Get Mystery Box with random crypto!

ህወሓት የቅድመ ግጭት ጩኸቱን እያሰማ ነው ሲል የመከላከያ ሚኒስቴር ገለፀ ህወሓቶች 'የሰላም ድ | አዲሰ ነገር አለም አቀፍ ዜና 🌎🌏🌍

ህወሓት የቅድመ ግጭት ጩኸቱን እያሰማ ነው ሲል የመከላከያ ሚኒስቴር ገለፀ

ህወሓቶች "የሰላም ድርድሩ ቴክኒካል ፈርሷል፣ መከላከያ ኃይሉን እያስጠጋ ነው፣ መከላከያ በከባድ መሳሪያ እየደበደበን ነው፣ ከላይ እስከታች የዕዝ ሰንሰለቱን ጠብቆ እየተፈፀመ ያለ ጥቃት ነው" ወዘተ በማለት የቅድመ ግጭት ጩኸታቸውን በስሙልኝ ፕሮፖጋንዳቸው እያስተጋቡ ይገኛሉ ሲል መከላከያ ሚኒስቴር ገልጿል።

ሚኒስቴሩ ዛሬ ባወጣው መግለጫ የሠራዊቱን ወቅታዊ ሁኔታ ባልተረጋገጡ፣ ባልተገቡ መረጃዎችና አሉባልታዎች የመዘገብ ወይም የማራገብ አሉታዊ ሙከራዎችም በአስቸኳይ እንዲቆሙ ሲል በጥብቅ አሳስቧል።

@Adisnews
@Adisnews