Get Mystery Box with random crypto!

ተቃዋሚ ፓርቲዎች የፌደራል መንግስት የሚያደርጋቸው ድርድሮች ግልፅነት መጉድል እንዳሳሰባቸው ገለፁ | አዲስ ዘይቤ ~ Addis Zeybe

ተቃዋሚ ፓርቲዎች የፌደራል መንግስት የሚያደርጋቸው ድርድሮች ግልፅነት መጉድል እንዳሳሰባቸው ገለፁ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) ብልፅግና ፓርቲ ኢትዮጵያን መምራት ከጀመረ አንስቶ በተለያየ ጊዜ የሚፈፅሙ ድርድሮች ግልፅነት መጉደል እንዳሳሰበው ገለፀ።

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ትላንት ሚያዝያ ሚያዝያ 24፣ 2015 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ “በጦርነቱ ወቅት የተከፈለውን ዋጋ በማይመጥን ደረጃና አግባብ” ብሎ በገለፀው ሁኔታ የመልሶ ማቋቋም ስራ እና ድኅረ-ጦርነት ላይ በመንግስት በኩል “ግልፅነት የሌለው የፖለቲካ እንቅስቃሴ በአማራ ሕዝብ ላይ ከፍተኛ ቅሬታ እና ስጋት መፍጠሩን መተማመን ያስፈልጋል” ብሏል።

ኢዜማ በመግለጫው “መንግስት ከሕወሓት ጋር ድርድር አድርጌ ሰላም አውርጃለሁ ባለበት የፕሪቶሪያው ስምምነት እንደ ስምምነቱ ያልተፈፀሙ ጉዳዮችን አስተውለናል” ብሎ ሂደቱ ምን ላይ እንደሆነ አሁንም ድረስ በግልፅ አለመታወቁ በፓርቲው እና ሌሎችም አካላት ላይ ቅሬታ መፍጠሩን ገልጿል። ዝርዝር ዘገባውን ያንብቡ - https://am.addiszeybe.com/featured/addis-ababa/%E1%8B%9C%E1%8A%93/politics-am/current-affairs-am/The-opposition-parties-said-that-they-were-concerned-about-the-lack-of-transparency-in-the-negotiations-of-the-federal-government