Get Mystery Box with random crypto!

'የ2014 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከመስከረም 30 /2015 ዓ/ም ጀምሮ በ2 ዙር እንዲ | አዲሰ ነገር አለም አቀፍ ዜና 🌎🌏🌍

"የ2014 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከመስከረም 30 /2015 ዓ/ም ጀምሮ በ2 ዙር እንዲሰጥ ታቅዷል"

ትምህርት ሚኒስቴር

የ2ዐ14 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ ፈተና በዩኒቨርስቲዎች እንዲሰጥ መወሰኑ ይታወቃል፡፡

ፈተናው ከመስከረም 30 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ #በሁለት_ዙር እንዲሰጥ መታቀዱን በትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ተፈርሞ ለ42 ዩኒቨርሲቲዎች በተላከውን እና ቲክቫህ ኢትዮጵያ ትክክለኛነቱን ባረጋገጠው ደብዳቤ መመልከት ችለናል።

በዚሁ መሠረት ከመስከረም 28 እስከ ጥቅምት 17 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ዩኒቨርስቲዎች ፦

1. ምንም አይነት የመደበኛ ተማሪ በግቢ እንዳይኖር እንዲያደርጉ፤

2. በቀጣይ በሚገለጸው ተማሪ ቁጥር ልክ ምግብ እንዲቀርብ ዝግጅት እንዲያደርጉ፤

3. ለፈተናዎች ማቆያ ቦታ እንዲዘጋጅ እና

4. የፈተናውን አሰጣጥና ደህንነት የሚቆጣጠር በፕሬዚዳንት የሚመራ ዋና ግብረ-ኃይልና በየካምፓሶቹ በዲን /ካምፓስ ኃላፊ የሚመራ ንዑስ ግብረ-ኃይል እንዲያደራጁ መልዕክት ተላልፎላቸዋል።

ዩኒቨርሲቲዎች የ2ዐ15 የአካዳሚክ ካላንደር የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ ፈተና ወቅት (ከመስከረም 28 - ጥቅምት 17) ታሳቢ በማድረግ እንዲያዘጋጁ የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ አሳስበዋል።

@Adisnews
@Adisnews