Get Mystery Box with random crypto!

በሰሜናዊ ቱርክ በደረሰው ርዕደ መሬት ከወደሙ የህንጻ ፍርስራሾች ውስጥ አዲስ የተወደለች ህፃን በህ | AMN-Addis Media Network

በሰሜናዊ ቱርክ በደረሰው ርዕደ መሬት ከወደሙ የህንጻ ፍርስራሾች ውስጥ አዲስ የተወደለች ህፃን በህይወት ተገኘች

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ (ኤ ኤም ኤን) የካቲት 01/2015 ዓ.ም

የህፃኗ እናት አደጋው በተከሰተበት ቅጽበት ምጥ ይዟት ስለነበር ከወደለች በኃላ ህይወቷ ሊያልፍ እንደቻለ ተዘግቧል፡፡

በአደጋው አባቷ፣ አራት ወንድሞችና እህቶቿ ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን ህፃኗ ከህንፃ ፍርስራሽ ውስጥ በአደጋ ጊዜ ሰራተኞች መገኘት መቻሏ ታውቋል፡፡

የሕፃኗ አጎት ኻሊል አል-ሱዋዲ ሲናገሩ ህንፃው ሲደረመስ ከአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ጋር ወደ ቦታው ደርሰን ስንቆፍር ድምጽ ሰማንና ህፃኗን አገኘናት ብለዋል፡፡

የህፃናት ዶክተር የሆኑት ዶ/ር ሃኒ ማሩፍ ሲናገሩ “ህፃኗን ወደ ሆስፒታላችን ሲያመጧት መላ ሰውነቷ ተጫጭሮና ከባድ ቅዝቃዜ ውስጥ ገብታ ስለነበር ወደ ሙቀት ክፍል እንድትገባ ካልሺየምም እንድታገኝ አድርገናል›› ሲሉ ተናግረዋል።

በቱርክ በደረሰው ርዕደ መሬት ምክንያት እስካሁን ወደ 5 ሺህ የሚጠጉ ዜጎች መሞታቸውንና በመቶዎች የሚቆጠት ደግሞ በፍርስራሹ ውስጥ እንዳሉ ተዘግቧል፡፡

ቱርክ ርዕደ መሬት ከደረሰባቸው ግዛቶቿ አንዱ በሆነው ኢድሊብ ግዛት በደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ በርካታ ህንፃዎቿ መውደማቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡