Get Mystery Box with random crypto!

አይደለም ምኞቴ በእውቀቱ ስዩም አይደለም ምኞቴ ለምለም ኣንገትሽ ላይ፣ ከንዶቼን መጠምጠም ዳሌ | አድማስ ሬድዮ- Admas Radio

አይደለም ምኞቴ
በእውቀቱ ስዩም

አይደለም ምኞቴ
ለምለም ኣንገትሽ ላይ፣ ከንዶቼን መጠምጠም
ዳሌሽ ላይ መንሳፈፍ፣ ጭንሽ መሃል መስጠም

አይደለም ምኞቴ
ከንፈርሽን ማለብ ቀሚስሽን መግለብ
ከገላሽ ቆርሼ፣ ገላየን መቀለብ
ደረትሽን ማለም ጡትሽን መሳለም
በቁንጅናሽ ጅረት፣ ገነቴን ማለምለም
ዓላማዬ አይደለም።

ምኞቴን ልንገርሽ?
ካለሺበት ቦታ፣ ቀልቤን ማሰማራት
ወትሮ ካንቺ ጋራ፣ ቡና መጠራራት
ሰላም መገባበዝ፣ ትዝታ መጋራት

የጨለመ ፊቴን፤ ባይንሽ ጮራ ማድመቅ በቃላትሽ መስከን፣ በሣቅሽ መጠመቅ
በጎ መንፈስሽን፡ ካይንሽ ላይ መሻማት
ርጋታሽን ማጥመድ፡ ዝምታሽን መስማት።

@admasradio