Get Mystery Box with random crypto!

አዲስ መረጃ

የቴሌግራም ቻናል አርማ adissemereja — አዲስ መረጃ
የቴሌግራም ቻናል አርማ adissemereja — አዲስ መረጃ
የሰርጥ አድራሻ: @adissemereja
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 11.61K
የሰርጥ መግለጫ

መረጃዎች በትኩሱ ና ሳይዉሉ እንዲሁም ሳያድሩ በቻናሉ በኩል ይደርሳሉ
ለአስተያየት እና ለማስታወቂያ ስራዎች 👇👇

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-07-03 20:57:32
" አብዛኞቹ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለመውጫ ፈተና በተዘጋጁ የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አልተገኙም " - ባለስልጣን መ/ቤቱ

የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ከመውጫ ፈተና ጋር በተያያዘ አስጠንቅቋል።

የግል እና የመንግሥት ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሞዴል የቅድመ ምረቃ መውጫ ፈተና ከዛሬ ሰኔ 26/2015 ዓ.ም እስከ ሰኔ 29/2015 ዓ.ም መሰጠት ተጀምሯል፡፡

ይሁን እንጂ ባለሥልጣኑ ዛሬ ባደረገው ክትትል፤ አብዛኞቹ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለመውጫ ፈተና በተዘጋጁ የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እንዳልተገኙ ገልጿል።

የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ ተማሪዎቻቸው ሞዴል ፈተናውን እንዲወስዱ አለማድረጋቸውንም ባለሥልጣኑ ጠቁሟል፡፡

በመሆኑም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ በአቅራቢያቸው በሚገኙ ለመውጫ ፈተና በተዘጋጁ   የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎቻቸውን በመላክ ሞዴል ፈተና እንዲወስዱ ማድረግ እንዳለባቸው ባለሥልጣኑ አሳስቧል።
1.1K viewsedited  17:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-03 20:57:32
#DigitalLottery

አድማስ ዲጂታል ሎተሪ ዛሬ ወጥቷል።

3 ሚሊዮን ብር ባለዕድለኛ የሚያደርገው የዕጣ ቁጥር 0120773349 ሆኖ ወጥቷል።

3 ሚሊዮን ብር - 0120773349
1,200,000 ብር - 0121599869
800 ሺህ ብር - 0120855225
400 ሺህ ብር - 0122312400
250 ሺህ ብር - 0120231703

(ተጨማሪ የዕጣ ቁጥሮች ከላይ ተያይዘዋል)

በሌላ በኩል ደግሞ የአድማስ ዲጂታል ሎተሪ ሽልማት ማደጉ ተገልጿል።

ሽልማቱ ያደገው በደምበኞች አስተያየት መሆኑን የገለፀው ብሔራዊ ሎተሪ ፦
- የአንደኛው ዕጣ 4 ሚሊዮን ብር፣
- የሁለተኛው ዕጣ 2 ሚሊዮን ብር
- የሶስተኛው ዕጣ 1 ሚሊዮን ብር በማድረግ ከሰኔ 24 2015 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ መደረጉን አመልክቷል።
              
ምንጭ፦ ኢትዮ ቴሌኮም እና ብሔራዊ ሌተሪ አስተዳደር
1.0K viewsedited  17:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-01 16:26:12
በኬንያ በደረሰ የከባድ መኪና አደጋ ቢያንስ 48 ሰዎች ሞቱ!

በኬንያ እንቅስቃሴ በሚበዛበት መስቀለኛ መንገድ ላይ በደረሰ በአንድ የትራፊክ አደጋ ቢያንስ 48 ሰዎች መሞታቸውን ፖሊስ እና የዐይን እማኞች ገለጹ።አደጋው የተከሰተው ኮንቴኔር የጫነ ከባድ ተሽከርካሪ በምዕራባዊቷ ከተማ ኬሪቾ አቅራቢያ በሚገኝ ሎንዲያኒ መስቀለኛ መንገድ ላይ ከቁጥጥር ውጭ በመሆኑ እንደሆነ የአገሪቷ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

የፖሊስ አዛዡ ጄፍሪ ማዬክ እንደተናገሩት በአደጋው ከሞቱት በተጨማሪ ሌሎች 30 ሰዎች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል።የተጎጂዎች ቁጥርም ከተጠቀሰው በላይ ሊሆን እንደሚችል የፖሊስ አዛዡ ጨምረው ተናግረዋል።

ከዚህም በተጨማሪም አንድ ወይም ሁለት ሰዎች አሁንም በተገለበጠው ተሽከርካሪ ሥር ሳይሆኑ እንዳልቀሩም ስጋታቸውን ገልጸዋል።

የፈረንሳዩ የዜና ወኪል (ኤኤፍፒ)፣ ቶም ምቦያ ኦደሮ የተባሉ ሌላ የአካባቢው የፖሊስ መኮንን ጠቅሶ እንደዘገበው ወደ ኬሪቾ ሲጓዝ የነበረው ከባድ ተሽከርካሪ ፍጥነቱን መቆጣጠር አቅቶት ስምንት መኪኖችን፣ በርካታ ሞተርሳይክሎችን፣ በመንገድ ዳር የነበሩ ሰዎችን፣ በጎዳና ላይ እቃ ሲሸጡ የነበሩ እንዲሁም በሌላ ሥራ ላይ የነበሩ ሰዎችን ገጭቷል።

የዐይን እማኞችም ተሽከርካሪው በመንገዱ ላይ ተበላሽቶ የቆመውን አውቶብስ ለማለፍ ሲሞክር ከቁጥጥር ውጪ ወጥቶ አደጋው መከሰቱን ለኬንያ መገናኛ ብዙኃን ተናግረዋል።

Via BBC
2.0K viewsedited  13:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-01 15:22:48 የኦሮሚያ ክልል ለሚያስገነባው አዲስ ቤተ-መንግስት ማሰሪያ ከወር ደመወዛችን ላይ ተቆርጦብናል ሲሉ በሶማሊያ ሰላም ማስከበር የተሰማሩ ኢትዮጵያውያን ወታደሮች ቅሬታ አቀረቡ!

በአፍሪካ ህብረት የሶማሊያ የሽግግር ተልዕኮ (አትሚስ) ስር ሆነው በሰላም ማስከበሩ የተሰማሩ ኢትዮጵያውያን የሰራዊት አባላት ከሚከፍላቸው ወርሃዊ ደመወዝ ላይ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በአዲስ አበባ ከተማ ለሚያስገነባው ቤተ-መንግስት ማሰሪያ የሚሆን ኢትዮጵያውያን ወታደሮችን በወከሉ አመራሮች በኩል እንደተቆረጠባቸው ገለፁ።

በሶማሊያ ሰላም ማስከበር የተሰማሩ ኢትዮጵያውያን ወታደሮችን ጨምሮ በሀገር ውስጥ የሚገኙ የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላት በቦረና ድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ በሚል እያንዳንዳቸው ከደመወዛቸው ላይ 25% እንደተቆረጠባቸው ይታወቃል።

በዚህም ከተቆረጠብን 25% ገንዘብ ላይ በቦረና ድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ብቻ ሳይሆን በአማራ ክልል የተለያዩ አከባቢዎች ላይ ተጠልለው ለሚገኙ የእለት ደራሽ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖችም ይሰጥልን የሚል ጥያቄ ያቀረቡ የሰራዊቱ አባላት ታፍነው የተሰዱ ሲሆን የደረሱበት አለመታወቁንም የአማራ ድምፅ ከወራት በፊት የአይን እማኞችን ጠቅሶ መዘገቡ አይዘነጋም።

በአሁን ሰዓት በአፍሪካ ህብረት የሶማሊያ የሽግግር ተልዕኮ (አትሚስ) ስር ሆነው በሶማሊያ ሰላም ማስከበር የተሰማሩ ከሰባት ሺ በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ወታደሮች ይገኛሉ የተባለ ሲሆን ከባለፈው ወር ጀምሮ ከወርሀዊ ደመወዛቸው ላይ እየተቆረጠባቸው መሆኑን ነው የገለፁት።

የሰራዊት አባላቱ፡ "ግዳጁን ስንጨርስ ከሚከፈለን ብር ተጨማሪ በየወሩ ለኪስ 38 .33 $ እና ለሻይ ቡና ተብሎ ደግሞ 6.90 $  በድምሩ 45.23  ዶላር አትሚስ በኢትዮጵያ መንግስት በኩል ይከፈለን ነበር ነገር ግን አሁን ላይ ለኪስ ተብሎ ከሚሰጠን ገንዘብ ላይ 22 $ ለሻይ ቡና ተብሎ ከሚሰጠን ላይ ደግሞ 4.7$ በድምሩ 26.70 $ ተቆርጦብናል" ለቤተመንግስቱ ማሰሪያ ተቆርጦብናል ሲሉ ገልፀዋል።

 
1.8K viewsedited  12:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-01 15:22:48
በመውጫ ፈተና ወቅት የዲሲፕሊን ጥሰት የሚፈጽሙ ተፈታኞች የተለያዩ የዲሲፕሊን እርምጃ ሊወሰድባቸው እንደሚችል ተገለጸ።

ዩኒቨርሲቲዎች የትምህርት ማስረጃ መከልከልን ጨምሮ የተለያዩ የዲሲፕሊን እርምጃ መውሰድ እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

ሚኒስቴሩ ለመንግሥት ዩኒቨርስቲዎች እና ለግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በጻፈው ደብዳቤ እንዳሳወቀው፤ ተቋማቱ የዲሲፕሊን ጥሰት የሚፈጽሙ ተፈታኞች ላይ እንደ ችግሩ ስፋትና ጥልቀት የትምህርት ማስረጃ መከልከል፣ ድጋሚ ለፈተና እንዳይቀመጥ ማድረግ እና ሌሎች እርምጃዎችን መውሰድ ይችላል።

በሚኒስቴሩ የአካዳሚክ ጉዳዮች ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) በቀን ሰኔ23/2015 ዓ.ም ተፈርሞ የወጣውን ደብዳቤ ትክክለኛነት አረጋግጧል።
1.7K viewsedited  12:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-30 11:44:58
#ኦዲት

" በ86 የመንግስት መስሪያ ቤቶች 6 ቢሊዮን 838 ሚሊዮን 886 ብር ተመላሽ እንዲደረግ ሙያዊ አስተያየት ቢሰጥም 0.65 በመቶው ብቻ ነው ተመላሽ የሆነው " - የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት

የመንግስት ወጪ፣ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ክርስትያን ታደለ ፤ የመንግስት እና የሕዝብ ኃብት ለታለመለ ዓለማ እያዋለ ባለመሆኑ ሙስና እና ብልሹ አሰራር የብሔራዊ ስጋት እየሆነ ስለመጣ የፍትህ ተቋማት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ አሳሰቡ።

አቶ ክርስቲያን ታደለ ይህ ያሳሰቡት ከቀናት በፊት የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ለፓርላማው የ2014 ዓ/ም የፌዴራል መስሪያ ቤቶች የፋይናንስ ክንዋኔ ሪፖርት ባቀረበበት ወቅት ነው።

" የመንግስት እና የሕዝብ ኃብት ለታለመለት ዓለማ በትክክል እንዲውል ዋና ኦዲተር መ/ቤት እያደረገ ያለውን ጥረት የሚበረታታ ነው " ያሉት አቶ ክርስቲያን " የክዋኔ ኦዲት ስራዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ ጥራታቸውን የጠበቁ እንዲሆኑ በማድረግ የሪፖርቱን ተአማኒነት እና ተቀባይነትን ማረጋገጥ ይገባል " ብለዋል።

ዋና ኦዲተር የአስፈጻሚ መስሪያ ቤቶችን ዕቅድ እና ሪፖርት በወቅቱ በመገምገም የተሻለ ውጤት እንዲመጣ በይበልጥ ጥረቱን አጠናክሮ መስራት እንደሚጠበቅበት አስገንዝበዋል።

አቶ ክርስቲያን ፤ " አስፈጻሚው አካል ለኦዲት ግኝቶች ትኩረት ባለመስጠት የገንዝብ የመመለስ ምጣኔው በጣም ዝቅተኛ በመሆኑ፤ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ተቋማትን በመቆጣጠርና ተጠያቂነትን ማስፈን ይጠበቅበታል " ብለዋል።

" የመንግስት እና የሕዝብ ኃብት ለታለመለ ዓለማ እያዋለ ባለመሆኑ ሙስና እና ብልሹ አሰራር የብሔራዊ ስጋት እየሆነ የመጣ በመሆኑ የፍትህ ተቋማት ኃላፊነታቸውን በአግባቡ መወጣት አለባቸው " ሲሉም አሳስበዋል።

የፌደራል የዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ዋና ኦዲተር ወ/ሮ መሰረት ዳምጤ በበኩላቸው ፤  " በ86 የመንግስት መ/ ቤቶች 6 ቢለዮን 838 ሚሊዮን 886 ብር ተመላሽ እንዲደረግ ሙያዊ አስተያየት ቢሰጥም 0.65 በመቶው ብቻ ተመላሽ በመደረጉ የሚፈለገውን ለውጥ እያመጣ አይደለም።  " ሲሉ ተናግረዋል።

ዋና ኦዲተሯ ፤ በተወሰኑ የመንግስት እና የህዝብ ሃብት ባባከኑ የስራ ኃላፊዎች ላይ የገንዘብ ቅጣት እና የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ እርምጃ በገንዘብ ሚኒስቴር መወሰዱን ሲናገሩ ተደምጠዋል።

#HoPR

@tikvahethiopia
2.1K views08:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-30 11:44:58
" 3,114 ደንበኞቼ 21,592,811 ብር ብድር አግኝተዋል " - ኢትዮ ቴሌኮም

ኢትዮ ቴሌኮም ፤ ከ48 ሰዓት ባነሰ ጊዜ ውስጥ 3,114 ደንበኞቹ 21,592,811 ብር ብድር ማግኘታቸውን አሳወቀ።

ኢትዮ ቴሌኮም ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር በአጋርነት በ " ቴሌብር " አዳዲስ የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎቶች መጀመሩ ይታወቃል።

ከእነዚህ ከተጀመሩት አዳዲስ አገልግሎቶች መካከል አንዱ " እንደራስ " የተሰኘው አገልግሎት ነው።

ይህ አገልግሎት ፤ የግለሰብ ደንበኞች በ " ቴሌብር " እንደሚያከናውኑት የግብይት መጠን እስከ ብር 15,000 ድረስ የአነስተኛ ብድር አገልግሎት የሚሰጥበት ነው።

ዛሬ ኢትዮ ቴሌኮም ይፋ ባደረገው መረጃ በዚሁ አገልግሎት ከ48 ሰዓት ባነሰ ጊዜ 3,114 ደንበኞቹ 21,592,811 ብር ብድር ማግኘታቸውን አስታውቋል።

በሌላ በኩል ፤ ከ48 ሰዓት ባነሰ ጊዜ " ስንቅ " በተሰኘው አገልግሎት 2,035 ደንበኞቹ 1,719,754 ብር እንደቆጠቡ ገልጿል።

ይህ " ስንቅ " የተሰኘው አገልግሎት ደንበኞች ከወለድ ነጻ ወይም የተለያየ የወለድ ምጣኔ የሚታሰብባቸው የተንቀሳቃሽ እና የጊዜ ገደብ ተቀማጭ የቁጠባ አገልግሎት የሚያገኙበት ነው።

@tikvahethiopia
1.8K views08:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-29 17:06:02 #ETHIOPIA

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ ቤት በመንግሥት ተቋማት በርካታና ሰፋ ያሉ የኦዲት ክፍተቶችን በኦዲት ሪፖርት ማረጋገጡን አስታውቋል።

ባለፈው ፤ ማክሰኞ ለፓርላማው የፌዴራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ሪፖርት ቀርቦ ነበር።

ይህ ሪፖርት እንደሚያመለክተው የ2014 ዓ.ም. በጀት አፈጻጸምን በተመለከተ በተደረገው የኦዲት ሥራ 6 ተቋማት አስተያየት ለመስጠት ያልተቻለባቸው ሲሆኑ 19 ተቋማት ደግሞ የጎላ ችግር ያላባቸው ሆነው በመገኘታቸው " ተቀባይነት የሚያሳጣ " አስተያየት ተሰጥቶባቸዋል፡፡

#ሒሳባቸው_የጎላ_ችግር_ያለበት በመሆኑ ተቀባይነት የሚያሳጣ አስተያየት ከተሰጠባቸው ተቋማት መካከል ፦
- የፌዴራል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን፣
- የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ፣
- የኢንፎርሜሽንና መረብ ደኅንነት አገልግሎት
- የፌዴራል ፖሊስ
- ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ፣
- ጂንካ ዩኒቨርሲቲ፣
- ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ፣
- ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ፣
- ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ፣
- አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣
- ቦሌሆራ ዩኒቨርሲቲና የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ይገኙበታል፡፡

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት አስተያየት ለመስጠት አልቻልኩባቸውም ካላቸው ተቋማት መካከል ፦
- የሪፐብሊኩ የጥበቃ ኃይል፣
- አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ፣
- ብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት፣
- የቀድሞው የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት፣
- የአደጋ ሥጋትና ሥራ አመራር ኮሚሽን
- የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አሉበት፡፡

ከ1 ዓመት እስከ 6 ዓመት ዕድሜ ያለውና ለመንግሥት ገቢ መደረግ የነበረበት 13.4 ቢሊዮን ብር ውዝፍ የጉምሩክ #ቀረጥ እና #ታክስ ዕዳ መኖሩ በሪፖርቱ ተመላክቷል፡፡

• የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ 124 ሚሊዮን ብር፣
• የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር 65 ሚሊዮን ብር፣
• የአደጋ ሥጋትና ሥራ አመራር ኮሚሽን 64 ሚሊዮን ብር፣
• የሰመራ ጉምሩክ ቅርንጫፍ 7.9 ሚሊዮን ብር፣
• የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን 5.6 ሚሊዮን ብር፣
• ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ 4.8 ሚሊዮን ብር በድምሩ 307.5 ሚሊዮን ብር የተሟላ ወጪ ሳይቀርብ በወጪ መዝግበው የተገኙ መሥሪያ ቤቶች ናቸው።

በሌላ በኩል ፤ ከደንብ እና ከመመርያ ውጪ ያላግባብ ክፍያ ከፈጸሙ ተቋማት መካከል ፦

- የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ 30 ሚሊዮን ብር፣
- የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ 22 ሚሊዮን ብር፣
- የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ 11.8 ሚሊዮን ብር፣
- የመንግሥት ግዥና ንብረት ባለሥልጣን 7.6 ሚሊዮን ብር፣
- የቤተ መንግሥት አስተዳደር 6.5 ሚሊዮን ብር፣
- አርሲ ዩኒቨርሲቲ 6.1 ሚሊዮን ብር በድምሩ 134.2 ሚሊዮን ብር ተጠቃሽ ሲሆን ዩኒቨርሲቲ የመንግሥት የግዥ አዋጅ ደንብና መመርያ ያልተከተሉ ግዥዎችን የፈጸሙ 82 ተቋማት በሪፖርቱ የተጠቀሱ ሲሆን ከእነዚህ መሥሪያ ቤቶች የተገኘው የግዥን ሕግ የጣሰ ክፍያ 592.4 ሚሊዮን ብር ነው፡፡

ተቋማቱ ፦
> ጉምሩክ ኮሚሽን፣
> ጂንካ ዩኒቨርሲቲ፣
> ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ፣
> የኢንፎርሜሽን መረብና ደኅንነት አገልግሎት፣
> የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካደሚ
> ቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ ናቸው፡፡

" በተከፋይ ሒሳብ " ተመዝግበው የተገኙ ነገር ግን ዝርዝር ማስረጃ ባለማቅረቡ የሒሳቡን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ ያልተቻለባቸው ያሉ ሲሆን። ከእነዚህ ተቋማት መካከል ፦
- የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት 1 ቢሊዮን ብር፣
- የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት 583 ሚሊዮን ብር፣
- የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር 131.8 ሚሊዮን ብርና ጉምሩክ ኮሚሽን 96.5 ሚሊዮን ብር ይገኙበታል፡፡

#ከተደለደለላቸው_በጀት_በላይ_የተጠቀሙ መሥሪያ ቤቶችም በሪፖርቱ የተጠቀሱ ሲሆን፣ ከእነዚህ መካከል ፦
• ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ 358.9 ሚሊዮን ብር፣
• ዲላ ዩኒቨርሲቲ 125 ሚሊዮን ብር፣
• ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ 139.9 ሚሊዮን ብር፣
• ዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ 166.7 ሚሊዮን ብር፣
• አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ 113 ሚሊዮን ብር ናቸው፡፡

የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በ2014 የተፈቀደላቸውን በጀት መጠቀም ሲገባቸው ባለመጠቀማቸው የተገኘው አጠቃላይ ገንዘብ 35 ቢሊዮን ብር መሆኑ በሪፖርቱ ተጠቅሷል፡፡

በጀት ሥራ ላይ ካላዋሉ መሥሪያ ቤቶች ፦
- የመስኖና ቆላማ ሚኒስቴር 8.9 ቢሊዮን ብር፣
- የገንዘብ ሚኒስቴር 6.3 ቢሊዮን ብር፣
- የጤና ሚኒስቴር 3 ቢሊዮን ብር፣
- ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን 1.2 ቢሊዮን ብር፣
- የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር 1 ቢሊዮን ብር፣
- የትምህርት ሚኒስቴር 915 ሚሊዮን ብር፣
- የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር 599 ሚሊዮን ብር ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡

ያንብቡ : https://telegra.ph/Reporter-Newspaper-06-29
2.0K viewsedited  14:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-29 17:06:02
#Update

በኦሮሚያ ክልል፣ " አሊ ዶሮ " ላይ ከታገቱት ሹፌሮች እና ረዳቶች መካከል በአጋቾች የተጠየቀውን ብር ከፍለው የተለቀቁ ስለመኖራቸው ቪኦኤ ሬድዮ ቤተሰቦቻቸውን ዋቢ በማድረግ ዘግቧል።

ቃላቸውን የሰጡ አንድ ወላጅ ፤ ልጃቸውን 1 ሚሊዮን ብር ከፍለው ከእገታው እንዳስለቀቁ አመልክተዋል።

ከታገቱት አሽከርካሪዎች ውስጥ ሰባቱ፣ የምሥራቅ ጎጃም ዞን ማቻከል ወረዳ ዐማኑኤል ከተማ ወጣቶች እንደሆኑ የጠቆሙት እኚህ አባት፣ ከልጃቸው ጋራ አምስቱ እንደተለቀቁ አክለው ገልጸዋል።

ከቀናት በፊት ልጃቸው መታገቱንና 1 ሚሊዮን ብር ቢከፍሉ እንደሚለቁላቸው፣ በስልክ ያነጋገራቸው አካል መኖሩን የተናገሩት እኚኹ አባት በተጠየቁት መሠረት ከተለያየ ቦታ ያሰባሰቡትን ገንዘብ በማዳበሪያ አስረው በማድረስ ልጃቸውን እንዳስለቀቁ አስረድተዋል።

የታጋች ቤተሰቦች የእገታ ድርጊቱን በመፈፀም የከሰሱት መንግሥት " ሸኔ " እያለ የሚጠራውን አካል / የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት / ነው።

ጉዳዩን በተመለከተ እስካሁን በመንግሥት በኩል የተሰጠ ማብራሪያ የለም።

የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ዓለም አቀፍ ቃል አቀባይ እንደሆነ የገለፁት ኦዳ ተርቢ ፤ ታጣቂዎቻቸው እንዲህ አይነቱን ድርጊት እንዳልፈጸሙ ገልጸው፣ በተጠቀሰው አካባቢ፣ የተለያዩ ኃይሎች እየተንቀሳቀሱ እንደሚገኙ ለቪኦኤ ሬድዮ ተናግረዋል።

ከሳምንት በፊት በኦሮሚያ ክልል " አሊ ዶሮ " ላይ ወደ 30 የሚደርሱ ሹፌሮች እና ረዳቶቻቸው በታጣቂዎች መታገታቸው ፤ ከእገታው በኃላም ወደ ቤተሰቦቻቸው እየተደወለ እስከ 1 ሚሊዮን ብር መጠየቁን የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መጠቆማቸው የሚዘነጋ አይደለም።
1.8K viewsedited  14:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-28 15:06:01
ከፓኪስታን - መካ በእግር . . .

የፓኪስታኑ ተማሪ ኡስማን አርሻድ ለሃጅ ሃይማኖታዊ ጉዞ ጃንጥላ እና በጀርባ ላይ የሚታዘል ሻንጣ ይዞ 4,000 ኪሎ ሜትር በእግሩ በመጓዝ ሳዑዲ አረቢያ መካ ደርሷል።

አቅሙ ያለው ሙስሊም በሕይወት ዘመኑ ቢያንስ አንድ ጊዜ ለማሳካት የሚመኘውን የሃጅ ጉዞ ኡስማን አርሻድ በእግሩ በመጓዝ አውን አድርጎታል።

ጉዞውን የጀመረው ፤ ከትውልድ ከተማው የፓኪስታኗ ኦካራ ሲሆን፣ ስድስት (6) ወራትን ተጉዞ ነው መካ የደረሰው።

ቅዱሱን የሃይማኖታዊ ጉዞ በእግሩ የፈጸመው ኡስማን በሺዎ የሚቆጠሩ ኪሎ ሜትሮች በእግር በመጓዝ ሳዑዲ አረቢያ መካ ለመድረስ የተለያዩ አገራትን ማለትም ኢራን ፣ የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስን (UAE) አቆራርጧል።

ኡስማን አርሻድ ስለ ጉዞው ምን አለ ?

" ሁሉም ሙስሊም በሕይወት ዘመኑ አንድ ጊዜ #መካ መጥቶ የፈጣሪን ቤት ማየት ይነኛል።

የእኔ ምኞች ደግሞ በእግር ተጉዤ የፈጣሪንና የነብዩን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)  መስጂድ ማየት ነበር።

ጉዞው ከባድ ነበር የኢራቅ ቪዛን ማግኘት ስላልቻልኩ ከኢራቅ ወደ ተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ለመግባት ጀልባ ነበር የተጠቀምኩት።

አንዳንድ ችግሮች ነበሩ መጥፎ የሆነ የአየር ሁኔታ እና በጉዞው ምክንያት እግር መቁሰል አጋጥሞኛል።

አብዛኛው መንገድ ሰው የማይታይበት እና መንደርም ሆነ ከተማ ያልነበረው ነው።

ጉዞዬን እንድቀጥል ያደረጉኝ መንገድ ላይ ያገኘኋቸው ሰዎች ናቸው። ረጋ ብዬ ጉዞዬን መጨረስ እንዳለብኝ አበረታተውኛል።

ባገኘሁበት ቦታ ነበር የማድረው፣ በመስጂድ  ፣ በፍተሻ ጣቢያ ፣ በሆቴል፣ ወይም እንዳርፍ ከፈቀዱልኝ ሰዎች ጋር ሊሆን ይችላል። አማራጭ ሳጣ ድንኳን ጥሬ በረሃ ላይ ብዙ ጊዜ አድሬያለሁ።

በመጨረሻም ከ6 ወር በኃላ ያሰብኩበት ደርሻለሁ።

ምንም ነገር ማድረግ ብትፈልጉ በራሳችሁ ተማመኑ።  ማንኛውንም ጉዞ እንድትፈፅሙ ፈጣሪ ይረዳችኋል። "

Via BBC - Al Jazeera

@tikvahethiopia
2.1K views12:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ