Get Mystery Box with random crypto!

የ34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ በአስተናጋጇ ኮትዲቫር አሸናፊነት ተጠናቀቀ AMN-የካቲት 03/2016 ዓ | AMN-Addis Media Network

የ34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ በአስተናጋጇ ኮትዲቫር አሸናፊነት ተጠናቀቀ

AMN-የካቲት 03/2016 ዓ.ም

በ2023ቱ የአፍሪካ ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ አዘጋጇ ኮትዲቯር ናይጄሪያን 2ለ1 በማሸነፍ ዋንጫውን አንስታለች።

ኮቲዲቫር የአፍሪካ ዋንጫን ስታነሳ ለ3ኛ ጊዜ ሲሆን ይህም ከ9 አመታት በኋላ ማለት ነው።

ሁለቱ ቡድኖች ከዚህ ቀደም በነበራቸው የአፍሪካ ዋንጫ ታሪክ ኮትዲቯር 2 ጊዜ እና ናይጄሪያ ደግሞ 3 ጊዜ የዋንጫ ባለቤት መሆን ችለዋል።

በጫዋታው የመጀመሪያ አጋማሽ ምንም እንኳን ናይጄሪያ ጎል በማስቆጠር የመሪነቱን ሚና ብትወስድም የኮትዲቯር ባሳየችው የተሻለ እንቅስቃሴ የጨዋታውን ውጤት መቀየር ችላለች።

ናይጄሪያን ከመሸነፍ ያላዳነችውን ብቸኛዋን ግብ የቡድኑ አምበል ዊሊያም ትሩስት ኢኮንግ በ38ኛው ደቂቃ ከማዕዘን የተሻገረን ኳስ በራሱ በመግጨት ከመረብ አሳርፏል።