈሮቹን እያንቀሳቀሰ ሊቀራ ግድ ነዉ ይህ ካልሆነ ቁርአንን ቀርቷል ሊባል እንዲሁም የመቅራት ቱሩፋት ሊያገኝ አይችልም፡
          [አልፈታዋ ኢብነ ባዝ 8/363]

https://t.me/alfiqhulmuyser
373 views09:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 06:45:44 ዒድ ሙባረክ
تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال
كل عام وانتم بخير عيد مبارك
749 views03:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 06:45:32 ጃቢር ባስተላለፈው ሀዲስ እንዲህ ይላል፦
መልእክተኛው ﷺ ለዒድ ሶላት በሚወጡ ጊዜ (የሄዱበትን) መንገድ ይቀይሩ ነበር፡፡
[ቡኻሪይ ዘግበውታል]

መንገድ የመቀያየሩ ጥበብ ምንድ ነው?

ከኢድ ቀን ሱናዎች ውስጥ አንዱ መንገድ መቀያየር ነው። እንደሚታወቀው የአላህ መልእክተኛ ለኢድ ሶላት በወጡበት መንገድ ተመልሰው አይመጡም ነበር። ሲወጡ በሌላ ሲመለሱ በሌላ መንገድ ነበር። ይህ የሆነበት ምክንያት ምንድ ነው? መልሱ ከኢብኑ ኡሰይሚን፦

ኢብኑ ኡሰይሚን አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ይላሉ። በኢድ ሶላት መንገድ የምንቀይርበት ምክንያት፦
የአላህ መልእክተኛ ስለሰሩት እሳቸውን ለመከተል ነው።

ከፊል ኡለማዎች……
ምክንያቱ ለሙስሊም ባለሱቆችና በዛ አካባቢ ላሉ ሰዎች ይህንን የዲን መገለጫ ለማሳየት ነው ብለዋል።
ከፊል ኡለማዎች……
ምክንያቱ የውመል ቂያማ የሄድንበትና የተመለስንበት መንገድ እንዲመሰክርልን ነው ብለዋል።
ከፊል ኡለማዎች……
ምክንያቱ በሁለቱም መንገዶች ላይ ላሉ ምስኪኖችና ድሆች ሰደቃ ለማዳረስ ነው ብለዋል።

ምክንያቱና ጥበቡ ምንም ይሁን ምንም ውዱ ነብያችን ስለሰሩት የሳቸውን ፈለግ ህያው ለማድረግ ብለን ልንፈፅመው ይገባል።

@alfiqhulmuyser
625 views03:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 06:45:32 1.3 ሴቶችና ህፃናት ለዒድ መውጣት

በጥቅሉ ሴቶች (ያገባችም-ያላገባች) ለዒድ ሶላት እንዲወጡ መልእክተኛው አዘዋል፡፡ ሀይድ ላይ ያሉት ሴቶች ሳይቀሩ ለዒድ ተጥደው የሙስሊሞችን ዳዕዋና መልካም ስራ ይመለከታሉ፡፡ ህፃናትም ለዒድ እንደሚወጡ ከአነስ የተዘገው ሀዲስ ማስረጃ ይሆናል፡፡[ቡኻሪይ 977].

1.4 መንገድ መቀየር
ጃቢር ባስተላለፈው ሀዲስ እንዲህ ይላል፦ መልእክተኛውﷺ ለዒድ ሶላት በሚወጡ ሰአት መንገድን ይቀይሩ ነበር፡፡[ቡኻሪይ ዘግበውታል].
አቢ ሑረይራ አሏህ መልካም ስራውን ይውደድለትና እንዲህ ይላል፦ መልእክተኛውﷺ
ለዒድ በወጡ ጊዜ መጀመሪያ የወጡበትን መንገድ ቀይረው ይመለሡ ነበር፡፡
[ኢብን ማጃህ እና ቲርሚዚ/ሀሰን/].

ቲርሚዚይ አሏህ ይዘንላቸውና እንዲህ ይላሉ፦ ከፊል የእውቀት ባልተቤቶች ይህንን ሀዲስ በመያዝ ለኢማም መንገድ መቀየር የተወደደ ነው ብለዋል፡፡
ኢማም አሽሻፍዒይ እንዲህ ይላሉ፦ መንገድ መቀየር ለኢማም፣ ኢማምንም ተከትሎ ለሚሰግድ ባጠቃላይ የተወደደ ነው፡፡ [ኡም].
ሁሉንም ያጠቃለለ ነው በሚለው ብዙ የእውቀት ባልተቤቶች ተናግረዋል[ሀፊዝ ኢብን ሀጀር].

1.5 የዒድ ሶላት አሠጋገድ

የዒድ ሶላት ሁለት ረከዓ ያላት ስትሆን በመጀመሪያው ሰባት ተክቢራን ሲያደርግ በሁለተኛው ረከዓ ላይ ደግሞ አምስት ተክቢራዎችን ያደርጋል፡፡ አዒሻ አሏህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና፦ መልእክተኛው ﷺ ለዒድ ፊጥር እና አድሃ ጊዜ ሰባትና አምስት ተክቢራን አደረጉ]. [ሀዲሱን የሀሠን ደረጃ ያደርሱታል].

1.6 በተክቢራዎች መሀከል የሚባል ዚክር አለን?

ይህን አስመልክቶ ከመልእክተኛው ﷺ የተረጋገጠ የሆነ(ሀዲስ) ማስረጃ የለም፡፡ ነገር ግን ኢብን መስኡድ በተክቢራ መሀከል አሏህ ላይ ምስጋናንና ውዳሴን ካደረገ በሗላ መልእክተኛው ﷺ ላይ ውዳሴን እንደሚያወርድ የተረጋገጠ ሰነድ መጥቷል፡፡ [ሰነዱን አልባኒ ሀስን ብለውታል].
ኢብን ኡሠይሚን እንዲህ ይላሉ፦ ይህ ነጥብ ሁሉንም ያማከለ በመሆኑ፤ በተክቢራ መሀከል ዚክርን ካለ እሱ በመልካም ላይ ነው፡፡ ተክቢራንም ብቻ ያለ እሱ በመልካም ላይ ነው፡፡ ነው የምንለው፡፡[ሸርህ ሙምቲዕ].

1.7 ተኪቢራ ማለት ሁክሙ(ብይኑ) ምንድነው?

ጁምሑሮች(አብዛኛዎቹ የእውት ባልተቤቶች) ያሉበት የሆነው የዒድ ተክቢራ ሱንና እንደሆነች ነው፡፡ ስለዚህ ሰውየው አውቆም ይሁን ሳያውቅ ቢተዋት ሰላቱ ላይ ምንም ተፅእኖ አታሳድርም፡፡
ኢብን ቁዳማ እንዲህ ይላል፦ በዚህ ነጥብ ላይ ምንም አይነት ተፃርኖ አላውቅም፡፡
ኢቢ ሀኒፋና ማሊክ ሲቀሩ ሌሎቹ የእውቀት ምሁራን ተክቢራዎቹ ሳያስገኝ ቢቀር የመርሳት ሱጁድ አድርግ አይባልም ብለዋል፡፡

1.8 በየተክቢራዎች እጅን ማንሣት

ይህ ነጥብ የእውቀት ባልተቤቶች ዘንድ ልዩነት ያለው ነጥብ ነው፡፡ ከፊሎቹ እጅ ማንሳትን ሲከለክሉ ሌለኞቹ ደግሞ እጅ ማንሠትን የፈቀዱ አሉ፡፡ ከልካዮቹ ለክልከላቸው ያቀረቡት ከመልእክተኛው ﷺ ትክክል(ሶሂህ) የሆነ ማስረጃ እጅ በማንሣት ስላልተገኘ ነው ብለዋል፡፡ ይህ ንግግር የማሊኪያዎች ንግግር ነው፡፡

1.9 ለዒድ ሶላት የሚቀሩት የቁርአን አንቀፆች

ኑእማን ኢብን በሺይር እንዲህ ይላል፦ መልእክተኛው ﷺ ለሁለቱም ዒዶችና ለጁምዓ በሡረተል አዕላ እና በሡረቱል ጋሺያህ ያሰግዱ ነበር፡፡ ዒድና ጁምአም በአንድ ቀን በገጠሙም ጊዜ በጁምአም በዒድም ድጋሜ ይቀሯቸው ነበር፡፡[ሙስሊም].

ከአቢ ዋቂድ አልለይሲ ለዑመር መልእክተኛውﷺ በዒድ አልፈጥር እና በዒድ አል አድሃ ጊዜ ምንን የቀሩ ነበር? እሱም እንዲህ አለው፦ መልእክተኛው ﷺ በሁለቱም ዒዶች ላይ በሱረቱል "ቋፍ" እና በሡረቱል "ቀመር" ይሰግዱ ነበር፡፡[ሙስሊም].

2.0 ከዒድ ሶላት በፊት ወይም በሗላ የሚሠገዱ ሶላቶች አሉን?

ኢብን አባስ አሏህ መልካም ስራውን ይመንዳለትና መልእክተኛው የዒድ ለት ወጡና ሁለት ረከዓ(የዒድ ሶላትን) ሰገዱ፡፡ ከዚህ ሶላታቸው በፊትም በሗላም ሌላን አልሠገዱም፡፡ [ቡኻሪይና ሙስሊም] .

ኢማም ሸውካኒይ እንዲህ ይላል፦ እዚህ ሀዲስ ላይ ከዒድ ሶላት በፊትም ይሁን በሗላ መስገድ የተጠላ መሆኑን ያመላክታል፡፡[ነይሉል አውጣር 371/3].
ዙህሪይ እንዲህ ይላል፦ ከኡለማዎቻችን ከዚህ ኡማህ ሰለፎች ይህንን ብሏል ያለን አንድንም አልሠማሁም፡፡[ዓውኒል መዕቡድ16/4].
ሀፊዝ ኢብን ሀጀር እንዲህ ይላሉ፦ ገዳዩ፦ለዒድ ሶላት ሱንና ከፊቷም ሆነ ከበስተሗላዋ የመጣላት ምንም ማስረጃ የለም፡፡ የጁምዓን ክንውን ለሷ ያደረጉ ሲቀሩ፡፡ ምናልባት ወቅቱ ለሶላት በየትኛውም ጊዜ መስገድ የተጠላበት ወቅት ከሆነ እንጅ ልቅ የሆነውን ትርፍ ሶላት እሱን የሚከለክል የተነጠለ ማስረጃ አልፀደቀም፡፡[ፈትህ አልባሪ 476/2].
ሸውካኒይ እንዲህ ይላል፦ ይህ የሀፊዝ ኢብን ሀጀር ንግግር ማስረጃ በምታስፈርደው አካሄድ የተቀመጠ እውነት ንግግር ነው፡፡ ትርፍ የሆኑ ሶላቶች ላይ ክልከላን የሚያመላክት ማስረጃ የለም፡፡ እንዲሁም ማስረጃ ነጥሎ የጠቀሰውን ድርጊትንም አይከለክልም፡፡ ልክ ተህየተል መስጂድ ይመስል፤ የዒድ ሶላት በመስጂድ ከተሰገደች፡፡ [ነይሉል አውጣር 373/3].

ሌላው ከዒድ ሶላትም በሗላ መልእክተኛው ﷺ ማረፊያቸው ዘንድ ሁለት ረከዓን እንደሰገዱ ከሰዒድ ኢብን ጁበይር ሀሰን በሆነ ዘገባ ተዘግቧል፡፡ ስለዚህ ያለፈውንና ይህንን ሀዲስ ስናስማማ፦ ከዒድ ሶላት በሗላ እዛው በመስገጃው ስፍራ አይሰገድም፡፡ ነገር ግን ማረፊያው ሲደርስ ይፈቀዳል፡፡ የዒድ ሱንና ናትም አይባልም፡፡ ሶላት አድ ዱሃንም ሊሆን ይችላልና መልእክተኛው የሰገዱት፡፡

ሼር
••••••••••••¶•••••••••••
T.me/alfiqhulmuyser
••••••••••••¶•••••••••••
438 views03:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 06:45:31 1.0 ዒድ ሶላት ሑክሙ(ብይኑ) ምንድነው?

እዚህ ውስጥ የዒድ ሶላት ብለን ካልን ሁለቱንም ዒዶችን ግንዛቤ ውስጥ እንክተት(ዒድ አልአድሀ እና ዒድ አልፊጥር)፡፡ አህመድ ከሁለት በአንድ ንግግራቸው፣ ሻፍዒይ ከሁለት በአንድ ንግግራቸው እና አቡ ሀኒፋ ፈርድ(ትዕዛዝ የመጣባት ቅሮት የሌላት) ናት ብለዋል፡፡ ለዚህም ንግግራቸው ያቀረቡት ሀዲስ፦ መልእክተኛው ለሶላተል ዒድ ሴቶችን ሳይቀር ዒድን እንዲጣዱ፣ ሀይድ ላይ ያለች ሴት ሳትቀር ተጥዳ የዒድን ክንውን ከመስገጃዋ ራቅ ብላ እንድትመለከት አዘዋል፡፡[ቡኻሪይ እና ሙስሊም].

1.1 የዒድ ቀን የሚወደዱ ተግባሮች፦
1ኛ፦ለዒድ መጋጌጥ እና መዋብ
ከአብደሏህ ኢብን ዑመር በፀደቀው ኢብን ኡመር የዒድ ዕለት ከኢማም ጋር መስጂድ ፈጅርን ከተጣደ በሗላ ወደ ቤቱ ይመለስና ልክ ለጀናባ እንደሚታጠበው ገላውን ታጥቦ፤ እርሱ ዘንድ ባለው ንፁሁን ልብሱን ለብሶና ሽቶን ተቀብቶ ወደ መስገጃ ቦታ ይመጣ ነበር፡፡[ኢብን አቢ ሸይባህ 181/2].

2ኛ፦ የዒድ አል አድሀ ጊዜ በባዶ ሆድ ወደ ሶላት መስገጃ ቦታ መውጣት
ቡረይዳህ ባስተላለፈው ሀዲስ መልእክተኛው የዒድ አል ፊጥር በሆነ ጊዜ አንዳችን ነገር ሳይበሉ አይወጡም ነበር፡፡ የኡድሒያ(አድሃ) ጊዜ ግን ከሶለት እስኪመለሡ አንዳችንም ነገር አይበሉም ነበር፡፡[ኢብን ማጃህ 1754].
ሰዒድ ኢብን ሙሠይብ እንዲህ ይላል፦ ሙስሊሞች የኢድ አል ፊጥር ጊዜ ከሶላት በፊት ይበሉ ነበር፡፡ ይህን ድርጊታቸውን ግን ለኢድ አል አድሃ አይፈፅሙም ነበር፡፡[ማሊክ ሙወጧ ላይ 128/1 ዘግቦታል].

የዒድ አል አድሃ ጊዜ ምግብ ሳይመገቡ ወደ ሶላት መውጣት የተፈለገው ለምንድነው?
ኢብን ሀጀር አሏህ ይዘንለትና እንዲህ ይላል፦ የኢድ አል አድሃ ጊዜ መመገብ መዘግየት የተፈለገበት ጥበብ(ምክንያት) በቀኑ እርድ የሚደረግበት ስለሆነ ከዛ ካዘጋጀው ኡድሂያ(እርድ) እንዲበላ ተፈልጎ ነው፡፡
[ፈትሁል ባሪ 518/2].

3ኛ፡ የዒድ ሶላትን ከመስጂድ ውጪ መስገድ

አቢ ሰዒድ አልኹድሪይ አሏህ መልካም ስራውን ይውደድለትና እንዲህ ይላል፦ መልእክተኛው የፊጥር ቀንና የአድሃ ቀን ለሶላት ወደ ሙሶላ(ወደ መስገጃ ቦታ) ይወጡ ነበር፡፡
[ ቡኻሪይ እና ሙስሊም]
ሐፊዝ ኢብን ሀጀር እንዲህ ይላሉ፦ እዚህ ሀዲስ ላይ ለዒድ ሶላት ወደ መስገጃ ቦታ መውጣት እንዳለ እናያለን፡፡ ለዶሩራ(ለአሳሳቢ ጉዳይ) ካልሆነ በስተቀር ሶላቷን በመስጂድ መስገድ አይበቃም፡፡ በሌላም ቦታ ላይ እንዲህ ይላል፦ በዚህ ሀዲስ ለጥ ወዳለ ቦታ(ሜዳ) የዒድን ሶላት መስገድ የተወደደ ነው ብለው ማስረጃ አደረጉ፡፡ መልእክተኛው መስጂድ ትልቅ ትሩፋት ገመኖሩም ጋር መስጂድን ትተው ከመስጂድ ውጪ መስገዳቸው ሜዳ ላይ መስገድ መስጂድ ከመስገድ በላጭ መሆኑን ያሳያል፡፡[ፈትሁል ባሪ 449/2]. ነገር ግን ዝናብ ወይም ሌላ ምክንያት ካለ መስጂድ ብትሰገድ አትጠላም፡፡

4ኛ፡ ወደ መስገጃ ቦታ በእግር መጓዝ

ዒራቂይ ለዒድ ሶላት ወደ መስገጃ ቦታ በእግር መጓዝ የተወደደች ናት ይላል፡፡ ለዚህም ንግግሩ ያቀረበው ማስረጃ ጥቅል የሆነው የአቢ ሁረይራን ሀዲስ ሲሆን መልእክተኛው እንዲህ አሉ፦ ወደ ሶላት በመጣችሁ ሰዓት በእግራቹ ተጓዦች ሆናችሁ ምጧት፡፡[ቡኻሪይ እና ሙስሊም].

1.2 ለዒድ ሶላት ከቤቱ ወደ መስገጃ ቦታ መቼነው የሚወጣው?

ይህንን አስመልክቶ የመጣ ታማኝ ሀዲስ ስላልተዘገበ እንደ ሰዎች አወጣጥ ሊለያይ ይችላል፡፡ ነገር ግን ከአንዳንድ ሶሀቦችና ታብእዮች ከሱብሒ ሶላት በሗላ ለዒድ ሶላት እንደሚወጡ ዘገባዎች ተገኝተዋል፡፡ ከነዚህም፦
ዘይድ ኢብን አቢ ዑበይድ እንዲህ ይላል፦ ከሰለማህ ኢብን አክዋዕ ጋር በመልእክተኛው መስጂድ የሱብህ ሶላትን አብሬው ሰገድኩ፡፡ ከዚያም እሱ ወጣ እኔም ተከትዬው የመስገጃው ቦታ እስክንደርስ ድረስ ወጣሁኝ፡፡ ከዚያም ኢማሙ እስኪመጣ ድረስ ተቀመጠ እኔም ተቀመጥኩኝ፡፡[ፈርያቢ/29/ ሶሂህ በሆነ ሰነድ ዘግቦታል].
አብዱራህማን ቢን ሀርመላህ ከሰዒድ ኢብነል ሙሰይብ ጋር ሱቢህን ከኢማም ጋር ካሰላመቱ በሗላ ወደ መስገጃ ቦታ የዒድ ለት ይሄድ ነበር፡፡[ኢብን አቢ ሸይባህ 123/2]

ሼር
••••••••••••¶•••••••••••
T.me/alfiqhulmuyser
••••••••••••¶•••••••••••c
395 views03:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 08:53:47 ለኡድሒያ የሚበቃው እንሠሣ ተቀባይነት ያለው የእድሜ ገደብ፦
ጃቢር አሏህ መልካም ስራውን ይውደድለትና ባወራው ሀዲስ መልእክተኛው እንዲህ ብለዋል፦ "እድሜያቸው መካከለኛ(የደረሱ)
/ከግመል፣ላም፣በሬ፣ፍየል/የሆነቱን እንጂ እንዳታርዱ፡፡ ነገር ግን እናንተ ላይ ጫና የሚያመጣ ከሆነ ከበግ(ትንሿን) እረዱ፡፡[ሙስሊም ዘግበውታል ]
ይህ ሀዲስ ለኡድሒያ እድሜ መስፈርት እንደሆነ ከሚያመላክቱ ሀዲሶች አንዱ መሆኑ ነው፡፡
ከግመል አምስ አመት፣ከከብት(ከላም/ላም) ሁለት አመት፣ ከፍየል አንድ አመት የሆናቸው፡፡[ሸርህ ሙምቲዕ 460/7].

በበግ የእድሜ ላይ ግን ልዩነት ያመጡ ሲሆን፤ ከፊሎቹ አመት የሞላት ፣ ስድስት ወር ፣ ስምንት ወር ብለው ጠቅሰዋል፡፡ [ነይሉል አውጣር 302/5].

ከላይ ያሣለፍነው የጃቢር ሀዲስን ይዘው፤ የሀዲሱንም ውጫዊ ገለፃውን በመያዝ ከኢብን ኡመርና ከዙህሪይ በበግ(ትንሹን) አይበቃም ብለዋል፡፡
ኢማም አንነወዊይ እንዲህ ይላል፦ ለኡድሒያ እርድ ከበግ(ትንሹ)ን ማረድ ፤ከሱ ውጪ ሌላ ተገኝቶም ይሁን ሳይገኝ ለእርድ እንደሚበቃ ከእውቀት ባለቤቶች የአጠቃላዮቹ ምርጫ ነው፡፡ይህንን ሀዲስንም ከበግ(ትንሹ) ውጪ ማረድ የተወደደ መሆኑን ነው የገለፁት፡፡ ሀዲሱ ላይ ግልፅ የሆነ ክልከላ የለም ፡፡ የሀዲሱንም ውጫዊ ገለፆ እንደማንይዝ ሁሉም የተስማማበት ነው፡፡
[ፈትሁል ባሪ ላይ ኢብን ሀጀር ይህን ንግግር አጠንክሮታል 15/10].

የእርዱ ጊዜ

አነስ አሏህ መልካም ስራውን ይውደድለትና የአሏህ መልእክተኛ የእርዱ ቀን እንዲህ አሉ፦ ከሶላት በፊት ያረደ አንደገና ይረድ፡፡ በሌላ ዘገባም፦ ከሶላት በፊት ያረደ፤ ያረደው ለራሱ ነው፡፡ ከሶላት በሗላ ያረደ በእርግጥም እርዱን አሟልቷል፡፡የሙስሊምችንም መንገድ ገጥሞል(አግኝቷል)፡፡[ቡኻሪና ሙስሊም].
ይህ ሀዲስ እንደሚያመላክተው ከሆነ የመጀመሪያው የእርድ ጊዜ ከሶላተል ኢድ በሗላ እንደሆነ ነው፡፡ ነገር ግን ከሶላት በፊት ያረደ ኡድሒያን አላገኘም፡፡ እርዱም ለራሱ ብሎ እንዳረደው እርድ ይሆንበታል፡፡ በዚህም ምንም አይነት ምንዳ አይመነዳም፡፡ እርዱን ከአዲስ ሌላ ኡድሒያ ማድረግ ይኖርበታል፡፡

ከዚህም በተለየ ማሊኪያዎች እርድ የሚባለው ተቀባይነት እንዲኖረው በሌላ መስፈርት አጣምረውታል፡፡ እሱም ኢማም ከማረዱ በሗላ ማረድ አለበት፡፡ ለዚህም ንግግራቸው ያቀረቡት ሐዲስ ሲሆን ፦ ጃቢር እንዲህ ይላል መልእክተኛው መዲና ላይ የእርዱ ቀን አሰግደውን ሲያበቁ ፤ መልእክተኛው አርደው የጨረሱ መስሏቸው፤ ሰዎች ለእርድ ተሸቀዳድመው
እርዳቸውን አረዱ፡፡ መልእክተኛውም ከሳቸው በፊት እርድ ያረደን ሌላ እንዲያርድ አዘዙ፡፡ ስለዚህም መልእክተኛው ሳያርዱ አያርዱም ነበር፡፡[ሙስሊም ዘግቦታል].
ነገር ግን ይህ ማሊኪያዎች የጠቀሱትን ማስረጃ አንዳንድ ኡለማዎች በመልእክተኛው ብቻ የተገደበ ነው ሲሉ መልስ ሰጥተዋል፡፡
ኢማሙ አሽሻፊዒይ ይህ ከላይ ያለፈው ንግግር ከጊዜ ጋር የተቆራኘ (የተገደበ) እንደሆነ እንዲህ ሲሉ ተናግረዋል፦ የአድሀ ወቅት ኢማሙ ለሶላት እስከሚገባበት ልክ ነው፡፡ ይህ ማለት ፀሀይቷ ብርሀናማ ስትሆን፤ ሁለት ረከዐን ይሰግድና ሁለት አጠር ያሉ ኹጥባዎችን ያደርጋል፡፡ በዚሁ በቀኑ ክፍል አጠናቆ ሲሄድ እርዱም ይፈቀዳል፡፡ [መዓሊም አስሱነን 234/2].
ስለ ማብቂያው(ማገባደጃው) መቼ ነው ለሚለው ሀዲስ የገለፀው ሲሆን እሱም፦
ሁሉም አያመ አትተሽሪቅ(ከእርዱ ቀን አንስቶ እስከ ዙል ሂጃ 13 ፀሀይ መጥለቂያ)እርድ አለ የሚለው ነው፡፡

በነውሩ ምክንያት ለኡድሒያ ማይበቁ እንስሣት
በራእ ኢብን ዓዚብ የአሏህ መልእክተኛ እንዲህ አሉ፦ አራት አይነቶች ለኡድሒያ አይበቁም 1.እውርነቷ ግልፅ የሆነ እውር 2.በሽተኛ በሽታኝነቷ ግልፅ የሆነ 3. አንካሳ ስብራቷ ግልፅ የሆነ 4. ስጋ የሌላት ከሲታ የሆነች፡፡[አቡ ዳውድ እና ቲርሚዚይ ሶሂህ ብለው ዘግበውታል].
ዓሊ አሏህ መልካም ስራውን ይውደድለትና እንዲህ ይላል፦ መልእክተኛው አይንንና ጆሮን እንድንመለከት አዘውናል፡፡ ጆሮ የተቆረጠ፣ ጆሮ ላይ ቀዳዳ ያለበትና የጆሮ ጫፍ ወይም ጥግ ላይ እንከን ያለበትን ለኡድሒያ እንዳናደርግ ከልክለውናል፡፡ [አቢዳውድ፣ ነሣዒ፣ ትርሚዚይና ኢብን ማጀሕ ሶሂህ ብለው ዘግበውታል].
እነዚህ ሀዲሶች እንደሚያመላክቱት ከሆነ ጆሮ ላይ እንከን መኖር፣ግልፅ የሆነ ስብራት(አንካሳ)፣ ግልፅ የሆነ ከሲታነት፣ ግልፅ የሆነ እውርነትና ግልፅ የሆነ በሽታ እነዚህ ለኡድሒያ በቂ ያልሆኑ መሆናቸው ነው፡፡
በሽታው ወይም ስብራቱና መሰል እንከኖቹ ትንሽና ግልፅ ያልሆኑ ከሆኑ ኡድሒያ ለማድረግ በቂ ይሆናሉ፡፡ ለምን ከተባለ ሀዲሱ ላይ "ግልፅ የሆነ" በሚል ተጣምሯልና፡፡
እንደ እውርነትና ስብራት ከነዚህ በተጠቀሱት እንከኖችና ከነሡ የበለጡ እንከኖች ከተገኙ ኡድሒያን በነዚህ ማድረግ አይበቃም፡፡[ነይሉል አውጣር 206/5].
ለኡድሒያ ግዢ ጥሩውን መምረጥ ይወደዳል፡፡ከላይ ሀዲሱ ላይ እንዳሣለፍነው "አይንና ጆሮን እንድንመለከት ታዘናል" እንዚሁ በሌላ ሀዲስ አቢ ኡማማ እንዲህ ይላል " ለኡድሒያ ብለን መዲና ላይ እንስሳቶችን እናደልብ ነበር፡፡ሙስሊሞችም ያደልቡ ነበር፡፡"[ቡኻሪይ በተእሊቅ ዘግቦታል9/10].
ኡድሒያው ላይ ያለፋብን ሀዲሶች ላይ ከተጠቀሱት እንከኖች ውጪ ከተገኘባቸው ለኡድሂያ መቅረብ ይችላሉ ኡድሒያውም በቂ ነው፡፡ በላጩ ከየትኛውም ጉድለት የጠራው ከመሆኑም ጋር፡፡ ስለዚህ ቀንዱ ሙሉውን ወይም ከፊሉን የተሠበረ፣ ጥርሱ የተሠበረ፣ጭራው የተቆረጠና ሌሎች ኡድሒያው በቂ ከመሆን ምንም ተፅዕኖ የላቸውም፡፡ ለምን ከተባለ እነዚህን አስመልክቶ (ኡድሒያ በነዚህ አይበቃም) ብለው የተዘገቡት ሀዲሶች ደካማ(ውድቅ) ናቸው፡፡ [ሙሓላ 9-13/8].

ለአንድ ሠው የሚያብቃቃው የኡድሒያ አደራረግ
ለአንድ ሰው እና ለቤተሠቡ አንድ በግ ያብቃቃዋል፡፡ ከብት(ላም/በሬ)እና ግመል ለሠባት(ከነቤተሰቦቻቸው)፡፡ ስለዚህ ለሰባቶቹ ከብትን ወይም ግመልን ለሰባት ሆነው ይካፈላሉ ማለት ነው፡፡ አጧዕ ኢብን የሣር አቢ አዩብ አል አንሷሪይን በመልእክተኛው ዘመን እርዳቹህ እንዴት ነበር ስል ጠየቁኩት? እርሱም እንዲህ አለ፦ "አንድ ሠው በመልእክተኛው ዘመን አንድ ሠው ለራሱና ለቤተሠቡ አንድ በግን ያርዱና ይመጋባሉም ይመግባሉ፡፡[ሶሂህ ቲርሚዚይ ዘግቦታል]. ስለ ከብትና ስለ ግመል ማስረጃው ጃቢር ባወራው ሀዲስ እንዲህ ይላል፦ "መልእክተኛው በግመል ወይም በበሬ(ከብት) ሰባት ሆነን እንድንካፈል አዘውናል፡፡[ሙስሊም ]
@alfiqhulmuyser
766 viewsedited  05:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 18:21:10
የበጎችን እድሜ ለይቶ ለማወቅ የሚረዳ ምስል ነው፡፡ ትንሹ(ጀዘዕ) የሚባለው፦ ጥርሶቹ አጠር ብለው እኩኩል ደረጃ ላይ ያሉ ሆነው ክፍተትና ንፃት ያላቸው ናቸው፡፡ይህ እድሜው ስምንት ወር የሞላው ነው፡፡
(ሰንያ) የሚባለው የመሀል ሁለቱ ጥርሶቹ ከሌላው በተለየ መልኩ ረዘም ያሉ ናቸው፡፡ እድሜውም ከ1-2 አመት የሆነው ነው፡፡
(ሩባዕ)የሚባለው የፊተኛው አራቱ ጥርሶቹ በከፍታ እኩኩል የሆኑ ሲሆን እድሜውም ከ2-2.5 የሞላው ነው፡፡
(ሱዱስ)የሚባለው ስድስቱም ጥርሶቹ በከፍታ እኩኩል የሆኑ ሲሆን እድሜውም 3አመት የሞላው ነው፡፡ እንዚህ አገላለፆች ግን በማቀራረብ ነው፡፡
https://telegram.me/alfiqhulmuyser
775 views15:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 06:12:54 ለኡድሒያ የሚበቃው እንሠሣ ተቀባይነት ያለው የእድሜ ገደብ፦
ጃቢር አሏህ መልካም ስራውን ይውደድለትና ባወራው ሀዲስ መልእክተኛው እንዲህ ብለዋል፦ "እድሜያቸው መካከለኛ(የደረሱ)
/ከግመል፣ላም፣በሬ፣ፍየል/የሆነቱን እንጂ እንዳታርዱ፡፡ ነገር ግን እናንተ ላይ ጫና የሚያመጣ ከሆነ ከበግ(ትንሿን) እረዱ፡፡[ሙስሊም ዘግበውታል ]
ይህ ሀዲስ ለኡድሒያ እድሜ መስፈርት እንደሆነ ከሚያመላክቱ ሀዲሶች አንዱ መሆኑ ነው፡፡
ከግመል አምስ አመት፣ከከብት(ከላም/ላም) ሁለት አመት፣ ከፍየል አንድ አመት የሆናቸው፡፡[ሸርህ ሙምቲዕ 460/7].

በበግ የእድሜ ላይ ግን ልዩነት ያመጡ ሲሆን፤ ከፊሎቹ አመት የሞላት ፣ ስድስት ወር ፣ ስምንት ወር ብለው ጠቅሰዋል፡፡ [ነይሉል አውጣር 302/5].

ከላይ ያሣለፍነው የጃቢር ሀዲስን ይዘው፤ የሀዲሱንም ውጫዊ ገለፃውን በመያዝ ከኢብን ኡመርና ከዙህሪይ በበግ(ትንሹን) አይበቃም ብለዋል፡፡
ኢማም አንነወዊይ እንዲህ ይላል፦ ለኡድሒያ እርድ ከበግ(ትንሹ)ን ማረድ ፤ከሱ ውጪ ሌላ ተገኝቶም ይሁን ሳይገኝ ለእርድ እንደሚበቃ ከእውቀት ባለቤቶች የአጠቃላዮቹ ምርጫ ነው፡፡ይህንን ሀዲስንም ከበግ(ትንሹ) ውጪ ማረድ የተወደደ መሆኑን ነው የገለፁት፡፡ ሀዲሱ ላይ ግልፅ የሆነ ክልከላ የለም ፡፡ የሀዲሱንም ውጫዊ ገለፆ እንደማንይዝ ሁሉም የተስማማበት ነው፡፡
[ፈትሁል ባሪ ላይ ኢብን ሀጀር ይህን ንግግር አጠንክሮታል 15/10].

የእርዱ ጊዜ

አነስ አሏህ መልካም ስራውን ይውደድለትና የአሏህ መልእክተኛ የእርዱ ቀን እንዲህ አሉ፦ ከሶላት በፊት ያረደ አንደገና ይረድ፡፡ በሌላ ዘገባም፦ ከሶላት በፊት ያረደ፤ ያረደው ለራሱ ነው፡፡ ከሶላት በሗላ ያረደ በእርግጥም እርዱን አሟልቷል፡፡የሙስሊምችንም መንገድ ገጥሞል(አግኝቷል)፡፡[ቡኻሪና ሙስሊም].
ይህ ሀዲስ እንደሚያመላክተው ከሆነ የመጀመሪያው የእርድ ጊዜ ከሶላተል ኢድ በሗላ እንደሆነ ነው፡፡ ነገር ግን ከሶላት በፊት ያረደ ኡድሒያን አላገኘም፡፡ እርዱም ለራሱ ብሎ እንዳረደው እርድ ይሆንበታል፡፡ በዚህም ምንም አይነት ምንዳ አይመነዳም፡፡ እርዱን ከአዲስ ሌላ ኡድሒያ ማድረግ ይኖርበታል፡፡

ከዚህም በተለየ ማሊኪያዎች እርድ የሚባለው ተቀባይነት እንዲኖረው በሌላ መስፈርት አጣምረውታል፡፡ እሱም ኢማም ከማረዱ በሗላ ማረድ አለበት፡፡ ለዚህም ንግግራቸው ያቀረቡት ሐዲስ ሲሆን ፦ ጃቢር እንዲህ ይላል መልእክተኛው መዲና ላይ የእርዱ ቀን አሰግደውን ሲያበቁ ፤ መልእክተኛው አርደው የጨረሱ መስሏቸው፤ ሰዎች ለእርድ ተሸቀዳድመው
እርዳቸውን አረዱ፡፡ መልእክተኛውም ከሳቸው በፊት እርድ ያረደን ሌላ እንዲያርድ አዘዙ፡፡ ስለዚህም መልእክተኛው ሳያርዱ አያርዱም ነበር፡፡[ሙስሊም ዘግቦታል].
ነገር ግን ይህ ማሊኪያዎች የጠቀሱትን ማስረጃ አንዳንድ ኡለማዎች በመልእክተኛው ብቻ የተገደበ ነው ሲሉ መልስ ሰጥተዋል፡፡
ኢማሙ አሽሻፊዒይ ይህ ከላይ ያለፈው ንግግር ከጊዜ ጋር የተቆራኘ (የተገደበ) እንደሆነ እንዲህ ሲሉ ተናግረዋል፦ የአድሀ ወቅት ኢማሙ ለሶላት እስከሚገባበት ልክ ነው፡፡ ይህ ማለት ፀሀይቷ ብርሀናማ ስትሆን፤ ሁለት ረከዐን ይሰግድና ሁለት አጠር ያሉ ኹጥባዎችን ያደርጋል፡፡ በዚሁ በቀኑ ክፍል አጠናቆ ሲሄድ እርዱም ይፈቀዳል፡፡ [መዓሊም አስሱነን 234/2].
ስለ ማብቂያው(ማገባደጃው) መቼ ነው ለሚለው ሀዲስ የገለፀው ሲሆን እሱም፦
ሁሉም አያመ አትተሽሪቅ(ከእርዱ ቀን አንስቶ እስከ ዙል ሂጃ 13 ፀሀይ መጥለቂያ)እርድ አለ የሚለው ነው፡፡

በነውሩ ምክንያት ለኡድሒያ ማይበቁ እንስሣት
በራእ ኢብን ዓዚብ የአሏህ መልእክተኛ እንዲህ አሉ፦ አራት አይነቶች ለኡድሒያ አይበቁም 1.እውርነቷ ግልፅ የሆነ እውር 2.በሽተኛ በሽታኝነቷ ግልፅ የሆነ 3. አንካሳ ስብራቷ ግልፅ የሆነ 4. ስጋ የሌላት ከሲታ የሆነች፡፡[አቡ ዳውድ እና ቲርሚዚይ ሶሂህ ብለው ዘግበውታል].
ዓሊ አሏህ መልካም ስራውን ይውደድለትና እንዲህ ይላል፦ መልእክተኛው አይንንና ጆሮን እንድንመለከት አዘውናል፡፡ ጆሮ የተቆረጠ፣ ጆሮ ላይ ቀዳዳ ያለበትና የጆሮ ጫፍ ወይም ጥግ ላይ እንከን ያለበትን ለኡድሒያ እንዳናደርግ ከልክለውናል፡፡ [አቢዳውድ፣ ነሣዒ፣ ትርሚዚይና ኢብን ማጀሕ ሶሂህ ብለው ዘግበውታል].
እነዚህ ሀዲሶች እንደሚያመላክቱት ከሆነ ጆሮ ላይ እንከን መኖር፣ግልፅ የሆነ ስብራት(አንካሳ)፣ ግልፅ የሆነ ከሲታነት፣ ግልፅ የሆነ እውርነትና ግልፅ የሆነ በሽታ እነዚህ ለኡድሒያ በቂ ያልሆኑ መሆናቸው ነው፡፡
በሽታው ወይም ስብራቱና መሰል እንከኖቹ ትንሽና ግልፅ ያልሆኑ ከሆኑ ኡድሒያ ለማድረግ በቂ ይሆናሉ፡፡ ለምን ከተባለ ሀዲሱ ላይ "ግልፅ የሆነ" በሚል ተጣምሯልና፡፡
እንደ እውርነትና ስብራት ከነዚህ በተጠቀሱት እንከኖችና ከነሡ የበለጡ እንከኖች ከተገኙ ኡድሒያን በነዚህ ማድረግ አይበቃም፡፡[ነይሉል አውጣር 206/5].
ለኡድሒያ ግዢ ጥሩውን መምረጥ ይወደዳል፡፡ከላይ ሀዲሱ ላይ እንዳሣለፍነው "አይንና ጆሮን እንድንመለከት ታዘናል" እንዚሁ በሌላ ሀዲስ አቢ ኡማማ እንዲህ ይላል " ለኡድሒያ ብለን መዲና ላይ እንስሳቶችን እናደልብ ነበር፡፡ሙስሊሞችም ያደልቡ ነበር፡፡"[ቡኻሪይ በተእሊቅ ዘግቦታል9/10].
ኡድሒያው ላይ ያለፋብን ሀዲሶች ላይ ከተጠቀሱት እንከኖች ውጪ ከተገኘባቸው ለኡድሂያ መቅረብ ይችላሉ ኡድሒያውም በቂ ነው፡፡ በላጩ ከየትኛውም ጉድለት የጠራው ከመሆኑም ጋር፡፡ ስለዚህ ቀንዱ ሙሉውን ወይም ከፊሉን የተሠበረ፣ ጥርሱ የተሠበረ፣ጭራው የተቆረጠና ሌሎች ኡድሒያው በቂ ከመሆን ምንም ተፅዕኖ የላቸውም፡፡ ለምን ከተባለ እነዚህን አስመልክቶ (ኡድሒያ በነዚህ አይበቃም) ብለው የተዘገቡት ሀዲሶች ደካማ(ውድቅ) ናቸው፡፡ [ሙሓላ 9-13/8].

ለአንድ ሠው የሚያብቃቃው የኡድሒያ አደራረግ
ለአንድ ሰው እና ለቤተሠቡ አንድ በግ ያብቃቃዋል፡፡ ከብት(ላም/በሬ)እና ግመል ለሠባት(ከነቤተሰቦቻቸው)፡፡ ስለዚህ ለሰባቶቹ ከብትን ወይም ግመልን ለሰባት ሆነው ይካፈላሉ ማለት ነው፡፡ አጧዕ ኢብን የሣር አቢ አዩብ አል አንሷሪይን በመልእክተኛው ዘመን እርዳቹህ እንዴት ነበር ስል ጠየቁኩት? እርሱም እንዲህ አለ፦ "አንድ ሠው በመልእክተኛው ዘመን አንድ ሠው ለራሱና ለቤተሠቡ አንድ በግን ያርዱና ይመጋባሉም ይመግባሉ፡፡[ሶሂህ ቲርሚዚይ ዘግቦታል]. ስለ ከብትና ስለ ግመል ማስረጃው ጃቢር ባወራው ሀዲስ እንዲህ ይላል፦ "መልእክተኛው በግመል ወይም በበሬ(ከብት) ሰባት ሆነን እንድንካፈል አዘውናል፡፡[ሙስሊም ዘግበውታል].

https://t.me/alfiqhulmuyser
527 views03:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ