Get Mystery Box with random crypto!

ክርስቲያን አቱስ በነብስ አድን ሰራተኞች ከህንጻ ፍርስራሸ ውስጥ በህይወት መገኘቱ ተገለጸ አዲስ | AMN-Addis Media Network

ክርስቲያን አቱስ በነብስ አድን ሰራተኞች ከህንጻ ፍርስራሸ ውስጥ በህይወት መገኘቱ ተገለጸ

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ (ኤ ኤም ኤን) ጥር 30/2015 ዓ.ም

በቱርክ ለሀታይስፖር ክልብ የሚጫወተው ጋናዊው የእግር ኳስ ተጫዋች ክርስቲያን አቱስ ቆስሎ በህይወት መገኘቱ ተገዘግቧል፡፡

በቱርክ በተከሰተው የርእደ-መሬት አደጋ ክርስቲያን አቱስ ደብዛው ጠፍቶ በነብስ አድን ሰራተኞች በየፍርስራሹ ሲፈለግ ቆይቷል፡፡ አደጋው ከተከሰተ በኋላ ተጫዋቹ የደረሰበት እንዳልታወቀ የክለቡ አመራሮች ሲያስታውቁ አስታውቀው ነበም፡፡ ተጫዋቹ አደጋው ከመከሰቱ ከሰአታት በፊት እሁድ እለት ክለቡ በነበረው ጨዋታ የማሸነፊያዋን ጎል ማስቆጠሩ ይታወቃል።

የቀድሞው የኒው ካስትልና ቸልሲ ተጨዋች የነበረው የ31ዓመቱ ክርስቲያን አቱ በህይወት ይገኝ ዘንድ ጋናውያንም ሆኑ በአለም ዙሪያ ያሉ አድናቂዎቹ ፈጣሪያቸውን ሲማጸኑ ቆይተዋል፡፡

አቱ እና የቱርኩ ለሀታይስፖር ክልብ ዋና ዳይሬክተር ታነር ሳቩት በህንጻ ፍርስራሽ ስር ታግተው ሊኖሩ እንደሚችሉ ተገምቶ ፍለጋው ሲካሄድ እንደቆየም ተነግሯል፡፡

ዳይሬክተሩ እስካሁን እንዳልተገኘ ተገልጿል፡፡ የክለቡ መቀመጫ የሆነችው ሃታይ ከተማ በርእደ መሬቱ በእጅጉ ከተጠቁ ከተሞች አንዷ ናት ተብሏል፡፡

ክርስቲያን አቱስ ቆስሎ ከህንጻ ፍርስራሽ ውስጥ በነብስ አድን ሰራተኞች በህይወት መገኘቱን ማናጀሩ ሙስተፋ ኦዛት ለቱርክ ሬዲዮ ገልጸዋል፡፡

የተጨዋቹ በህይወት መገኘት ተጨንቀው ለነበሩ ብዙዎችን እፎይታን እንደሰጠ ይታመናል ሲል የዘገበው ቢቢሲ ነው።