Get Mystery Box with random crypto!

#አሐዱ_መንፈሳዊ_መዝሙር_ቤት

የቴሌግራም ቻናል አርማ ahduuuu — #አሐዱ_መንፈሳዊ_መዝሙር_ቤት
የቴሌግራም ቻናል አርማ ahduuuu — #አሐዱ_መንፈሳዊ_መዝሙር_ቤት
የሰርጥ አድራሻ: @ahduuuu
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 171
የሰርጥ መግለጫ

ፈረንሳይ ለጋሲዮን አደባባይ ወደ አቦ ቤተክርስቲያን በሚወስደው መንገድ ያገኙናል፡፡ ለበለጠ መረጃ 0949111436

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

3

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-06-11 11:09:19 ልዩ የቅዳሜናእሁድ የጥቅል ቅናሽ
#አሐዱ_መንፈሳዊ_መዝሙር_ቤት ከሰኔ 04 እስከ ሰኔ 05/ 2014 ዓ.ም. የሚቆይ ልዩ የጥቅል ግዢ አዘጋጅቷል። በዚሁ መሠረት፦
#የሀገር_ባለውለታዎች

#በኢትዮጵያ_ቤተክርስቲያን_የመጀመሪያው_ፓትሪያርክ

#እነኀት_ክርስትና

የሽፋን ዋጋቸው ተደምረው #550 ብር የኾኑትን
በብር #405 ብቻ

#ገድለ_ሰማዕታት

#ገድለ_አቡነ_አብርሃም_ወሣራ

#ድርሳነ_ማርያም

የሽፋን ዋጋቸው ተደምረው #1,100 ብር የኾኑትን
በብር #850 ብቻ
#ምስካ_በጾታ

#ሥነ_ምግባር

#ደቂቀ_ነብያት

የሽፋን ዋጋቸው ተደምረው #330 ብር የኾኑትን
በብር #250

ቅናሽ አድርገናል።
-------------

ለተጨማሪ መረጃ 094911143
እንዲሁም @jerusalemle ላይ ያናግሩን።

@ahduuuu ብለው የቴሌግራም ቻናላችን ላይ ቤተሰብ ይሁኑ እንዲሁም ለወዳጆቾ share በማድረግ ይጋብዙ::
87 viewsedited  08:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-11 11:09:14
81 views08:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-10 09:48:04
… በመንገዳችን ላይ በኃጢአት ሥራዋ በሁሉ ዘንድ የምትታወቅ የአንዲት ሴት ቤት ነበር፡፡ በዚያ ስናልፍ በሁኔታው የተከበረ ሰው የሚመስል በደጃፏ ተቀምጦ አምርሮ ሲያዝን ቅዱሱ ተመለከተ፡፡ በሁለት እጆቹ ፊቱን ሸፍኖ ያለቅሳል፡፡ ትንሽ ቆይቶ ደግሞ ዓይኖቹን ወደ ሰማይ አቅንቶ ይጸልይና መልሶ ደግሞ አምርሮ ያለቅሳል፡፡

ኒፎን ሁኔታው ልቡን ነክቶት ማልቀስ ጀመረ፡፡ ወደ ተከበረው ሰውም ቀርቦ “ወንድሜ ሆይ! በዚህ ውርደት በተሞላ ሥፍራ ተቀምጠህ በምሬት የምታለቅስ ስለ ምን ነው? ኀዘንህ ልቤን ሰብሮታል፤ እባክህ ስለ እግዚአብሔር ብለህ የሆንከውን ንገረኝ?” ሲል ለመነው፡፡

“የተወደድከው ኒፎን! ከአንተ እንደማይሠወረው እኔ የእግዚአብሔር መልአክ ነኝ፡፡ ክርስቲያን ሁሉ ጥምቀተ ክርስትናን በተቀበለበት ዕለት አንድ ጠባቂ መልአክ ይሰጠዋል፡፡ እኔም አንድ ሰውን እንድጠብቅ ኃላፊነት ተሰጥቶኛል፡፡ ነገር ግን ኃጢአትን አዘውትሮ በመሥራት አስመርሮኛል፡፡ አሁንም እንኳ በዚህ በረከሰ ቤት ከአንዲት ሴት ጋር በዝሙት ራሱን ያጎሰቁላል፡፡ በእግዚአብሔር አርአያና አምሳል የተፈጠረ እንዲህ ያለርኵሰትና የጨለማ ሥራ ተውጦ እየተመለከትሁ አለማልቀስ እንዴት ይቻለኛል?”

“ለምን ከኃጢአት ሥራ እንዲርቅ አታስጠነቅቀውም?” ሲል ኒፎን ጠየቀው፡፡

“እንዳለመታደል ሆኖ አሁን…
____
ከራእየ ኒፎን መጽሐፍ የተቆነጠረ፣
------------------
መጽሐፋ ዋጋ፡ 130 ብር

መጽሐፉን፡ #በአሐዱ_መንፈሳዊ_መዝሙር ቤት ያገኙታል፡፡
91 views06:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-21 12:07:49
129 views09:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-05 07:34:49
"ለሚጠይቋችሁ ሁሉ ዘወትር መልስ ለመስጠት የተዘጋጃችሁ ሁኑ"1ኛ ጴጥ 3÷15
ሚያዚያ 1 የሚጀምር ተከታታይ መንፈሳዊ ትምህርት ትምህርቱ የሚሰጠው ቅዳሜ እና እሁድ ከ10:00-12:00
እንዲሁም ማክሰኞ ሀሙስ ቅዳሜ ከ12:00-1:30በመሰጠት ላይ ይገኛል መማር የምትፈልጉ ዘወትር በሰ/ት/ቤቱ አዳራሽ 12:00-2:00 ወይም ቅዳሜ እና እሁድ ከቅዳሴ በኋላ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን ።
በተጨማሪ በስልክ ቁጥር
0934147347
0931796533
በ telegram
@Mes_0417
@Dzrbetsi
መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
መካነሕይወት ሰ/ት/ቤት
ትምህርት እና ስልጠና ክፍል
243 views04:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-31 20:18:32
መጽሐፈ ምንኃር የመጻሕፍት ምንጭ

ዲ.ን የሺበላይ በላቸው

"ምንኃር" ከገነት መነሻቸውን ያደረጉ ዐራቱ አፍላጋተ ወንዞች መነሻ ቦታቸው ገነት ምንኃር ከተባለ ምንጭ ነው። ያ ቦታ ወንዞች ወደዐራት ቦታ ሳይከፋፈሉ አስቀድሞ አንድ ሆነው የሚፈልቁበት ቦታ ምንኃር ይባላል።

ዐራቱ አፍላጋት ማን ማን ናቸው ቢሉ:-
አንደኛው ኤፍራጥስ የሚባለው ወንዝ ዘይት ነው።
ሁለተኛው ኤፌሶን የሚባለው ወንዝ ሲሆን እሱም ወተት ነው።
ሦስተኛው ጤግሮስ የሚባለው ወንዝ ማር ነው።
ዐራተኛው ግዮን እርሱም አባይ ነው የኢትዮጵያ ደም ሥሯ ማለት ነው።

እነዚህ ዓለምን የሚያጠጡ ዐራቱ ወንዞች መነሻቸው አንድ ምንጭ ነው እርሱም ምንኃር ይባላል።

ይህም መጽሐፍ በባቢሎን ግንብ በሰው ልጆች ኃጢአት ምክንያት የሰው ልጆች ቋንቋ ከመደበላለቁ አስቀድሞ ለሰው ልጅ ሁሉ ከሰማይ የተሰጠጸጋ ግዕዝ ቋንቋን የሚያብራራ የሚያመሠጥር ቀመረ ፊደልን የሚያሳይ አቡሻክርን የጠነቀቀ የጠፋ ማንነታችንን ከሥሩ ከምጩ የተቆመ ምንጭ በመሆኑ መጽሐፈ ምንኃር ተብሏል።

አንድም ከገነት ምንጭ ጥርት ያለ ምንም የሌለበት ንጹሕ ውኃ ይፍልቃል። እመቤታችንም “ነቅዓ ፈልፈለ ማየ ሕይወት - የሕይወት ውኃ ምንጭ” ናት(ውዳሴ ማርያም)፤ አማናዊ የሕይወት ውኃ ጌታችንን አስገኝታልናለችና።

በገነት ዐራቱ አፍላጋት ይወጣሉ፣ ገነትን ያጠጡና ወደዐራቱ አቅጣጫ ይፈሳሉ። እመቤታችንም “ፈልፈለ ማየ ሕይወት ዘይውሕዝ እምከርሱ - የሕይወት ውኃ ከሆዱ ይፈልቃል” ተብሎ የተነገረለት አማኑኤልን አስገኘች። ስለዚህ ይህም መጽሐፍ ማንነታችንን የምናገኝበት ከፍታችንን የምንወጥንበት ወደምንጫችን የምንመለስበት ኢትዮጵያዊነት ልዕልናችንን የምናገኝበት የዕውቀት ትንሣኤ የያዘ አብሣሬ ርግብ የሆነ መጽሐፍ ነው።

እውነትም መጽሐፈ ምንኃር ይነብብ ይነብብ ይነብብ ይነብብ እላለሁ።
186 viewsedited  17:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-04 13:18:47 https://t.me/kemariyam
184 views10:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-25 12:39:56
246 views09:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-03 12:05:38
"በበረት ተኛ በጨርቅም ተጠቀለለ"
እንኳን ለጌታችን ለመድሀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሳችሁ እያለ ሰ/ት/ቤታችን ለልደት በዓል የሚሆን በረት አዘጋጅቷል በአንዳንዶቻችን ቤት ልማድ ያረግነው ነገር ግን መቅረት ያለበት የገና ዛፉ በእምነታችንም ሆነ ባህላችን እኛን የማይወክል ነውና በእምነታችን መሰረት ቤተክርስቲያናችንም እንደምታስተምረን ሰ/ት/ቤታች በረት አዘጋጅቶ አቅርቧል ስለዚህም የምንችል ሁላችንም በረቱን እድንገዛ እና አገልግሎቱንም እንድንደግፍ የሰ/ት/ቤታችን ልማት እና በጎ አድራጎት ክፍል ጥሪውን ያስተላልፋል።
በረቶቹን በ አሐዱ መንፈሳዊ መዝሙር ቤት ያገኛሉ
መልካም በዓል!!!
470 viewsedited  09:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-13 15:09:25 በስመአብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን !!!
"የተሰጣችሁን የተስፋ ቃል እንድታገኙ መፅናት
ያስፈልጋችኋል"ዕብ 10÷36
ታላቅ የምስራች
የመካነ ሕይወት አቡነ ገብረ መንፈስቅዱስ ቤ/ክ ሰ/ት/ቤት
ከተለይዮ ት/ቤቶች የተውጣጡ የክፍል ደረጃቸው ከ9-12 የሆኑ ተማሪዎችን በጊቢ ጉባኤ መርሐግብር ያስተምር እንደነበር ይታወቃል።
በዚህም ዓመት ጉባኤውን አጠናክሮ ለመጀመር ዝግጅቱን አጠናቆ ተማሪዎችን በመጠባበቅ ላይ ይገኛል ስለዚህም በፈረንሳይ እና አካባቢው የምትገኙ የክፍል ደረጃችሁ ከ9-12 የሆነ በዚህ ጉባኤ ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ
በስልክ ቁጥር ¤0912383379
¤ 0934147347
መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን። ትምህቱ ዘወትር እሁድ ከቀኑ 10:00-11:00 ይሰጣል።
የሚጀመርበት ቀን ታህሳስ 10/2014ዓ.ም
አዘጋጅ የመካነ ሕይወት ሰ/ት/ቤት ከማህበረ ቅዱሳን ጋር በጋራ በመሆን።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
አምላከ ገብረ መንፈስቅዱስ አገልግሎታችንን ይባርክ!!!
291 views12:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ