Get Mystery Box with random crypto!

የባህር ዳር ከተማ ሁሉም መንገዶች በአሁኑ ሰዓት ተዘግተዋል ሚያዝያ 3፤ 2015 ዓ.ም. (አዲስ | አዲስ ዘይቤ ~ Addis Zeybe

የባህር ዳር ከተማ ሁሉም መንገዶች በአሁኑ ሰዓት ተዘግተዋል
ሚያዝያ 3፤ 2015 ዓ.ም.

(አዲስ ዘይቤ፤ ባህር ዳር) በአማራ ክልል ከልዩ ኃይል አባላት ወደ ፌደራል የፀጥታ መዋቅር መግባት ጋር ተያይዞ የተከሰተው ውጥረት ቀጥሏል።

በዛሬው እለት የክልል መስተዳደሩ መቀመጫ በሆነችው ባህር ዳር ከተማ ሁሉም መንገዶች መዘጋታቸውን አዲስ ዘይቤ ተመልክታለች። በተጨማሪም የትራንስፖርት አገልግሎት ሙሉ ለሙሉ የተቋረጠ ሲሆን የንግድ ድርጅቶች እና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ዝግ ሆነዋል።
በተቀጣጠለ ጎማ የተዘጉ መንገዶችን የእሳት አደጋ መከላከያ ተሽከርካሪ እያጠፋም ይገኛል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ከቦታው በፍጥነት ከፈለጉ አዲስ ዘይቤ ቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ ።
Telegram - https://t.me/AddisZeybe