Get Mystery Box with random crypto!

የምስራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ኃይልን ለማጠናከር  የሚያስችል የፖሊሲ ማሻሻያ ውይይት በአዲስ አበባ መ | AMN-Addis Media Network

የምስራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ኃይልን ለማጠናከር  የሚያስችል የፖሊሲ ማሻሻያ ውይይት በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ(ኤ ኤም ኤን) የካቲት 2/2015 ዓም

የምስራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ኃይልን ለማጠናከር እና በቀጠናው ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን የሚያግዝ የፖሊሲ ማሻሻያ ውይይት በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።

ውይይቱ ከሁሉም የምስራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ኃይል አባል ሀገራት የተውጣጡ ባለሙያዎችን ያገናኘ ሲሆን በተለያዩ የፖሊሲ ጉዳዮች ላይ በመወያየት ለውሳኔ ሰጪዎች ምክረ ሀሳብ ያቀርባልም ተብሏል።

ለአራት ቀናት የሚቆየውን የውይይት መድረክ የከፈቱት የምስራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ኃይል  ሊቀ መንበር እና የኢፌዴሪ መከላከያ የውጭ ግንኙነት ወታደራዊ ትብብር ዋና ዳይሬክተር ሜ/ጄነራል ተሾመ ገመቹ የፖሊሲ ማሻሻያው የቀጠናውን ሰላም ለመጠበቅ እና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን በተጠናከረ መልኩ ለመመከት የሚያግዝ ነው ብለዋል።

ኢሳፍ 10 ሀገራትን በአባልነት ያቀፈ ቀጠናዊ ተቋም ሲሆን ከተመሰረተም 20 ዓመታትን አስቆጥሯል።

በአሰግድ ኪ/ማርያም