2022-08-22 16:29:29
ታይቶ ማይጠገበው የደብረ ሊባኖስ / የጉር ወንዝ ፏፏቴ
ነሀሴ 15 2014 ዓ.ም (እሁድ) ታዳጊ ህፃናትን ጭምር አሳታፊ ያደረገው ቀለል ያለ የእግር ጉዞ ፣ የዋሻ ፣ ፏፏቴ እና የደብረ ሊባኖስ ገዳም እና ሙዚየም ጉብኝትን ያካተተው የጉዞ ፕሮግራማችን እጅግ ያመረ ነበር።
በጀማ ወንዝ ሸለቆ አስደማሚ የተፈጥሮ መልክዓምድር ውበት ተደስተን ፤ በጉር ወንዝ ፏፏቴ የውሃ ጅራፍ መላው ሰውነታችንን እየተገረፍን ከጉዞ ቤተሰቦቻችን ጋር ጥሩ ቀን አሳለፍን።
በየሳምንቱ እሁድ በምናካሂደው የክረምት ወቅት አዝናኝ እና አስተማሪ ተከታታይ የጉዞ ፕሮግራሞች አንዲትም ቀን ቀርተው የማያውቁት የ Plogging-Ethiopia - ፕሎጊንግ ኢትዮጵያ ንብ ትውልድ ተወካዮች የደብረ ሊባኖስ እና አካባቢው የቱሪስት መዳረሻ ቦታዎችን ላይ የሚገኙ በርካታ የፕላስቲክ ቆሻሻዎችን ሲያፀዱ ውለዋል።
ለዚህም መላው የ Plogging-Ethiopia ቤተሰቦች ትውልዱ ላይ እየፈጠሩ ስላሉት በጎ ተፅህኖ ከልብ ለማመስገን እንወዳለን።
የደብረ ሊባኖስ ፏፏቴ እና የፖርቹጋል /ራስ ዳርጌ ድልድይ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በበርካታ የሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ ጎብኚዎች የዕይታ ትኩረትን እየሳበ የመጣ የውሎ ገብ የቱሪስት መዳረሻ ሲሆን ፤ አዲስ አበባ እና አቅራቢያ ከተሞች ላይ እየኖሩ ይህን ስፍራ አለመጎብኘት ( ይበልጥ በዚህ የክረምት ወቅት)
እጅግ ያስቆጫል።
በመጨረሻም በዚህ ጉዞ ላይ አብራችሁን ለነበራችሁ አዳዲስ እና ነባር የጉዞ ዓድዋ ቤተሰቦች በሙሉ ከልብ እናመሰግናለን።
ቀጣዩ ጉዟችን በያዝነው ሳምንት መጨረሻ እሁድ (ነሀሴ 22 ) ይካሄዳል።
ጉዞ አንጎለላ
ወደ እምዬ ምንሊክ የትውልድ መንደር
የቀሩን ቦታዎች ውስን ስለሆኑ ፈጥነው ይመዝገቡ!
ቦታ:- ሰሜን ሸዋ / አንጎለላ
ይዘት :- የታሪካዊ ቦታ ጉብኝት ፣ ቀለል ካለ የእግር ጉዞ ጋር
ለዝርዝሩ https://t.me/adwav/5198
ለምዝገባ
በ +251964423971 ፣ +251942545470 ፈጥነው ይደውሉ ወይንም @guzoadwahiking @guzoad @miki_2012 ''አለሁ'' በማለት አጭር የፅሁፍ መልዕክት ይላኩልን !!
ሠላም ለሀገራችን !
#ethiopia #landoforigins #guzoadwahiking #debrelibanoswaterfall #Portuguesebridge
1.7K viewsedited 13:29