Get Mystery Box with random crypto!

#Update በቱርክዬ እና በሶሪያ በተከሰተው የርዕደ መሬት አደጋ ምክንያት የሟቾች ቁጥር ጨምሯ | AMN-Addis Media Network

#Update

በቱርክዬ እና በሶሪያ በተከሰተው የርዕደ መሬት አደጋ ምክንያት የሟቾች ቁጥር ጨምሯል
አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ (ኤ ኤም ኤን) የካቲት 01/2015 ዓ.ም

ሰኞ ዕለት በቱርክዬ እና በሶሪያ በተከሰተው የርዕደ መሬት አደጋ ምክንያት የሟቾች ቁጥር 11,000 መድረሱን አልጄዚራ ዘግቧል።

ከ11 ሺህ ሟቾች መካከል ከቱርክዬ 8,574 የሚሆኑት ሲሆኑ ከሶሪያ ደግሞ 2,530 ሆነው መመዝገባቸውን ዘገባው አመልክቷል።

የነፍስ አድን ስራው አሁንም መቀጠሉ የታወቀ ሲሆን የሟቾች ቁጥር ከዚህም ሊጨምር እንደሚችል የመረጃ ምንጩ ጠቁሟል።