Get Mystery Box with random crypto!

በሀዲያ ዞን በፀጥታ ኃይሎች በተወሰደ እርምጃ በሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱ ተሰማ በደቡብ ክልል ሀዲ | አዲስ ዘይቤ ~ Addis Zeybe

በሀዲያ ዞን በፀጥታ ኃይሎች በተወሰደ እርምጃ በሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱ ተሰማ

በደቡብ ክልል ሀዲያ ዞን የሚገኙ የመንግስት መስሪያ ቤት ሰራተኞች ካለፈው ጥር ወር ጀምሮ ደመወዝ አልተከፈለንም በሚል ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ ከጀመሩ ሁለተኛ ቀናቸውን አስቆጥረዋል፡፡

በዞኑ ባደዋቾ ወረዳ እና ሾኔ ከተማ ከ ሰባት ሰዓት በላይ በተደረገዉ ሰላማዊ ሰልፍ አዲስ አበባን ከአርባ ምንጭ  የሚያገናኘዉ መንገድ ዝግ ሆኖ ሲውል ከምሽቱ 12 ሰዓት በኋላ ሰልፈኞችን ለመበተን በዞኑ ፓሊሶች ተኩስ መከፈቱን የአዲስ ዘይቤ ምንጮች ገልጸዋል።

በሾኔ ከተማ ሰልፉን ለመበተን በተወሰደዉ እርምጃ አንድ የፓሊስ አባል በእራሱ ተኩሶ ጉዳት ሲደርስበት ሶስት ሰዎች ድብደባ ተፈፅሞባቸዉ በከተማዋ ወደሚገኘዉ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል መወሰዳቸዉን ምንጮቻን ተናግረዋል።
ዝርዝሩን ያንብቡ - https://am.addiszeybe.com/featured/hawassa/current-affairs-am/It-was-heard-that-people-were-injured-in-the-action-taken-by-the-security-forces-in-Hadiya-Zone