Get Mystery Box with random crypto!

ረመዷን ሊገባ ቀናቶች ቀርተውታል፤ ያለፈው ረመዷን ቀዷእ ያለብዎ ከሆነ ከወዲሁ ፆመው ያካክሱ። | Ahmedin Jebel - አሕመዲን ጀበል

ረመዷን ሊገባ ቀናቶች ቀርተውታል፤ ያለፈው ረመዷን ቀዷእ ያለብዎ ከሆነ ከወዲሁ ፆመው ያካክሱ።


አላህ ስራቸውን ይውደድላቸውና አቢ ሰለማ እንዳሉት እናታችን ዓኢሻ ረዲየ አላሁ ዓንሀ “ከረመዳን ወር ፆም ቀሪ ይኖርብኝና በሻዕባን ወር ካልሆነ በስተቀር ፆሜ ማካካስ አልችልም ነበር።" ትላለች ብለዋል። (ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።)

አል-ሃፊዝ ኢብኑ ሀጀር አላህ ይዘንላቸውና በዚህ ሀዲስ ላይ ተመርኩዘው በፈትሁል-ባሪ (4/191) ላይ እንዳሰፈሩት

«እናታችን ዓኢሻ (ረዲየ አላሁ ዓንሀ) በሻዕባን ወር የረመዳንን ፆም "ቀዷእ" ለማውጣት ጥረት በማድረጓ ከዚህ የምንገነዘበው ነገር የረመዳንን ወር ፆም "ቀዷእ" ሌላኛው ረመዳን እስኪገባ ድረስ ማዘግየት የማይቻል መሆኑን ነው።» ብለዋል።

ስለዚህ እህትና ወንድሞች ከፊትለፊታችን ያሉት ጥቂት ቀናት ናቸውና ያልተፆመ እዳ ካለብዎት ፈጠን ብለው ይክፈሉና ለቀጣዩ ይዘጋጁ። አላህ ይወፍቀን።