Get Mystery Box with random crypto!

ኤልሮኢ:(ስነፅሁፍ) በዜሮ ይባዛል! ፆም×0=0 ስግደት×0=0 ጸሎት ×0=0 ተግ | "ኤልሮኢ ዘተዋህዶ"

ኤልሮኢ:(ስነፅሁፍ)
በዜሮ ይባዛል!

ፆም×0=0 ስግደት×0=0
ጸሎት ×0=0


ተግቼ ብጸልይ እጆቼን ዘርግቼ
ቤቴ ባዶ ቢቀር ያለኝን መጽውቼ
ቀኑን ሙሉ ብጾም እስኪቆረጥ አንጀቴ
ዘወትር ብሰግድ እስኪዝል ጉልበቴ
በቀድስ ባስቀድስ በመቅደሱ ግርማ
ብዘምር ባወድስ የሚጣፍጥ ዜማ
ወንጌልን ብሰብክ ምስጢር አመስጥሬ
ብናገር ባስተምር ትርጉሙን ዘርዝሬ
ጥልና ክርክር ካሉ በህይወቴ
ሐሜት ክርክር ካልጠፉ ከቤቴ
በዜሮ ይባዛል ፍቅር በማጣቴ።

ስብሐት ለእግዚአብሔር!

ፆም×ፍቅር= 30 ያማር ፍሬ
ጸሎት×ፍቅር= 60ያማር ፍሬ
ስግደት× ትህትና= 100ያማረ ፍሬ

@aleroe