Get Mystery Box with random crypto!

ከ1500 በላይ የሸኔ አባላት ተደምስሰዋል፣ ከ7500 በላይ የአሸባሪው ሸኔ እና ህወሀት አባላት በ | አዲሰ ነገር አለም አቀፍ ዜና 🌎🌏🌍

ከ1500 በላይ የሸኔ አባላት ተደምስሰዋል፣ ከ7500 በላይ የአሸባሪው ሸኔ እና ህወሀት አባላት በተለያዩ የኦሮሚያ አከባቢዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል

የኦሮሚያ ክልል ኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ በዛሬው እለት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

በዚህም በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች ከህዝብ ጋር በመተባበር የፀጥታ ኃይሉ በወሰደው የተቀናጀ ዘመቻ ከ1500 በላይ የሸኔ የሽብር ቡድን አባላት ተደምሰዋል ብለዋል።

በከተሞች ውስጥ የተደራጁ የአሸባሪው ሸኔና ህወሓት የሎጂስቲክ እንዲሁም የመረጃ ስራ የሚሰሩ ከ7500 በላይ አባላቶቻቸው በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው በህግ እየታየ ስለመሆኑም በመግለጫው ተገልፆል። ሸኔን እስከ መጨረሻው በመደምሰስ የኦሮሚያ ክልልና የኢትዮጵያን ሰላም የማረጋገጥ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላልም ብለዋል።

@Adisnews