Get Mystery Box with random crypto!

ማንነት

የቴሌግራም ቻናል አርማ maninet1 — ማንነት
የቴሌግራም ቻናል አርማ maninet1 — ማንነት
የሰርጥ አድራሻ: @maninet1
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 758
የሰርጥ መግለጫ

ራስን ማወቅ ጥበብ ነው… የማንዳስሰው ነገር አይኖርም
ከመጽሃፍት አለም
ሃይማኖታችን
ፍልስፍና
የኑሮ ዘይቤያችን
ፖለቲክስ
የፍቅር ህይወታችን…ሁሉም ሁሉንም ማንነታችን ይዳሰሳል
ለየትኛውም ጥያቄ ወይም አስተያየት እና cross @betsiroyal ይጻፉልን…
@maninet1
@maninet1

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-06 17:38:10 አንዳንድ ትዝታ አለ
-ዝምታችን -ከዝምታ ገዝፎ በአርምሞ በተዘጋንበት ጊዜ :በዕዝነ ልቡናችን በኩል <<ኡኡ>> ብሎ የሚጮህ ፡፡ በለሆሳስ ÷በዝግታ ካሳለፍነዉ የእድሜ ዘመን፡ ቅፅበቶቻችንን ከሽርፍራፊ የልጅነት ምስላችን በልጦ ፡በልቦቻችን ጥጋጥግ ካንጠለጠልነዉ ፡ ተናፋቂ ትዝታወች መሀል ፡ ምናለ በደገምነዉ እያልን የምንመኘዉ፡፡
ከትላንት ትዝታወቻችን ጋር ፡ ባንቀላፋን ቁጥር ሳንሰለች ደጋግመን የምንኖረዉ፡፡ አንዳንድ ትዝታ አለ ፡ እንደወይን እያደር ጣዕሙ የሚጨምር ፡ በእምባ በተምሸርንበት ጊዜ እንኳ ÷ በሐዘን ወህኒ ተወርዉረን ፡ መረሳት ክፋ እድል ፊት ለፊታችን ሲጋረጥ፡ የመኖር ጣዕም ሲጎመዝዝ ÷በእቅፋ ሚያስጠልለን፡፡ አንዳንድ ትዝታ አለ በዘመን መጎስቆል ባረመምንበት ጊዜ እንደ አዲስ የሚወልደን ፡ የማያረጅ የእድሜያችን ሞቃት ምዕራፍ ፡፡ አነዳንድ ትዝታ አለ --- አየ ጉድ - ትዝ አለችኝ መሰል፡፡
92 views14:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-17 20:27:57 ፍቅር በዚያ ወራት !

(ክፍል 5)
ሚካኤል.አ

ለምን እንደሆነ ባላውቅም የዛኪን ስልክ አለማንሳት አልቻልኩም። ድምፁ ናፍቆኛል.. .

"ሄሎ "

"ሄሎ ንፁህ.. ."

ዝም አልኩት ። ረጋ ያለ ድምፅ!  ... 

ንፁህ ብሎ ሲጠራኝ እንባዬ ፈሰሰ ። አፍቃሪው ልቤ በክህደት ሰንሰለት ተተብትቦ በፀፀት አርጩሜ እየተወገረ ነው።

"ሄሎ " .. የድምፄን መጥፋት ሲረዳ ደግሞ ተናገረ ።

"ሄሎ ቲቸር "

"በሰላም ነው የጠፋሽው? ህመሙ አልተሻለሽም እንዴ?"

የተሻለኝ ህመም የለም። ጭራሽ የማይድን ሌላ የውስጥ ቁስል አመርቅዣለሁ ።

እወደዋለሁ.. .

የንሰሀዬ መንገድ የሱ ስክነት ነው። እሱ ቢያቅፈኝ...እሱ ቢያስብልኝ... እሱ መዳፉን አውሶ ቢዳብሰኝ እንደስሜ እነፃ ነበር ።

"ምንድነው ለቅሶ ነው የምሰማው ?" 

"አዎ ዛክ "

"ምን ሆነሻል ?" 

"እወ.. .."

ሰውን እወድሀለሁ ብሎ መናገር ለካ ይከብዳል ።

ቃላቶቼን ከምኔው እንደዋጥኳቸው አላቅም። ለሱ ፍቅሬን መግለፅ ስሜቱን የሚገድልብኝ ይመለኛል። ዛክ ከወንዶች ሁሉ ይለያል ብዬ ባስብም ሁሉም ወንዶች ደግሞ የሚያመሳስላቸው የጋራ ባህሪ እንዳላቸው አምናለሁ ። 

ሴት ልጅ ለወንድ ልጅ የውስጧን ስሜት በግልፅ ከነገረችው ለሷ ያለው አመለካከት ይወርዳል። ወንድ ልጅ ከአፍቃሪው ይልቅ በኩራት ገመድ ወጥራ ለምታሰቃየው ሴት የልቡ በራፍ ይከፈታል ።

ኩራት !

ወንዶች መለመን ይፈልጋሉ.. . እንደ ወርቅ ተደብቃ የማህደሯ ክርታስን ለመቆፈር የምታታግል ሴት የወንዶችን ልብ ቁልፍ በእጇ ይዛ ትዞራለች ።

"ምን አልሽ?"

"አወ...ቅማ ዶክተር እባክህ ትንሽ ህመሜ ስለጠነከረ ተጨማሪ ቀናትን ባልመጣ እንዳትቀየመኝ። "

"ለምን እቀየምሻለሁ?  ትምህርትም...ስራም.. .ከጤና በላይ አይሆኑም። ስትኖሪ ነው ሁሉ ነገር የሚኖረው።

በይ ፈጣሪ ይማርሽ ።"

"አሜን !" አልኩት ።

ይሄን ያልኩት ግን ለበሽታዬ ድህነት አይደለም። ፈጣሪ እኔ ላይ የሰራሽውን ሀጥያት ይቅር ብሎ ይማርሽ እንዳለኝ ነው የተረዳሁት የኔ ካህን ።

ስልኩ ሲቋረጥ ከንፈሬን ወደ ስክሪኑ ሰድጄ ሳምኩት ።

እኔ የሱ መቅደላዊት ማርያም ... 

በደሌ በፍቅሩ የሚነፃ ከሆነ ብዬ በእንባዬ ራስኩኝ።

....

በዛኑ ቀን ዶክተር እዘዝ ደወለ።

በሙት ስሜቴ ስልኩን አነሳሁት ። እድለ ቢሶች ከምንወደው ነገር ይልቅ የማንወደው ነገር ይከተለናል ። ዶክተር እዘዝ ን አልወደውም። በተለይ ከዛ ክስተት በኃላ የርኩሰቴ ቤንዚን ሆኖ ይሰማኛል።

"ጣፋጯ " አለኝ።

መራሩ ልበለው ይሆን?

"ይቅርታ ዶክተር ...እንደዚህ አትበለኝ "

" ምነው አንዴ የቀመሽውን ገላ መድገም አትወጅም መሰለኝ። ይሄ እኮ የሴቶች ሳይሆን የእኛ ባህሪ ነበር ለወትሮው ...

ቂ....ቂ...ቂ ..."

ሳቅ ይሄን ያህል ይቀፋል?

"ሁሉም ነገር ባጋጣሚ ነው የሆነው "

ቲቸር እዘዝ ቀፋፊ ሳቁን ቀጠለው ።

"ቂ....ቂ ...ቂ 

ለማንኛውም ተረጋጊ ...ጥሩ ጊዜ ነበረን። ጥሩም ሆነን ሴሚስተሩን እንጨርሳለን"

ይሄን ሲል እየዛተ ነው። ለኔ ጥሩ ካልሆንሽ ጥሩ ጊዜ አይኖረንም ሊለኝ እንደፈለገ ግልፅ ነው።

"እባክህ..."

አላስጨረሰኝም ። ስልኩ ከወዲያኛው አቅጣጫ የመዘጋት ድምፅ አሰማኝ። 

ካሁን በኃላ ትምህርት ቤቴ ገሀነሜ ነው። 

ዶክተር እዘዝ የሰይጣኑ ቁንጮ ሉሲፈሬ ነው።

ዛክን በድዬ ከሱ ጋር ያሳለፍኩትን የአልጋ ላይ ጨዋታ እንደማልደግመው አውቃለሁ።

ገላዬን ስነሳው ደግሞ ነጥብ እንደሚነሳኝ እሙን ነው ። 

የኔና የሱ ግንኙነትን ደግሞ ዛክዬ ከሰማ ሌላ የህይወት ፍላት ላስተናግድ ነው ።

ሁለት ፍላት በአንድ እስትንፋሴ የምሸከምበት አቅም ያለኝ አይመስለኝም።

አልጋዬ ማህፀን ገብቼ ተሸፋፍኜ ተኛሁ ።

የውሸት እንቅልፍ ነበር ...

ሰኞ ትምህርት ቤት ስሄድ ለሚገጥመኝ ጦርነት ልቦናዬን ማዘጋጀት ጀመርኩ ።

አሸናፊው ማን እንደሚሆን እናያለን! 

@maninet1
@maninet1
@betsiroyal
362 views17:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-13 20:00:04 "እመጓ"
311 views17:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-11 22:17:51 ሰላም ቤተሰቦች ለሰሞኑን

የአለማየሁ ዋሴ እሸቴን መፅሐፍ ልለቅላችሁ አስቤያለው ከየትኛው ይጀመር @betsiroyal ላይ ምርጫችሁን ንገሩኝ

1.እመጓ
2.ዝጎራ
3.መርበብት
4.ሰበዝ
5.ሜተራሊዮን በቅርቡ የታተመ ስለሆነ በpdf ለም!
@betsiroyal

ማጋራት መተሳሰብ ነው!

@maninet1
345 viewsedited  19:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-11 22:17:51 ዶ/ር ዓለማየሁ ዋሴ እሸቴ


ሁሉን ነገር መፈለግ፣ ሁሉን መሻት፣ ያለገደብ ለመኖር ማሰብ የዚህ ዓለም ጣጣ፣ የድካም ምንጭ ነው።

የምትጠቀምበትን ያክል ብቻ እወቅ፤ የሚያጠግብህን ያክል ብቻ ብላ፤ የሚያረካህን ያክል ብቻ ጠጣ፤ ሁሉን ነገር ማጣት ሰቀቀን ቢሆንም ሁሉን ነገር ማግኘትም ዕዳ ይሆናል፡፡

ምንም አለማወቅ ባዶነት ቢሆንም ሁሉን ማወቅ ደግሞ ሸክምም ይሆናል።''

<ዝጎራ>


ማጋራት መተሳሰብ ነው!

@maninet1
377 views19:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-08 19:36:39 ፍቅር በዚያ ወራት (ሚካኤል.አ) #ክፍል 3 ከንፈሮቹን ልጎርሳቸው ተጠጋሁት.. ወደ ከናፍሩ ስጠጋ የውብ ትንፋሹ መዓዛ አወደኝ ። የተቀባው ሽቶ በአፉ ከሚያላምጠው ሜንት ማስቲካ ጋር ሲዳበል የገነት መግቢያው የሱ መዓዛ ነው ቢሉኝ ውሸት ነው አልልም። ወድያው "አይዞሽ ውዴ! " የሚል ድምፅ ሰማሁ ። ሺት ! የፈራኋት ጣውንቴ መጣች ። የነጃት ጥላቻዬ አስራ አንድ በመቶ ሲያድግ ተሰማኝ (ፖለቲካ አይደለም…
332 views16:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-06 20:24:09 {የቀይ ኮከብ ጥሪ የተቀነጨበ \ ከበዓሉ ግርማ}

የሰው ልጅ በጣም የሚወደው ንብረቱ ሕይወቱ ነው። ሕይወቱም የተሰጠው አንድ ጊዜ ብቻ ነው። ለባከኑ አመታት ምንም አይነት ጭንቀት ሳይሰማው የተሰጠውን ሂወት መኖር አለበት። ስላለፉ ጥቃቅን ነገሮች እያሰበ በሀፍረት የመሸማቀቁን ትርጉም በጭራሽ ሊያውቀው አይገባም...በሂወቴ ሙሉ ክፍል የተሰጠኝ ሙሉ ሀይል የተቸረኝ በአለም ላይ ምርጥ ለሆነ አላማ ነው።

@maninet1
@betsiroyal
311 views17:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-05 16:15:45 ፍቅር በዚያ ወራት
(ሚካኤል.አ)
#ክፍል 3
ከንፈሮቹን ልጎርሳቸው ተጠጋሁት.. ወደ ከናፍሩ ስጠጋ የውብ ትንፋሹ መዓዛ አወደኝ ። የተቀባው ሽቶ በአፉ ከሚያላምጠው ሜንት ማስቲካ ጋር ሲዳበል የገነት መግቢያው የሱ መዓዛ ነው ቢሉኝ ውሸት ነው አልልም።
ወድያው "አይዞሽ ውዴ! " የሚል ድምፅ ሰማሁ ።
ሺት !
የፈራኋት ጣውንቴ መጣች ። የነጃት ጥላቻዬ አስራ አንድ በመቶ ሲያድግ ተሰማኝ (ፖለቲካ አይደለም !)... በሷ ቤት አንድ ቀን ኒቃቧ ከፊቷ ሲወርድ ቀድሜ ስለደረስኩላት በችግሬ ጊዜ ቀድማኝ መድረሷ ነው። ችግሬ እሷ እንደሆነች ብታውቅ ስል ተመኘሁ።
"ነጅዬ እባክሽ handle " አድርጊያት ብሎ ዶክተር ወደ ክፍሉ ገባ። ነጅዬ ሲላት ደግሞ ነብር ሆንኩኝ... ከየት መጣ ያልተባለ ቀዝቃዛ ውሀ ፊቴ ላይ ከነበለችብኝ።
የዛክዬን ከናፍር ከመጉረስ ስታግደኝ ነው መቀዝቀዝ የጀመርኩት ።
"ተረጋጊ እንጅ ፀጉሬን ..." ብዬ ጮህኩባት ።
እሷ እንኳን ልትደነግጥ ወገቤ ስር ገብታ አነሳችኝ ። በጥፊ ጉንጯን ባቀላው ስሜቴ ነው ።
እሷና ጓደኞቿ አንከብክበው ጥላ ያላት አፀደ ስር አኖሩኝ ። ንፋሱ ከውሀው ቅዝቃዜ ጋር ተዳብሎ በረደኝ ።
ጥርሶቼ በእልህና ቅዝቃዜ ተንገራገጩ።
"አይዞሽ ንፁህ.. . "
ራስሽ አይዞሽ ብዬ ልመልስላት ይሆን?
አይኖቿ የሚስቁለት.. .ነፍሷ የምትፈነጥዝለት ዛኪን ልቀማት መሆኑን ማን ሹክ ባላት ?
...
ከዛ ክስተት በኋላ ወደ መደበቂያዬ ሮጥኩ !
ክለብ.. .
ጠጣሁ.. . አምሮቴ ንቅል እስኪልልኝ ጠጣሁ ።
ሞቅ እንዳለኝ ያየ አንድ ጎረምሳ የሚያጨሰውን ሺሻ ትቶ ወደኔ አቅጣጫ መጣ።
"ቆንጆ ነሽ" አለኝ።
ዝም!
"ምነው የከፋሽ ነገር አለ ?"
ዝም!
ምናለ ከዛኪ በስተቀር የዓለም ወንዶች ሁሉ ባያናግሩኝ? አባቴና ወንድሜ እንኳ እንዲያናግሩኝ የምፈልግ አይመስለኝም።
አሁን ይሄ የሰማይ ስባሪ የሚያህል ወደል እንዴት ያናግረኛል ?
ጠጪ ...አጫሽ ወንድ ነው ያስጠላኝ።
ያዘነ ለመምሰል ሞከረ !
ውሸት.. . አይኖቹ ውሸት! ...ሳቁ ውሸት...ንግግሩ ውሸት ...
ቆንጆ ነሽ ሲለኝ አመሰግናለሁ ቢለኝ ...አብረን እንፍታታ ብሎ ይቀጥላል ።
እሺ ብለው እኔ ጋር ለማስመሰል ውስኪ ያወርዳል።
ምድር ላይ ያፈቀራት ሴት እኔ ብቻ የሆንኩኝ ያህል አስመስሎ ይንከባከበኛል...ከዛ መተኛት !
አንዴ ጭኔ ስር ገብቶ በለሴን ከቀጠፈ እኮ በነጋታው ስልክ አያነሳልኝም።
ይሄ ህይወት ሰልችቶኛል.. . ነፍሴ ዛኪ ጉያ ገብታ መሸሸግ ትፈልጋለች ።
ሀጥያቴ የሚጠራው በሱ ላቦት ነው።
"ማሬ አመልሽም ?"
"ማርህን ጎዣም ፈልግ !" አንባረቅሁበት ። ከመቅፅበት ከስሬ በሮ ጠፋ ። ፈሪ ወንድ !
አሁን ይሄ ነው የኔን ጀንታላ ዛክ የሚተካልኝ?
ሌላ ብስጭት.. .
መጠጥ.. . ሻት ...
በቃ ራሴን አጣሁት ። የክለቡ ብልጭ ድርግም መብራት ...መጠጡ.. .ሙዚቃው ናላዬን አዞረኝ ።
ምንም ሆንኩ !
እንደምንም ተንገዳግጄ ሰው መሀል ገብቼ ጨፈርኩ።
እንደ ልማዴ የሰው ሆንኩ...ሳቄ ...ደስታዬ ሁሉ የሰው ሊሆኑ ራሳቸውን ከመቃብር ቀስቅሰው ተነሱ።
ከሩቅ ለሚያየኝ ሰው ደስተኛ ነኝ...ነፈዝኩ...ነጎድኩ ...ብንንንንንንንንንን....
አላልኩም ?
ስጠጣ የሰው ነኝ ብዬ አልነበረምን ?
ማልዶ ስነሳ ራሴን ከሰው ጋር አገኘሁት ።
አንሶላዬን ገልጬ ተስፈንጥሬ ተነሳሁ ።
አብሮኝ ያደረው ወንድ እንደ ጆንያ ተንደባሎ ፊቱን ወደኔ አዞረ?
እንዴ?
ይሄ የኢኮኖሚክስ መምህሩ እዘዝ ነው እንዴ?
ዛኪ የነፍስና ገላዬን መርከስ አይቶ የጠላኝ መሰለኝ...
"አንተ ማነህ ?"
.
(ይቀጥላል)

@betsiroyal
@maninet1
@maninet1
322 views13:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-02 18:26:37 ፍቅር በዚያ ወራት 

ክፍል 2

(ሚካኤል .አ)

የክፍላችን በር ጋር እስክደርስ የነበረኝ በራስ መተማመን ስሜት እምን ጉድጓድ እንደገባ አላውቅም። ዶክተር ዛኪን ሳየው ልቤ በአፌ ልትወጣ ታገለችኝ። 

እንደ ልማዱ ፅድት ብሎ መጥቷል። (በጣም የሚገርመኝ ነገር ጫማው ላይ እንኳ ብናኝ አቧራ የለምኮ ) ... ለነገሩ ከቤቱ ወጥቶ በኔ ልብ ላይ ተራምዶ ክፍል እየደረሰ በየት በኩል አቧራ ሊነካው ይችላል?

በማስተማሩ በፊት ሁላችንንም በስስት እያየ ሰላምታ ይሰጠናል...ጨዋታ አዋቂ ነው። 

ቢያንስ ፊት ለፊት ከሚቀመጡ አንድ ሁለት ልጆች ጋር ሳይጨዋወት ወደ ማስተማሩ አይገባም። ሲስቅ ከልቡ ነው ... ነጭ ባይሆንም ፈዛዛ ሽሮ መልክ ያላቸው ስድር ጥርሶች አሉት ። ድዱ በእጅ ሳይወቀር ተፈጥሮ አሽሞንሙና ሰርታዋለች ። 

እሱ ይስቃል.. .ልቤ ታለቅሳለች ። ስድር ጥርሶቹ የኔን ነፍስ የሚያጠፋባቸው ድርድር ጥይቶች መሆናቸውን ማን በነገረው ?

ፈገግታው ደስም ይለኛል.. .ያስቀናኛልም። 

በተለይ ለነጃት ሲስቅላት እነዳለሁ ።

ደግነቱ እንደዚህ አይነት አክራሪ ክርስትያን ሙስሊሟን ነጃት ሊወድ ስለማይችል ለራሴ ቅናት መፅናኛ አላጣም።

ይሁንና ግን ይሄን አስቤ እንኳ ልቤ እርፍ አትልልኝም...ያቺ ጣውንቴ አይኖቿ ያምራሉ ...ሰውነቷ ከኔ ይበልጥ የሚስቡ ይመስለኛል...ብዙ ጊዜ ዛኪ አቀርቅሮ ትምህርት ሲተነትን እነዛ ሎጋ የእግር ጣቶቿን እያየ ስለሚመስለኝ እበሽቃለሁ ።

የሆነ ቀን ላይ የፊት ኒቃቧ ሲወርድ መልኳን አየሁት ...ለክፋቱ ደግሞ ዶክተር ፊትለፊታችን ነው። መልኳን ሲያይ መደንገጡን አይቼበታለሁ ...(ድንገትም ስለማፈቅረው መስሎኝም ሊሆን ይችላል )

ከሁሉም ተማሪ በላይ ዘልዬ ፊቷን የሸፈንኩላት እኔ ነኝ። ሙስሊም ጓደኞቿ አላህ ይባርክሽ ብለው መረቁኝ... (ይሄን ያደረኩት ከነጃት የውበት ፆር ዛኪዬን ለመደበቅ መሆኑን የሚያውቀው አላህ ሲባርከኝ እኮ ታየኝ !)

በቃ ከዛን ቀን በኋላ አይኖቼ ሁለቱንም ይከታተላቸዋል። ለሴት ልጅ ውበት ግድ አልባው ዛኪ ለነጃት ግን የተመየ ስሜት ያሳደረ ይመስለኛል....። ክፍል ውስጥ ፊትለፊት ስለምትቀመጥ ሳያሳስቃት ምንም ነገር አይጀምርም። 

ደግሞ ሌላ የሚያበሽቀኝ ነገር የሷ ሳቅ ነው። ስታየው ገና አይኖቿ ይበራሉ.. .ትንሽ ያወራት ጊዜማ ነፍስያዋ ትዘላለች) 

በዚህ ቅናት ተነሳስቼ እኔም እንደሌሎች ቸካይ ተማሪዎች ፊትለፊት ሄጄ ተቀመጥኩ ።

ብዙ አልምጥ ጓደኞቼ ተሳለቁብኝ። ትምህርት እንደሚደብረኝ ብቻ ሳይሆን እኔም ትምህርትን እንደምደብረው ሁሉም በዙሪያዬ ያሉ ልጆች ያውቃሉ። የኔ ፊት ወንበር ሄዶ መቀመጥ ተማሪውን ብቻ ሳይሆን መምህሬንም ገርሞታል ።

"ዛሬ እንዴት ነው? ... የመማር ሞራልሽ መጥቷል ማለት ነው" ፈገግ አለልኝ ።

ሞትኩለት !

ክለብ ለክለብ የሚቅለበለበው ምላሴ ጉሮሮዬ ላይ ገብቶ ተሰነቀረ ።

የሆነ ቅጥ የሌለው መልስ መለስኩኝ.. .

"አ....አ......መ...ሰ....ለ....እ....ኝ "

ስደናበር ነጃትና ጓደኞቿ ተያይተው ሳቁብኝ። 

በቃ ጠመድኳት ይህችን ሴት !

"ንፁህ ምን ሆነሻል እጅሽ እየተንቀጠቀጠ ነው እኮ!  አመመሽ እንዴ? "

"አዎ ቲቸር !" 

ይኸው የኔ ትሁት ዛኪ ደገፍ አድርጎ ከክፍል እንድወጣ ዕድል ሰጠኝ ።

አለንጋ ጣቶቹ ወገቤን ሲይዙኝ የእውነት ታመምኩለት ...ሰውነቴን እሱ ላይ ጣልኩት ።

የክፍሉን በር ከፍቶ ወጣን ።

"አይዞሽ ንፁህ.. ."

እንዲህ ሲለኝ የነጃት የቅናት ዛር አናቴ ላይ ተፈናጠጠ ።

በድፍረት ከናፍሩን ስሜ ፍቅሬን ልገልፅለት ደፈርኩ ...

አንድ 

ሁለት

ሶስ.....

     (ይቀጥላል)

@maninet1
@maninet1
@betsiroyal
313 views15:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-31 19:58:27 ፍቅር በዚያ ወራት

፤፤፤ ሚካኤል.አ ፤፤፤

(ክፍል 1)

ስሜ ንፁህ ይባላል ። የስሜ እዳ አለብኝ። እንኳን ለሰው ልጅ ለመላዕክት እንኳ ያልተገባ መጠሪያ መያዜን ሳስበው እሸማቀቃለሁ።
ከክፍል ጓደኞቼ ጋር እየጨፈርን.. .ሺሻ እያጨስን በምናሳልፋቸው ወቅቶች ስሜን የሚጠራኝ ሰው ባይኖር ስል እመኛለሁ።
ደግሞ ማንም እንደሚያውቀው የትምህርት ቤት ህይወት (ላይፍ ይሉታል ጓደኞቼ በቋንቋቸው) ፈታኝ መሰናክሎች አሉት ።
ጥሩ ፋሽን የማይለብስ ...የማያጨስ ...የማይጨፍር ተማሪ ፋራ ተደርጎ ይቆጠራል። ከማህበራዊ ህይወት ገሸሽ ይደረጋል። ከዚህ ክበብ መውጣት የማይፈልግ ሰው ደግሞ በሰዎች ፍላጎት መሾር ይጀምራል።
ስጨፍር የሰው ነኝ...ከወንዶች ጋር ስላፋ የሰው ነኝ...አጭር ቀሚስ አድርጌ እንደ እሳት የሚጋረፉ ወላፈን ጭኖቼን ሳሳይ የሰው ነኝ።
ስስቅ የሰው ነኝ ። ሁሉ ነገሬ አርቴፊሻል !
ከዚህ ግብግብ ስወጣ ግን ጥያቄ አለብኝ።
የህሊናዬን ጥያቄ ማፈን ስለምፈልግ መጠጥ እጠጣላሁ።
ለምን ትጨፍሪያለሽ?
ለምን ከወንዶች ጋር የውሸት ትስቂያለሽ?
ለምን ትቅሚያለሽ?
ለምን ታጨሻለሽ?
ከዛ መጠጣት.. . መጠጥ ደግሞ ጀንትል ያደርገኛል። ህሊናዬን እናትህን እለዋለሁ ።
እጠጣለሁ.. .እጨፍራለሁ...እቅማለሁ...አምራለሁ ...
እንቅልፍ ይወስደኛል።
ስተኛ ም ዝም አልልም...ተኝቶ ማሰብ ይቻላል ወይ? ለምትሉኝ ሰዎች መልሴ ድብን አድርጎ ማሰብ ይቻላል የሚለው ነው።
የማስበው ዶክተር ዘካርያድን ነው። ምርጥ መምህሬ ... ማኔጅመንት ያስተምረናል...ራሴን ማኔጅ ማድረግ ለተሳነኝ ሴት የድርጅት ማኔጅመንት መማር ግን አያስቅም?
ዛኪ መደበቂያዬ ነው። በሱ ክፍል እኔን ጨምሮ የብዙ ሴት ጓደኞቼ አይን ይስለመለማል ። የሄዋን ዘር ይውደድህ ተብሎ የተመረቀ መምህር ።
አይቅለበለብም...አይቸኩልም...
እርጋታው...እውቀቱ.. .ንፅህናው (ፍንትው ያለ ነጭ ሸሚዝ የሚያደርግ ብቸኛው መምህር እኮ ነው)... ሁሉም ባህሪያቶቹ የሴትን ልጅ ልብ መክፈቺያ ቁልፎች ናቸው።
ቆፍጣና ወንድ !
ከትምህርት በተረፈው ሰዓት ማህበረ ቅዱሳን እንደሚያገለግል ሰምቻለሁ።
እሱ ሰላም ሲለኝ ሀጥያቴ ተሰርዮ የተቀደስኩ ይመስለኛል። ሳቁ.. .ጨዋታ አዋቂነቱ አይምጣብኝ ። በመሀል ጣል የሚያደርጋት ስብከት ለኔ የህይወት ስንቅ መሆኑን ማን በነገረው?
እንደ ሌሎች ቀለብላባ ወንድ መምህራን ለሴት ልጅ ባትና ዳሌ እጅ ስለማይሰጥ የፍቅር ፋኖስ ልቤ ውስጥ ተለኮሰ!
ቡም !
አዲስ ወጋገን...አዲስ ፍኖት ተለኮሰ !
ከእንቅልፌ ስነሳ ትራሴን ጭምድድ አድርጌ አቅፈዋለሁ። ዛኪ ነፍስያዬን ያግላታል። ሰውነቴን ሲተኩሰኝ እሰማዋለሁ። ትንፋሹ ከሱ ጋር ሳይሆን ከኔ ጋር ያድራል።
ከሁለት ሰዓታት በኋላ አይኑን ማየቴን ሳስበው ሀሴትን አደርጋለሁ።
ሆኖም ከደስታዬ ሲለጥቅ አንድ ጥያቄ ገረፍ አድርጎኝ ያልፋል።
ኪሩ ከዚህ ሁሉ አፍቃሪ ሴቶቹ መሀል እኔን እንዴት ሊመርጠኝ ይችላል?
ከኔ በላይ ቆንጆ ሴቶች ደግሞ አሉ። ልቤ ን ግን አያክሉትም...ልቤ ተራራ ነው። ማንንም ማንበርከክ ...ማንም እንዲያሸረግድልኝ የሚያደርግ ቅብዓ ቅዱስ አለኝ።
ሰለዚህ እሱን አማልሎ ወጥመዴ ውስጥ የማስገባበት ብልሀት ወጠንኩኝ...ትምህርት ቤት ስሄድ እሱን እንደምረታው ለራሴ እየነገርኩት ነው።
ንፁህ ታሸንፊያለሽ ! ብሎ የሚፎክር ጀብደኛ ልብ አለኝ።
ዶክተር ኪሩ መጣሁልህ !

(ይቀጥላል...)

@maninet1
@maninet1
@betsiroyal
284 views16:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ