Get Mystery Box with random crypto!

የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ተማሪዎቹ በስልክ ሪፖርት እንዲያደርጉ አሳሰበ በሰሜኑ ጦርነት ውድመት | አዲስ ዘይቤ ~ Addis Zeybe

የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ተማሪዎቹ በስልክ ሪፖርት እንዲያደርጉ አሳሰበ

በሰሜኑ ጦርነት ውድመት የደረሰበትና ከ35 ሺ በላይ ተማሪዎችን በማስተማር ላይ የነበረው መቀሌ ዩኒቨርሲቲ ከጦርነቱ በኋላ ስራ ለማስጀመር እየሰራ መሆኑን አስታውቋል።

በፌደራል መንግስት እና በትግራይ ኃይሎች መካከል በነበረው ጦርነት ሳቢያ ለዓመታት የመማር ማስተማር ስራውን ያቋረጠው መቀሌ ዩኒቨርሲቲ አሁን የጥገና እና የመረጃ ማጣራት ስራዎችን እየሰራሁ ነው ብሏል።

በጥር ወር 2013 ዓ.ም መከላከያ ሰራዊት መቀሌ መግባቱን ተከትሎ በጊዜያዊ አስተዳደር አማካኝነት መደበኛ ትምህርት ማስተማር ጀምሮ የነበረው ዩኒቨርሲቲው የጦርነቱን ማገርሸት ተክትሎ የመማር ማስተማር ሂደቱ እንዲቋረጥ የግድ ሆኗል።

የዩኒቨርሲቲው የትምህርት ክፍል ምክትል ኃላፊ ሳሙኤል ክፋሌ (ዶ/ር) ትምህርት ከመጀመሩ በፊት የጥገና፣ የበጀት ማስተካከል እና የአእምሮ ማነቃቂያ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ለአዲስ ዘይቤ ገልፀዋል።

ዝርዝሩን ያንብቡ - https://am.addiszeybe.com/featured/mekelle/current-affairs-am/mekele-university-urged-its-former-students-to-report-by-phone