Get Mystery Box with random crypto!

የቀድሞው የባርሴሎና ተጫዋች ዳኒ አልቬስ በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ጥፋተኛ ተባለ AMN - የካ | AMN-Addis Media Network

የቀድሞው የባርሴሎና ተጫዋች ዳኒ አልቬስ በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ጥፋተኛ ተባለ

AMN - የካቲት 14/2016 ዓ.ም

የቀድሞው የባርሴሎና እና የብራዚል ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች ዳኒ አልቬስ በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ጥፋተኛ በመባሉ የ4 ዓመት ከ6 ወር እስራት ተፈረደበት።

የ40 ዓመቱ ዳኒ አልቬስ እ.አ.አ ታኅሣሥ 31 ቀን 2022 ባርሴሎና ውስጥ በሚገኝ አንድ የምሽት ክለብ ውስጥ በአንዲት ሴት ላይ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል በመፈፀም ክስ ቀርቦበት በፍርድ ሒደት ላይ ነበር።

የፍርድ ሒደቱን ሲከታተል የቆየው አንድ የስፔን ፍርድ ቤትም ዳኒ አልቬስ ጥፋተኛ ሆኖ አግኝቼዋለሁ በሚል የ4 ዓመት ከ6 ወር እስራት እንደፈረደበት ቢቢሲ ዘግቧል።

ይግባኝ የመጠየቅ መብቱ የተጠበቀ መሆኑም በዘገባው ተመላክቷል።