Get Mystery Box with random crypto!

ባንኮች የደንበኞቻቸውን መረጃ እንዲያሟሉ ተጨማሪ የሁለት ወር ጊዜ ተሰጣቸው የኢትዮጵያ ብሔራዊ | አዲሰ ነገር አለም አቀፍ ዜና 🌎🌏🌍

ባንኮች የደንበኞቻቸውን መረጃ እንዲያሟሉ ተጨማሪ የሁለት ወር ጊዜ ተሰጣቸው

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በፋይናንስ ውስጥ ያለውን ውንብድና ለመቆጣጠር ለባንኮች አዲስ የደንበኛ ማንነት እንዲያዘጋጁ ያስቀመጠውን የግዜ ገደብ ማራዘሙን ተገልጿል። ምንጩ ያልታወቀና የህገወጥ ገንዘብ ለመከታተል ወይም በተጭበረበሩ ሰነዶች የሚገላበጠውን የገንዘብ ዝውውር ለማስቀረት ሁሉም ባንኮች ደንበኞቻቸው እነማን እንደሆኑ እንዲያጣሩ ብሔራዊ ባንክ መመርያ ማውጣቱ ይታወሳል።

የተሰጠው ቀን ገደብ በመጠናቀቂያው ሰዓት ጥድፊያና ግርግር ታይቷል፡፡ በዚህም ምክንያት የብሔራዊ ባንክ ባንኮች የደንበኛቸውን መረጃ እንዲሰንዱ ተጨማሪ የሁለት ወር ግዜ መስጠቱን ገልጿል።

@Adisnews
@Adisnews
@Adisnews