Get Mystery Box with random crypto!

በወልድያ ከተማ ሠላማዊ እንቅስቃሴዋ እንደቀጠለ መሆኑን የወልድያ ከተማ አስተዳደር ኮሚኒኬሽን አሳው | አድስ ዜና

በወልድያ ከተማ ሠላማዊ እንቅስቃሴዋ እንደቀጠለ መሆኑን የወልድያ ከተማ አስተዳደር ኮሚኒኬሽን አሳውቋል።

የተለያዩ ሚዲያዎች እና የፖለቲካ ተንታኝ ነን የሚሉ የውጭ አካላት በማህበራዊ ሚዲያው ወልድያን በተመለከተ ሀሰተኛ ዜና እያሰራጩ ይገኛሉ።

" ከወልድያ አመራሩ ወጥቷል፣ ወልድያንም ህወሓት ይዟል " የሚሉ መረጃዎችን ቢያሰራጩም ሁሉም ሀሰት መሆኑና ህዝቡን ለማሸበር የሚሰራ ስራ መሆኑን ለማረጋገጥ ተችሏል።

ከዚህ ቀደም በነበረው ግጭት በተለያዩ ከተሞች ተመሳሳይ አይነት በሀሰት ህዝብን የማሸበር ስራ ሲሰራ፣ ህዝብን ለማስደንገጥ ብዙ ጥረቶች ሲደረጉና በዚህ ሳቢያ ብዙ መመሰቃቀል ሲፈጠር እንደነበር አይዘነጋም።

እስካሁን ድረስ በወልድያና በቀጠናው ባለው ሁኔታ ከወልድያ ከተማም ይሁን ከጅቡቲ ወደብ የሚነሱ አገር አቋራጭ ተሽከርካሪዎችን ከተለመደው የዕለት ተዕለት ጉዟቸው ያስተጓጎላቸው ሁኔታ እንዳልተከሰተ ከወልድያ ከተማ የተገኘው መረጃ ያሳያል።

በሌላ በኩል ደግሞ ፤ በወልድያ ዩኒቨርሲቲ ከሚማሩ ተማሪዎች ከወቅቱ ሁኔታ ጋር በተያያዘ ስጋት አድሮባቸው ግቢያቸውን ለቀው የወጡ፤ የትራንስፖርት አጥተውም በእግር የተጓዙ እንዳሉ ለማወቅ ችለናል።

አንዳንድ መልዕክት የላኩ የግቢው ተማሪዎች ካለው ሁኔታ ጋር በተያያዘ " ወደ መጡበት አካባቢ እንዲመለሱ እንዲደረግ ፤ አሁን በሰሜን ኢትዮጵያ ባለው ሁኔታ እነሱም ቤተሰብም ጭምር ጭንቀት ላይ በመሆኑና በዚህ ሁኔታ ትምህርትን በንቃት መከታተል ስለሚያስቸግር ተቋማቸው መፍትሄ እንዲፈልግላቸው ጠይቀዋል።

በተማሪዎቹ ስጋት ዙሪያ ከዩኒቨርሲቲው ምላሽ ለማግኘት እንጥራለን።