Get Mystery Box with random crypto!

የብልፅግና መንግስት ከዚህ ቀደም ከኦነግ ጋር ሲስማማ የተፈጠረው ችግር እንዳይደገም ሲል ኢዜማ አሳ | አዲስ ዘይቤ ~ Addis Zeybe

የብልፅግና መንግስት ከዚህ ቀደም ከኦነግ ጋር ሲስማማ የተፈጠረው ችግር እንዳይደገም ሲል ኢዜማ አሳሰበ

ሚያዝያ 24፤ 2015 ዓ.ም.

(አዲስ ዘይቤ፤ አዲስ አበባ) የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ከኤርትራ ወደ ሀገር ቤት ከገባ በኋላ "በስምምነቱ መሠረት አልተፈፀመልኝም ሲል እንደነበረው" ተመሳሳይ ችግር እንዳይፈጠር ሲል የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) አሳሰበ።

አሁንም ሰላም የሰፈነባት እና ዴሞክራሲያዊ ኢትዮጵያን ለማየት ከፈለግን የትኛውም ዓይነት የሃሳብ ልዩነቶች ከአፈሙዝ ተላቀው ወደ ጠረጴዛ ዙሪያ መቅረብ እንዳለባቸው ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እናምናለን ያለው ኢዜማ፤ ባለፉት አምስት ዓመታት የተደረጉ ድርድሮች ግልፅነት ሲጎድላቸው ተመልክተናል ሲል አስታውቋል።

ኦነግ ከዚህ ቀደም ያቀረበው ዓይነት ሰበብ እንዳይኖር በተለይ ከሕወሓት ጋር ከተደረገው ስምምነት ልምዶችን መነሻ ማድረግ እንደሚገባ ኢዜማ ገልጿል።

ፓርቲው አክሎም የድርድሩን ሂደትና ስምምነቱን በተመለከተ ለህዝቡ ግልፅ መረጃ በመስጠት እነማን እየተሳተፉ ነው፣ የስምምነቱን ይዘት፣ እንዴት እንደሚፈፀም እና ተግባራዊነቱን በማሳየት ከተጨማሪ ውዥንብርና ትርምስ ማኅበረሰቡን እንዲጠበቅ አሳሰቧል።