Get Mystery Box with random crypto!

ቻይና ለWHO ቀልፍ መረጃ መከልከሏ ተሰማ! ቻይና የኮሮና አመጣጥ እየመረመረ ላለው የአለም አቀፉ | አድማስ ሬድዮ- Admas Radio

ቻይና ለWHO ቀልፍ መረጃ መከልከሏ ተሰማ!

ቻይና የኮሮና አመጣጥ እየመረመረ ላለው የአለም አቀፉ ጤና ድርጅት ቡድን ቁልፍ የሆኑ መረጃ መከልከሏን የመርማሪው ቡድን አባል ተናገሩ።

የስነህይወት ተመራማሪው ዶሚኒክ ድዋየር ቡድኑ መጀመሪያ ተመዘገቡ የተባሉ ህሙማንን ጥሬ መረጃ እንዲሰጧቸው መጠያቃቸውንና ይህም ደግሞ የተለመደ አሰራር መሆኑን ለሮይተርስ፣ዋል ስትሪት ጆርናልና ኒውዮርክ ታይምስ ተናግረዋል።

ነገር ግን በጠየቁት መሰረት ሳይሆን ያገኙት አጭር ማጠቃለያ ነው።

መርማሪዎቹ በአውሮፓውያኑ ታህሳስ 2019 በኮሮናቫይረስ የተያዙ የመጀመሪያ ህሙማን የተባሉ 174 ኬዞችን ጥሬ መረጃ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

መጀመሪያ ከተያዙ መካከል ቫይረሱ ተገኝቶበታል የተባለው የውሃን የስጋ ገበያ ጋር ንክኪ አላቸው የተባሉ ግማሾቹ የሚሆኑት ብቻ ናቸው።

"ለዚያም ነው ይህንን መረጃ እንዲሰጠን አጥብቀን እየጠየቅን ያለነው። ለምን መረጃውን አይሰጡንም? በዚህ ላይ ምንም ማለት አልችልም። ፖለቲካዊ ይሁን? አስቸጋሪ ስለሆነ ይሁን? ወይም መረጃው ሊኖርበት ያልቻለው ሌላ ምክንያት ይኖር ይሆን ወይ የሚለውን አላውቅም። ያው ማድረግ የሚቻለው የተለያዩ ግምቶችን ማስቀመጥ ነው" ብለዋል።

ቲያ ኮልሰን ፊሸር የተባሉ የመርማሪው ቡድን አባልና የወረርሽኝ ከፍተኛ ባለሙያ በበኩላቸው ምርመራው በከፍተኛ ሁኔታ "ጂኦ ፖለቲካል" መልክ እንዳለው ለኒውዮርክ ታይምስ ተናግረዋል።

"ቻይና ለምርመራው በሯን እንድትከፍት ምን ያህል ጫና እየተደረገባት እንደሆነ ሁላችንም የምናውቀው ነው። ከዚያም ጋር ተያይዞ ከፍተኛ ወቀሳዎች እየቀረቡ ነው" ብለዋል ተመራማሪዋ።

በሚቀጥለው ሳምንት ይወጣል ተብሎ በሚጠበቀው የመርማሪው ቡድን የመጨረሻ ሪፖርት የመረጃዎች ክልከላ እንደሚካተት ፕሮፌሰር ዶሚኒክ ይናገራሉ።

( BBC)
@admasradio