Get Mystery Box with random crypto!

ኤልሮኢ: ስለ ሰይጣን ከተተረኩት ለቅምሻ ሰዎች ርኩስ መንፈስ ያደረበትን ሰው ወደ አንድ ገዳም | "ኤልሮኢ ዘተዋህዶ"

ኤልሮኢ:
ስለ ሰይጣን ከተተረኩት ለቅምሻ

ሰዎች ርኩስ መንፈስ ያደረበትን ሰው ወደ አንድ ገዳም ይዘው መጡና ያድንላቸው ዘንድ
ለገዳሙ አበምኔት(አለቃ) ሰጡት። የገዳሙ አበምኔትም በተሰጠው ፀጋ ተጠቅሞ በስመ
እግዚአብሔር ሰይጣኑን ውጣ ሲለው ሰይጣኑም «መውጣቱንስ እወጣለሁ ግን አንድ ጥያቄ
ነበረኝ»ይላል።
የገዳሙ አበምኔትም «ምንድነው ጥያቄህ?» ይለዋል። ሰይጣኑም በወንጌል ላይ ፍየሎች
በግራ በጎች በቀኝ ይቆማሉ የሚል ቃል አለ፣ ለመሆኑ በፍየልና በበግ የተመሰሉት እነማን
ናቸው? ይኽንን በምሳሌ አድርገህ ንገረኝ አለው። የሰይጣኑ አመጣጥ የገባው ያ ደግ አባትም እንዲህ መለሰ። «በፍየል የተመሰሉት ኃጥአን፣ በበግ የተመሰሉት ደግሞ ፃድቃን ናቸው። በምሳሌ ንገረኝ ላልከው፣ በፍየል ከተመሰሉት ኃጥአን መካከል ለምሳሌ አንዱ እኔ ነኝ። በበግ የተመሠሉ ፃድቃንን ግን አላውቅም። አሁን ግን ውጣ» አለው። ተንኮሉ
የተነቃበትና ያጠመደው ውዳሴ ከንቱ መረብ ያልያዘለት ሰይጣንም በኃይል ጮኾ ከሰውየው
ወጣ። በሽተኛውም ዳነ፡፡

@aleroe