Get Mystery Box with random crypto!

የጥንቃቄ መልዕክት ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ AMN - መጋቢት 10/2016 ዓ.ም አጭበርባሪዎች | AMN-Addis Media Network

የጥንቃቄ መልዕክት ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

AMN - መጋቢት 10/2016 ዓ.ም

አጭበርባሪዎች ሰሞኑን ከሲስተም ጋር ተያይዞ የተፈጠረውን ችግር እንደ አጋጣሚ ለመጠቀም ሙከራ በማድረግ ላይ መሆናቸውን እንደደረሰበት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አስታውቋል።

እነዚህ አጭበርባሪዎች በአብዛኛው ከባንክ የደወሉ በማስመሰል “የተዘጋ ሒሳብችሁን እንክፈትላችሁ”፤ “ሒሳባችሁ እንዳይዘጋ የምንልክላቹሁን ኮድ አስገቡ” የሚል የማጭበርበሪያ ዘዴ በመጠቀም የዘረፋ ሙከራ በማድረግ ላይ ናቸው ብሏል ባንኩ።

ነገር ግን ባንኩ ስልክ ደውሎ ስለ ሒሳብ መረጃ የሚጠይቅበት፣ ሒሳብ የሚከፍትበትም ሆነ የሚዘጋበት አሠራር እንዲሁም ደንበኞች እንዲጠቀሙበት የሚልከው ምንም ዓይነት ኮድ አለመኖሩን ደንበኞች እንዲረዱ አስገንዝቧል።

በመሆኑም ማንኛውም የባንኩ ደንበኛ መሰል ሁኔታ ሲገጥመው ምንም ዓይነት እርምጃ ከመውሰድ በመቆጠብ በአቅራቢያው ወደሚገኝ ቅርንጫፍ በመሔድ አሊያም በ951 የባንኩ የደንበኞች ጥሪ ማዕከል በመደወል ስለሁኔታው መረጃ መጠየቅ እንዳለበት አሳስቧል።

#Addisababa
#Ethiopia

ትክክለኛውን የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዲጂታል ሚዲያ የትስስር አውታሮችን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑን!

https://linktr.ee/AddisMediaNetwork