Get Mystery Box with random crypto!

በአማራ ክልል መራዊ ከተማ ትላንት አንድ ግለሰብ በፀጥታ ኃይሎች ሲገደል ሁለት ሰዎች ቆስለዋል ተባ | አዲስ ዘይቤ ~ Addis Zeybe

በአማራ ክልል መራዊ ከተማ ትላንት አንድ ግለሰብ በፀጥታ ኃይሎች ሲገደል ሁለት ሰዎች ቆስለዋል ተባለ
ሚያዝያ 2፤ 2015 ዓ.ም.

(አዲስ ዘይቤ፤ ባህር ዳር) በትላንትናው እለት ከጃዊ አካባቢ ወደ ባህር ዳር ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የመከላከያ ሠራዊት አባላትን አታልፉም ብለው በከለከሉ የአካባቢው ነዋሪዎች መካከል ግጭት ተፈጥሮ አንድ ሰው መገደሉን አዲስ ዘይቤ ከስፍራው አረጋግጣለች።

አባተ መስፍን የተባለው ግለሰብ የአምስት ልጆች አባት ሲሆን የመራዊ ከተማ ነዋሪ ነበር። በትላንትናው እለት ከሰዓት የቤቱ በር አካባቢ በቆመበት በፌድራል መንግስት የፀጥታ ሀይሎች መገደሉን የአዲስ ዘይቤ ምንጮች ከስፍራው ማረጋገጥ ችለዋል።

በተጨማሪም ሁለት ሰዎች ላይ የመቁሰል ጉዳት ደርሷል ሲሉ ነዋሪዎች ገልፀዋል።
ወቅታዊ መረጃዎችን በፍጥነት ከፈለጉ አዲስ አበባን ጨምሮ ከ13 በላይ የኢትዮጵያ ከተማዎች ዘገባዎችን የምታቀርበውን አዲስ ዘይቤን ይወዳጁ ::
Telegram - https://t.me/AddisZeybe
Twitter - https://twitter.com/AddisZeybe
Facebook - https://bit.ly/2SeU3Ev
Website - https://addiszeybe.com/
ስልክ +251954903850
ኢሜይል info@addiszeybe.com