Get Mystery Box with random crypto!

ደቡብ አፍሪካ በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ የዘጋቻቸውን ድምበሮች ክፍት ልታደርግ ነው አዲሱ የኮሮና ቫ | አድማስ ሬድዮ- Admas Radio

ደቡብ አፍሪካ በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ የዘጋቻቸውን ድምበሮች ክፍት ልታደርግ ነው

አዲሱ የኮሮና ቫይረስ ዝርያ በደቡብ አፍሪካ ታይቷል መባሉን ተከትሎ ሀገሪቱ ከወር በፊት ድንበሮቿን ዝግ ማድረጓ ይታወሳል።

ደቡብ አፍሪካ በነገው እለት 20 ድንበሮችን ክፍት እንደምታደርግ አስታውቃለች።

በትላንትናው እለት ካቢኔው በጉዳዩ ዙሪያ በመምከር ነው ውሳኔው የተላለፈው።

ደቡብ አፍሪካ በሁለተኛው የወረርሽኙ መስፋፋት ወቅት ክፏኛ የተመታች ሲሆን አዲሱ ዝርያ እንዲገኝም ምክንያት ሁኗል።

ወደ 1.5ሚሊዮን ተጠቂዎች በሀገሪቱ ሲገኙ 47,000 ዜጎቿ ህልፈት መመዝገቡ ከአህጉሪቱ ቀዳሚው ያደርጋታል።

(ብስራት ራዲዮ)
@admasradio