Get Mystery Box with random crypto!

#መረጃ #Update የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወሳኝ ኩነት ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ የተ | AMN-Addis Media Network

#መረጃ
#Update

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወሳኝ ኩነት ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ የተለያዩ የወሳኝ ኩነት አገልግሎቶችን በየዕለቱ እየሰጠ ይገኛል፡፡

ተገልጋዮችም በየዕለቱ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ለጠፋ አዲስ ትክ መታወቂያ የመስጠት፣ ነባር መታወቂያን የማደስ፣ የጋብቻ ውል ሰርተፍክት፣ የፍቺ ሰተፍኬት ...ወዘተ) በኤጀንሲው ቅርንጫፎች ተገኝተው መገልገል እንደሚችሉ የኤጀንሲው የሲስተምና መረጃ ቋት ቡድን መሪ አቶ ሙዘሚን አሰን አሊል ለኤ ኤም ኤን ዲጂታል ገልፀዋል።

በዚሁ መሰረት ያለፉት ሶስት ቀናት (ከጥር 29-የካቲት/2015 ዓ.ም) በከተማ ደረጃ 9366 ለሚሆኑ ተገልጋዮች የመታወቂያ ህትመት አገልግሎት መስጠት የተቻለ ሲሆን በነዚህ ቀናት ኤጀንሲው 920 የሚሆኑ ጥንዶችንም ህጋዊ የጋብቻ ውል ማፈራረም ችሏል። በሌላ በኩል ኤጀንሲው በቀናቱ 1806 ለሚሆኑ የአገልግሎቱ ጠያቂዎች የልደት ማረጋገጫ ሰጥቷል።

ትክክለኛውን የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዲጂታል ሚዲያ የትስስር አውታሮችን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑን!
YouTube ➲ http://bit.ly/3itThRr
Telegram ➲ http://bit.ly/3W4puw9
Facebook ➲ https://bit.ly/3CJVgI8
Twitter ➲ http://bit.ly/3IKQ3TZ

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የካቲት 02/2015 ዓ.ም