Get Mystery Box with random crypto!

ወንጌል ያሸንፋል✔️

የቴሌግራም ቻናል አርማ adventistnet — ወንጌል ያሸንፋል✔️
የቴሌግራም ቻናል አርማ adventistnet — ወንጌል ያሸንፋል✔️
የሰርጥ አድራሻ: @adventistnet
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 959
የሰርጥ መግለጫ

"ለአሕዛብም ሁሉ ምስክር እንዲሆን ይህ የመንግሥት ወንጌል በዓለም ሁሉ ይሰበካል፥ በዚያን ጊዜም መጨረሻው ይመጣል።"
(የማቴዎስ ወንጌል 24: 14)
☞ ቻናላችንን በዩቲዩብ ለመከታተል👇 ይጫኑት። http://bit.ly/2KM5PzL
ለሀሳብ አስተያየት👇
📨 @ApostleAbz
☞ አብረውን ለማገልገል #0930703775 ይደውሉ።

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-06-15 10:48:18
CALL FOR INVESTMENT

HOPE INVESTMENT GROUP

ክቡራት የFias ገጽ ተከታታዮች ኢንተርኔት ብቻ በመጠቀም እንዴት ገቢ ማግኘት እንደሚቻል በብዙ አባሎቻችን ዘንድ የታወቀ ነው። ሆኖም የሚስጥር ቁጥሮች መጥፋት፤ የወጪ ትዕዛዝ መዘግየትና የኤጀንትና አስተዳዳሪ መቀያየር የመሳሰሉ ችግሮች አጋጥመውናል። እንደ መፍትሄ አንድ የመረጃ ምንጭና አከፋፈል ጊዜ አመቻችቶ ለአባሎቻችን የምስራች ብለናል።

VIP 1
- Job - company sells
- Investment - 10,000 Etb
- Salary - 3,000+
VIP 2
- Job - company Guard
- Investment - 15,000 Etb
- Salary - 5,000+
VIP 3
- Job - company coordinator
- Investment - 30,000 Etb
- Salary - 10,000+
VIP star
- Job - company Agent
- Investment - 50,000 Etb
- Salary - 15,000+
VIP Gold
- Job - company Manager
- Investment - 100,000 Etb
- Salary - 20,000+

@fiasAmbassador

በዌብሳይት ለመመዝገብ https://fias777.com/#/pages/register?invite_code=c7RxW1Ym&t=1650283845748

አድራሻዎቻችን፦
አዲስአበባ - በፌዴራል
ባህርዳር - በአማራ ክ/መንግስት
ሀዋሳ - በሲዳማ ክ/መንግስት
አዳማ - በኦሮሚያ ክ/መንግስት
አርባምንጭ - በደቡብ ክ/መንግስት

Join https://t.me/fiasEthiopianofficial

Hope Natural Remedy Center
"Live today, Look Forward"
251 views07:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-01 10:42:05
HOPE INVESTMENT GROUP

ክቡራት የFias ገጽ ተከታታዮች ኢንተርኔት ብቻ በመጠቀም እንዴት ገቢ ማግኘት እንደሚቻል በብዙ አባሎቻችን ዘንድ የታወቀ ነው። ሆኖም የሚስጥር ቁጥሮች መጥፋት፤ የወጪ ትዕዛዝ መዘግየትና የኤጀንትና አስተዳዳሪ መቀያየር የመሳሰሉ ችግሮች አጋጥመውናል። እንደ መፍትሄ አንድ የመረጃ ምንጭና አከፋፈል ጊዜ አመቻችቶ ለአባሎቻችን የምስራች ብለናል።

VIP 1
- Job - company sells
- Investment - 10,000 Etb
- Salary - 3,000+
VIP 2
- Job - company Guard
- Investment - 15,000 Etb
- Salary - 5,000+
VIP 3
- Job - company coordinator
- Investment - 30,000 Etb
- Salary - 10,000+
VIP star
- Job - company Agent
- Investment - 50,000 Etb
- Salary - 15,000+
VIP Gold
- Job - company Manager
- Investment - 100,000 Etb
- Salary - 20,000+

ለመመዝገብ ቅድመ ሁኔታዎች፦
ዕድሜ 18+
የትምህርት ደረጃ 12+
ድርጅቱ በሚያወጣው መመሪያ መሠረት ለመሥራት ፈቃደኛ የሆነ
የCBE እና NIB Bank ተጠቃሚ መሆን

ለመመዝገብ @fiasAmbassador

አድራሻዎቻችን፦
አዲስአበባ - በፌዴ/መንግስት
ባህርዳር - በአማራ ክ/መንግስት
ሀዋሳ - በሲዳማ ክ/መንግስት
አዳማ - በኦሮሚያ ክ/መንግስት
አርባምንጭ - በደቡብ ክ/መንግስት

በቴሌግራም ገጾቻችንን ይከታታሉ https://t.me/fiasEthiopianofficial

Hope Natural Remedy Center
"Live today, Look Forward"
299 views07:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-04 16:21:18 በአንድ ወቅት አንድ ብዙ ህዝብ የያዘ አይሮፕላን ነበር፡፡ ይህ አውሮፕላን መነሻው ሰዓት በደረሰ ጊዜ ወደ መዳረሻው ለመድረስ ተነስቶ በረራውን ቀጠለ፡፡ በዚህ አውሮፕላን ውስጥ ብዙ አይነት ሰዎች ነበሩ፡፡ የአገር መሪዎችና ባለስልጣናት፣ ተመራማሪዎች፣ ሀኪሞች፣ ህፃናትና ብዙ ሙያ ያላቸውም ነበሩ። ታዲያ ይህ አውሮፕላን ይህንን ህዝብ ይዞ ጉዞውን ቀጥሏል፡፡ ነገር ግን በመካከል ያልተጠበቀ ችግር ተፈጠረ፡፡ አውሮፕላኑ በሀይል መናወጥ ጀመረ፡፡ እንደ ከዚህ ቀደም ቀጥ ብሎ መጓዝ አቃተው፡፡ ስለሆነም አብራሪዉና ረዳቶቹ ሰው ሁሉ ቀበቶውን እንዲያጠብቅና እንዲረጋጋ ቢታገሉም ሰው እጅግ ተረበሸ፡፡ በአውሮፕላኑ ወስጥ ጩኸት ሆነ፡፡ በውስጡ የነበሩ የተማሩና የአገር መሪዎች ሳይቀሩ እጅግ ተረበሹ፡፡ በዚህ መካከል አብራሪዉና ረዳቶቹ ተባብረው የነበረውን ችግር መፈታት ቻሉ፡፡ ከዚህም የተነሳ አይሮፕላኑ ተረጋግቶ መብረር ቀጠለ፡፡ ውስጡን መረጋጋትና ሰላም ሞላው፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን ግን ምንም ሳትረበሽ ተረጋግታ የተቀመጠች አንዲት ትንሽ ልጅ ነበረች፡፡ ከዚህም የተነሳ የተመለከቷት ሁሉ እጅግ ተገረሙ ምን ሆና ነው ችግር አለባት እንዴ በማለት ተጠቋቆሙባት፡፡ አንድ ሸምገል ያለ ሰው ግን ቀረብ ብሎ ጠየቋት፡፡ ምን ሆነሽ ነው ልጄ? እንደዚህ ተረጋግተሽ ልትቀመጪ የቻልሽ አላት፡፡ ልጅቷም እንዲህ ብላ መለሰች አብራሪው አባቴ ነው፤ እተማመንበታሁ አለች ይባላል፡፡

አያችሁ ይህች ልጅ እንዴት በአባቷ ላይ እንደተማመነች፡፡ She knows who is in control. ወዳጆቼ ዛሬ ዓለም በከባድ ችግር እየተናወጠች ትገኛለች፡፡ ብዙ አዋቂዎችና ሀያላን ግን መረጋጋትን ሊያመጡላት አልቻሉም፡፡ ከዚህም የተነሳ የብዙ ሰዎች ልብ ተሸብሯል፡፡ የሚይዙትን የሚጨብጡትን ያጡ ነፍሳት ከቁጥር በላይ ናቸው፡፡ ነገር ግን እንደዛች ህፃን የተማመኑበትን የሚያውቁ ብቻ ልባቸውን ሰላምና ፍፁም መረጋጋት ያገኛል፡፡ ጰውሎስም ለጢሞቴዎስ በላከው ሁለተኛው መልዕክት ምዕራፍ 2 ቁጥር 12 ላይ የታመንኩትን አውቀዋለው ይላል፡፡ አያችሁ የምናመለከው አምላክ የታመንበት እንደሆን ፈፅሞ አይጥለንም፡፡ እርሱ በእሳት ውስጥ ሆነ በውሃ ላይ መንገድ አለው፡፡ ስለዚህ ቃሉ እንደሚለው በፍፁም ልባችን በእግዚአብሔር እንታመን፡፡ አምላክም ስሜን አውቋልና አስጥለዋለው ይለናል፡፡ ከከበበን ነገር ሁሉ ሊያስጥለን የሚችል ታማኝ አምላክ አለን ስለዚህ በእርሱ እንታመን፡፡ በራሳችን ማስተዋል ፈፅሞ አንደገፍ እርሱም ጎዳናችንን ያቀናልናል፡፡

God is in control!
Have a Blessed day!

ተወዳጁ የክርስቲያን ቻናል
ይ ላ ሉን
https://t.me/joinchat/AAAAAFaNe2aPcCE9f9QyWA
605 views13:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-26 12:56:16
አይምሮን የሚጎዱ ተግባራት

1. ጥላቻ
2. ቁርስ አለመመገብ
3. እንቅልፍ ማጣት
4. ብዙ እንቅልፍ ማብዛት
5. ከፍተኛ የስኳር መጠን መውሰድ
6. ከመጠን በላይ መመገብ
7. ተሸፋፍኖ መተኘት
8. እየታመሙ መስራት
9. አልኮልና አደንዛዥ ዕጽ መጠቀም
10. ማጨስ

አዕምሯችንን ጤናማ በማድረግ የእግዚአብሄርን ቤተመቅደስ ባለማርከስ አምላካችንን እያመሰገንን መኖር እንድንችል እግዚያብሔር ይርዳን!

ተወዳጁ የክርስቲያን ቻናል
ይ ላ ሉን
https://t.me/joinchat/AAAAAFaNe2aPcCE9f9QyWA
644 views09:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-23 20:36:32 #ማሳሰቢያ:
•ከመብራታችሁ ጋር በማሰሮአችሁ ዘይት ያዙ•
እንግዲህ የሰው ልጅ ሲመጣ፥ በዚያን ጊዜ ሁለት ሰዎች በዕርሻ ላይ ይውላሉ፤ አንዱ ይወሰዳል፤ ሌላው ይቀራል። ሁለት ሴቶች በወፍጮ ይፈጫሉ፤ አንዷ ትወሰዳለች፣ ሌላዋ ትቀራለች። ሙሽራው
በምን ሰዓት እንዲመጣ አታውቁም። ከሙሽራው ጋር አብሮ ለመሄድ፥ ከመብራታችሁ ጋር በማሰሮአችሁ ዘይት ያዙ!
~~~~~~~~
|ማቴዎስ 24 እና 25|
×××××××××××
መልካም ቀን ይሁንላችሁ።
@Yemezemur_Maikel1150
@Yemezemur_Maikel1150
771 views17:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-21 23:46:34
ግሩም ፍቅር/ Girum Fikir
ቂርቆስ አድቬንቲስት ቤ/ክ
12 መዝሙር
58 ደቂቃ

Amazing Love
by Kirkos SDA Church

http://itunes.apple.com/album/id1575605280?ls=1&app=itunes

http://itunes.apple.com/album/id/1575605280

https://open.spotify.com/album/5dQc2q9vK6NK3lNcRJEp7s

አድምጡት፤ ብሩካን ናችሁ!
@Adventistnet @Adventistnet
1.8K viewsedited  20:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-21 22:46:50 የዓመቱ ትንቢታዊ ቃል

“እግዚአብሔርን ፈልጉት፥ ትጸናላችሁም፤ ሁልጊዜ ፊቱን ፈልጉ።” 1 ዜና 16፥11

በጌታ በኢየሱስ ስም በእኔና በአማኞች ህይወት አውጃለሁ፤ 2 14 ትውልድ የእግ/ርን ፊት አብልጦ የሚፈልግበትና በጀመረው የጽድቅ መንገድ የሚፀናበት ሆነ በኢየሱስ ስሞ!

አሜን! እያላችሁ አጋሩ፤ ይሄ ቃል በእኔና በእናንተ ህይወት ተፈፀመ!

HAPPY NEW YEAR
@Adventistnet @Adventistnet
876 views19:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-21 13:26:51
823 views10:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-05-29 13:22:59 "ለምን" ብለህ ጠይቅ!

"አንዲት ሴት ወይዘሮ በባቡር ጉዞ ላይ ሳሉ አጠገባቸው ባለው ወንበር ላይ የተቀመጠ ሻንጣ ስለነበር አንድ ሠራተኛ መጥቶ ይህ ወንበር ለሰው መቀመጫ እንጂ ለዕቃ ማኖሪያ አልተፈቀደምና እባክዎ ያንሱ ሲላቸው ‹‹አላነሳም›› አሉት፡፡

‹‹ቢያነሱ ይሻላል እምቢ ካሉ ለአለቃዬ እነግራለሁ›› ቢላቸውም ‹‹ሂድ ንገር›› አሉት፡፡ ሂዶ ሲነግረው አለቅየው መጥቶ "ያንሱ እንጂ ለምን አላነሳም ይላሉ?" ብሎ ቢነግራቸው ‹‹አላነሳም›› በሚለው ሐሳባቸው ጸንተው የማይበገሩ ሆኑበት፡፡

በመጨረሻም ለዋናው ኃላፊ ተነግሮት ይመጣና ‹‹ይህን ሻንጣ ያንሱ›› ሲላቸው ‹‹አላነሳም›› አሉት፡፡ ዋና ኃላፊውም ‹‹ለምን?›› ሲላቸው ‹‹ገና አሁን አዋቂ ሰው መጣ፡፡ እኔ የቸገረኝ እኮ እስካሁን ድረስ ‹‹ለምን›› ብሎ የጠየቀኝ ባለመኖሩ ነበር፡፡ አንተ ‹‹ #ለምን ?›› ስላልከኝ አመሰግንናለሁ፡፡ በመሠረቱ ግን ሻንጣው የእኔ #አይደለም ሲሉት በመደነቅ ይቅርታ ጠየቃቸው ፡፡"

ወዳጄ በህይወትህ ለሚያጋጥም ነገር ሁሉ ለምን? ብለህ ጠይቅ።

ሰዎች ምን እንደሚያስቡ ስለማናውቅ ለመፍረድ አንቸኩል ለምን? ብለን በመጠየቅ፤ በማስተዋል እናመዛዝን።

“የእግዚአብሔርም ሰው ኤልሳዕ የእስራኤል ንጉሥ ልብሱን እንደ ቀደደ በሰማ ጊዜ፦ ልብስህን #ለምን ቀደድህ? ወደ እኔ ይምጣ፥ በእስራኤልም ዘንድ ነቢይ እንዳለ ያውቃል ብሎ ወደ ንጉሡ ላከ።” 2ኛ ነገሥት 5፥8


ክብር ለኢየሱስ ይሁን!

ተወዳጁ የክርስቲያን ቻናል
ይ ላ ሉን
https://t.me/joinchat/AAAAAFaNe2aPcCE9f9QyWA
1.6K views10:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-05-11 16:46:21 እምነት

ቅዱስ መጽሐፋችን ሰዎችን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ጸጋ እንደተገለጠ ይነግረናል (ቲቶ 2:11)። ይህም ማለት ከሁለት ሺህ ዓመት በፊት በቀራንዮ የፈሰሰው የልጁ ደም ከ7 ቢሊዮን በላይ የሆነውን የአለማችንን ህዝብ ማዳን የሚችልበት አቅም አለው ማለት ነዉ። ይሁን እንጂ፤ በአሁኑ ጊዜ ሁሉም የሰው ዘር መዳን አልቻለም። ለምን?

ማመን ስላልቻለ! በኢየሱስ ላይ እምነት ስለሌለው። እምነት ምንድን ነው?

እምነት ማለት የማይታይን ነገር እንዳለ እርግጠኛ መሆን ነው። በአንዳች ምድራዊ ጥበብ ልታብራራው የማትችለውን ነገር እውነት እንደሆነ ለራስህ የምታረጋግጥበት ሁኔታ እምነት ይባላል። የዕብራውያን መልዕክት 11ኛው ምዕራፍ ስለ እምነት እና የእምነት ምሳሌ ስለሆኑ አባቶች ዘርዘር አድርጎ ያብራራልናል። እምነት ተስፋ የምናደርገውን ነገር እንደተቀበልን የምንቆጥርበት መሣሪያ ነው። አብርሃም የት እንደሚሄድ እንኳን ሳያውቅ በእግዚአብሔር ትዕዛዝ እንደወጣ፤ ሄኖክ በዓይን ያላየውን አምላክ አምኖ አካሄዱን ከእርሱ ጋር እንዳደረገ፤ ስለ ሌሎችም ይናገራል። ሁሉም ታሪኮች እጅግ ማራኪ ቢሆኑም እኔ ግን በግሌ ውስጤን የሚነካው የኖኅ ታሪክ ነው።

እግዚአብሔር በሰው ልጅ ኃጢአት ብዛት ከመከፋቱ የተነሳ በውሃ ጎርፍ ሊያጠፋቸው በወሰነ ጊዜ ኖኅ ግን በእርሱ ፊት ሞገስ አግኝቶ ነበር። በመሆኑም፤ ኖኅ እና ቤተሰቦቹ ከጥፋት የሚሰወሩበትን መርከብ ራሱ ኖኅ እንዲያዘጋጅ እግዚአብሔር አዝዞት ነበር። ነገር ግን ፤ እግዚአብሔር የመርከቡን ዲዛይን ሲሰጠው ለጥፋት ውሃው መምጣት ብዙ ዓመታት ቀርተው ነበር። በወቅቱ ዝናብ አልነበረም፤ ወይም ደግሞ የተለመደው መደበኛ ዝናብ ብቻ ነበር። ኖኅ ግን፤ በታዘዘው መሠረት እንጨት መቁረጡን፤ መጥረቡን፤ መላጉን እና መገጣጠሙን ጀምሯል። ለሚጠይቀው ሁሉ የጥፋት ውሃ ሊመጣ እንደሆነ ሲነግር በሙሉ ልቡ ነበር። በባዶ ቦታ ስለ የጥፋት ውሃ ሲያወራ ሳቅ ያመለጣቸው እንደነበሩ መገመት አይከብድም። ምናልባትም ኖኅ እብደት እየጀማመረው እንዳይሆን ሰግተው ያዘኑለትም አይጠፉም። እርሱ ግን በደረቅ መሬት ላይ ተቀምጦ በእምነት ዓይኑ በጥፋት ውሃ የተጥለቀለቀለችን ምድር ያይ ስለነበር የመርከብ ዝግጅት ሥራውን እያፋጠነ ነበር። ይህ እእንግዲህ እምነት ይባላል።

መጽሐፍ እንደሚናገር ያለ እምነት እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት አይቻልም። እግዚአብሔር አማኞችን ይወዳል። እንደ ዕብራውያን መልዕክት አንድ ሰው እግዚአብሔርን ደስ ለማሰኘት በሁለት ነገር ላይ ጠንካራ እምነት ሊኖረው እንደሚገባ ያስረዳል። 1) እግዚአብሔር እንዳለ 2) ለሚጠይቁትም ነገር መልስ መስጠት እንደሚችል።

አንዳንድ ሰዎች እግዚአብሔርን "እስቲ እውን አንተ ካለህ እንዲህና እንዲያ አድርግና አረጋግጥልኝ" ይሉታል። ይህ እግዚአብሔር መልስ የማይሰጠው ጥያቄ ነው። ቢመልስም በበጎ እና ለበጎ ላይሆን ይችላልና እንዲህ አይነቱ ጥያቄ ለሥጋም ሆነ ለመንፈስ አይበጅም። በነገራችን ላይ፤ እግዚአብሔር አለ። ያንተ ጸሎት ቢመለስም ባይመለስም እርሱ አለ! ይኖራልም። የኛ ጥያቄ መልስ የማግኘት ያለ ማግኘት ጉዳይ የእርሱን ህልውና አያጸናም፤ አይሽርምም።

እግዚአብሔር እንዲሁ የሚያምኑትን ይወዳል። የኢየሱስን ቁስል በእጁ ነክቶ ካመነው ቶማስ ይልቅ ስለ ኢየሱስ ወሬ ሰምቶ ያመነ ሰው በብዙ እጥፍ የሚመሰገነውም ለዚህ ነዉ ። "ሳያዩ የሚያምኑ ብጹዓን ናቸው" ነውና መርሁ።

ጸጋና እምነት በአማኙ ሕይወት ውስጥ የማይነጣጠል፤ የማይነጻጸር ሚና አላቸው። ጸጋ ያለ እምነት በሰው ማንነት ውስጥ ሥራውን ሊሰራ ከቶ አይችልም። በሌላ አገላለጽ፤ ጸጋ ስላለ ብቻ ሰው ያለ እምነት ሊድን አይችልም። እምነት ስላለው ብቻም አይድንም። ሰው የዘላለም ሕይወት እንዲያገኝ እምነቱን በእግዚአብሔር ጸጋ ላይ ማድረግ አለበት (የሰው ልጅ እምነቱ በብዙ ነገር ላይ ሊሆን እንደሚችል ልብ ይሏል)። "ጸጋው በእምነት አድኖአችኋል" አይደል ቃሉ የሚለው (ኤፌ. 2:8)?

ስለዚህ ያላመነ በጸጋው አምኖ ይዳን! በጸጋው ያመነ እምነቱን አጽንቶ ይያዝ!
ጸጋ ብቻ! እምነት ብቻ!

የጸናው የትንቢት ቃል
1.2K views13:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ