Get Mystery Box with random crypto!

7ቱ_ቁርአን_ውስጥ_የተጠቀሱ_ከንቱ_ምኞቶች ⇦ ﴿يَٰلَيْتَنِى كُنتُ تُرَٰبًۢا﴾ ' | የነብዩ ☪ሠ,ዐ,ወ☪ ሀዲሶች

7ቱ_ቁርአን_ውስጥ_የተጠቀሱ_ከንቱ_ምኞቶች

⇦ ﴿يَٰلَيْتَنِى كُنتُ تُرَٰبًۢا﴾
" ዋ ምኞቴ! ምነው አፈር በሆንኩ "
[ሱረቱ ነበእ 40]

⇦ ﴿يَٰلَيْتَنِى قَدَّمْتُ لِحَيَاتِى﴾
" ዋ እኔ! ምነው በሕይወቴ (መልካምን ሥራን) ባስቀደምኩ ኖሮ "
[ሱረቱል ፈጅር 24]

⇦ ﴿يَٰلَيْتَنِى لَمْ أُوتَ كِتَٰبِيَهْ﴾
" ዋ ጥፋቴ! ምነው መጽሐፌን ባልተሰጠሁ "
[ሱረቱል ሃቀህ 25]

⇦ ﴿يَٰوَيْلَتَىٰ لَيْتَنِى لَمْ أَتَّخِذْ فُلَانًا خَلِيلًۭا﴾
" ዋ ጥፋቴ! እገሌን ወዳጅ አድርጌ ባልያዝኩ ኖሮ እመኛለሁ "
[ሱረቱል ፉርቃን 28]

‏⇦ ﴿يَٰلَيْتَنَآ أَطَعْنَا ٱللَّهَ وَأَطَعْنَا ٱلرَّسُولَا۠﴾
" ዋ ምኞታችን! አላህን በተገዛን መልክተኛውንም በታዘዝን ኖሮ "
[ሱረቱል አህዛብ 66]

⇦ ﴿يَٰلَيْتَنِى ٱتَّخَذْتُ مَعَ ٱلرَّسُولِ سَبِيلًۭا﴾
" ዋ ምኞቴ! ከመልክተኛው ጋር ቀጥተኛን መንገድ ይዤ በሆነ "
[ሱረቱል ፉርቃን 27]

⇦ ﴿يَٰلَيْتَنِى كُنتُ مَعَهُمْ فَأَفُوزَ فَوْزًا عَظِيمًۭا﴾
" ወይ ምኞቴ! ታላቅ ዕድልን አገኝ ዘንድ ከነሱ ጋር በሆንኩ "
[ሱረቱ ኒሳእ 73]

☞ ሁሉም የሟቾች ምኞት ናቸው
ቀብር ውስጥ ያሉት ሰዎች ምኞታቸው
ወደ ዱንያ አንዴ መጥተው ለአኺራቸው
ጥሩን ነገር መስራት ነው ...

☞ ቀብር ገብተህ/ሽ አንተም.አንቺም ይህን
ከምትመኝ/ኚ ነፍስህ/ሽ አካልህ/ሽ ውስጥ
እስካለች ድረስ ለአኺራህ አስቀድም/ሚ።

አላህ ሆይ! ከነዚህ ከንቱ ምኞቶች በእዝነትህ
ጠብቀን ያረብ!
ሼር ጆይን ተቀላቀሉ
https://t.me/Adnan567mh