Get Mystery Box with random crypto!

በቆቦ ከተማና ዙሪያዋ በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትና በፋኖ መካከል የጥይት ተኩስ መከፈቱን ነዋሪዎች | አዲስ ዘይቤ ~ Addis Zeybe

በቆቦ ከተማና ዙሪያዋ በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትና በፋኖ መካከል የጥይት ተኩስ መከፈቱን ነዋሪዎች ገለፁ

ሚያዝያ 1፤ 2015 ዓ.ም.

(አዲስ ዘይቤ፤ ጎንደር) የራያ ቆቦ ከተማ ነዋሪዎች ዛሬ ሚያዚያ 01 ቀን 2015 ዓ.ም ከ 5 ሰዓት አካባቢ ጀምሮ የመከላከያ ሰራዊት ከፋኖ እና የአማራ ልዩ ሃይል ጋር ተኩስ መለዋወጣቸውን ለአዲስ ዘይቤ ገለፁ።

በተያያዘ ቆቦና ወልዲያ አካባቢዎች ላይ መንገዶች እየተዘጉ ይገኛሉ።

ከመጋቢት 29 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እስከዛሬ ሚያዚያ 01 ቀን ድረስ መንገድ በመዝጋት በከተማዋ ምንም አይነት የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ እንዳይኖር እንደተደረገ ነዋሪዎች አክለዋል።