Get Mystery Box with random crypto!

በቱርክ 39 አባላትን ያቀፈው የታዳጊ ልጃገረዶችና ወንዶች የመረብ ኳስ ተጫዋቾች እንዲሁም የመምህራ | AMN-Addis Media Network

በቱርክ 39 አባላትን ያቀፈው የታዳጊ ልጃገረዶችና ወንዶች የመረብ ኳስ ተጫዋቾች እንዲሁም የመምህራኖቻቸው ቡድንን በህይወት የማግኘቱ ስራ መቀጠሉ ተገለጸ

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ (ኤ ኤም ኤን) የካቲት 2/2015 ዓ.ም

በቱርክ 39 አባላትን ያቀፈው የታዳጊ ልጃገረዶችና ወንዶች የመረብ ኳስ ተጫዋቾች እንዲሁም የመምህራኖቻቸው ቡድንን በህይወት የማግኘቱ የነብስ አድን ስራ መቀጠሉ ተገለጸ፡፡

በቱርክና ሶሪያ በተከሰተው አስከፊ ርእደ መሬት አደጋ ምክንያት በየቀኑ አዳዲስ ዜናዎች እየወጡ ይገኛሉ፡፡

በቱርክ በተከሰተው ርእደ መሬት የ 2 መምህራንና አንድ ታዳጊ የመረብ ኳስ ተጫዋች አስከሬን ተገኝቷል፡፡

39 አባላትን ያቀፈው የታዳጊ ልጃገረዶችና ወንዶች የመረብ ኳስ ተጫዋቾች እንዲሁም የመምህራኖቻቸው ቡድን ርእደ መሬቱ በተከሰተበት ወቅት ኢሳያስ በተባለ ትልቅ ሆቴል ውስጥ ከልምምድ መልስ እረፍት በማድግ ላይ ነበሩ ተብሏል፡፡

አዲያማና በተባለው የቱርክ ከተማ ለግጥሚያ ልምምዳቸውን አጠናቀው በሆቴሉ ውስጥ እረፍት እያደረጉ ባሉበት ሰአት ነው የርእደ መሬቱ አደጋ የተከሰተው ተብሏል፡፡

አራት የቡድኑ አባላት አደጋው በተከሰተበት ወቅት ከ7ኛ ፎቅ ራሳቸውን ወደ ምድር በመወርወር በህይወት መትረፍ መቻላቸው ተገልጿል፡፡

ቀሪዎቹ እስካሁን በህይወት ይኑሩ አይኑሩ የታወቀ ነገር የለም የተባለ ሲሆን የማፈላለጉ ስራ በነብስ አድን ሰራተኞቹ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተነግሯል፡፡

የታዳጊዎቹ ቤተሰቦች በህንጻው ፍርስራሽ አካባቢ ተገኝተው የልጆቻቸውን በህይወት መገኘት እየተጠባበቁ ነው መባሉን ቢቢሲ ዘግቧል።