2022-08-30 10:34:45
ማር ለጸጉር ውበትና እድገት
ማር ለምግብነት፤ ለቆዳ ህመሞች አልፎም ለውበት ጥቅም ላይ የሚውል እንድ ስሙ ጣፋጭ የተፈጥሮ ስጦታ ነው፡፡ ማር በተለምዶው ጸጉርን ያሸብታል፤ ያከረድዳል ሲባል ይሰማል፡፡ ይህ ፈጽሞ ከእውነት የራቀ ወይም አጠቃቀምን ባግባቡ ካለመለየት የሚመጣ ነው፡፡
ማር በተፈጥሮው የ ኢሞለንትና ሆሜክታንት (emollient and humectant) ባህሪያት አሉት እነዚህም በዋነኝነት ጸጉርን ለማለስለስ የሚጠቅሙ ናቸው፡፡ ማር ከውሃ ሞሎክዩሎች ጋር በመጣመር የደረቀ ጸጉርን በማለስለስ ጸጉርን አንጸባቂ ያደርጋል፡፡
ማር ራሱን ችሎ የጸጉር ትሪትመንት ሆኖ ማገልገል ይችላል፡፡ የጸጉር ቆዳን ሴሎች እድገትን ያፋጥናል፤ ድርቀትን ይከላከላል፤ ጠቃሚ የሆኑ ንጥረ ነገሮችን ቆዳ ላይ ያቆያል፤ ቆዳ መቆጣቶችንና ተያያዥ ችግሮችን ለመፍታት ይጥቅማሉ፡፡
ማር በአንቲዞክሲዳንቶች በመበልጸጉ የጸጉርን መርገፍና መበጣጠስ ይከላከላል ይህም ጸጉርን ለማጠንከርና ጤናማ ለማድረግ ይጠቅማል፡፡ ጸረ ባክቴሪያም ስለሆነም የቆዳ ኢንፌክሽኖችን በመከላከል ማሳከክን ይክላከላል አልፎም የቀሉ፤ ያበጡ፤ የተጫጫሩ ጸጉሮችንም ያክማል፡፡
የጸጉር በማፍታታት በማበጠር ጊዜ የሚኖሩ የጸጉር መርገፎችን ይከላከላል፡፡ የሞቱ የጸጉር ቆዳዎችንም እንዳዲስ እንዲነሳሱ በማድረግ የጸጉር እድገትን የተስተካከለና የተፋጠነ ያደርጋል፡፡
ማርን ከተለያዩ ውህዶች ጋር ቀላቅሎ መጠቀም የሚቻል ሲሆን የተሻለ ለውጥን ለማየትም የካካዎ ወተትንና እርጎን ቀላቅሎ መጠቀም የተሻለ ለውጥን ለማየት ያስችላል፡፡ ማርን ከጸጉር ላይ ከ 15 እስክ 20 ደቂቃ ያህል በማቆየት ጸጉርን ማከም/ ትሪት ማድረግ ይቻላል፡፡
ለሚረግፍ ጸጉርም ማርን ከእንቁላል ጋር በመደባለቅ የጸጉር ቆዳን ከኢንፌክሽኖች መከላከልና የጸጉርን መሳሳት/መርገፍ መከላከል ይቻላል፡፡
ለጸጉር እድገት ማርን ከሎሚ ጋር በመቀላቀል መጠቀም ከጸጉር እድገት ባለፈ ለጸጉር ጽዳት ውጤታማ ነው፡፡ ይህም ውህድ ሎሚ ውስጥ ካለው የተፈጥሮ አሲድነት ጋር በመተባበር የጸጉር ቆዳን ቀዳዶች ለማጠንከር ይረዳል፡፡
ዘላቂ ውበትን፤ ጤንነትና ጥንካሬን የተፈጥሮ ውህዶችን በመጠቅም ተፈጥሮአዊ/ ያልተበረዘ ውብትን ከመስጠቱም በላይ የራስ የሆነ የማያረጅና ጥንካሬን የተላበሰ ውበትን ይለግሳል፡፡
አፍሪ ኸርባል
#ወደ ተፈጥሮ እንመለስ!
1.1K views07:34