Get Mystery Box with random crypto!

#አሁን ከደብረ ብርሃን ወደ ሸኖ የሚወስደው በተቃውሞ ሰልፈኞች ተዘጋ ሚያዚያ 1፤ 2015 ዓ.ም. | አዲስ ዘይቤ ~ Addis Zeybe

#አሁን
ከደብረ ብርሃን ወደ ሸኖ የሚወስደው በተቃውሞ ሰልፈኞች ተዘጋ

ሚያዚያ 1፤ 2015 ዓ.ም.

(አዲስ ዘይቤ፤ አዲስ አበባ) በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ከደብረ ብርሃን ከተማ ወደ  ሸኖ ያለው አገር አቋራጭ መንገድ በተቃውሞ ሰልፈኞች ተዘግቷል።

በደብረ ብርሃን የሚገኙ የአዲስ ዘይቤ ምንጮች እንደገለጹት በደብረ ብርሃን ከአማራ ፖሊስ አድማ ብተና ውጪ የልዩ ኃይል በስፍራው አለመኖሩን ገልጸው የተለየ ነገር አልተስተዋለም ብለዋል።

በሸኖ ከተማ በኩል የተዘጋው መንገድ በተደጋጋሚ ጊዜ ከአማራ ክልል የሚመጡ ተጓዦች ወደ አዲስ አበባ እንዳይገቡ ሲከለከሉ የነበረበት እና ከፍተኛ ቅሬታ የሚነሳበት እንደነበር ይታወሳል።

ዛሬ ረፋድ በአማራ ክልል የተለያዩ ከተሞች የተቃውሞ ሰልፍ  እየተደረገ ይገኛል።