Get Mystery Box with random crypto!

ብዙዎች ዛሬን ማየት ናፍቀው ሳይመለከቷት አሸልበዋል፤ አንዳንዶችም ራዕያቸውን ሳያሳኩ ወደዛኛው ዓለ | Adoni Gospel channel

ብዙዎች ዛሬን ማየት ናፍቀው ሳይመለከቷት አሸልበዋል፤ አንዳንዶችም ራዕያቸውን ሳያሳኩ ወደዛኛው ዓለም ሔደዋል። እኛም ነገን ማየት እንናፍቃለን ነገ ላይ ከመድረሳችን በፊት ዛሬን በሚገባ ልንኖራት ይገባል። እኛ ዛሬ የሚጎበኘን ሰው አለ የሚጠይቃቸው ደጃቸው የሰው ኮቴ ከሰማ የሰንበቱ ምስኪኖች አሉ። በበዓል ቀን ሁሉም ሰው በቤቱ ከቤተሰቡ ጋር ሲሰባሰብ በብቸኝነትና በብዙ ናፍቆት ብቻቸውን የሚያሳልፉ አዛውንቶች አሉ። እነርሱን በማሰብ ካለን በመቁረስ አዲሱን አመት እንድንቀበል በፍቅር እጠይቃችኋለሁ።

በፍፁም ማንንም ሰው ለማሳቀቅ ታስቦ የተጠቀሰ የገንዘብ መጠን አይደለም። ይህንን ማድረግ የማይችል ሰው የአቅሙን ማድረግ ቢችል አጠራቅመን አስቤዛውን በመግዛት ለምስኪኖቹ ማድረስ እንችላለን። እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይባርካችሁ!

@adonigospel