Get Mystery Box with random crypto!

የአክስዮን ጉዳይ ጉዳያችሁ ለሆነ ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ የተሰጠ ወቅታዊ መረጃ፦ የኢትዮጵያ ል | AMN-Addis Media Network

የአክስዮን ጉዳይ ጉዳያችሁ ለሆነ

ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ የተሰጠ ወቅታዊ መረጃ፦

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ስላዘጋጀው አዲስ አማራጭ ካሁን ቀደም ማሳወቃችን ይታወሳል። በዚህ አማራጭ ለመጠቀም እየታየ ካለው ፍላጎት እና በሂደቱ ካስተዋልነው በመነሳት ከአሁን ቀደም የቀረበውን መረጃ በዚህ ምልኩ በድጋሚ ለማስታወስ ወደድን!!

በባንኩ የቀረበው አማራጭ ምንድነው?
→ ባለፉት ሶስት ዙሮች ሰልጥነው የምስክር ወረቀት/ሰርተፊኬት የተቀበሉ እና ፍላጎቱ ያላቸውን ሰልጣኞች የባንኩን ፖሊሲና መመሪያ በጠበቀ መልኩ በአክሲዮን ማህበር አደራጅቶ ወደ ቢዝነስ እንዲገቡ ማድረግ፡፡

የአማራጩ አስፈላጊነት ምን ላይ ነው (ከብዙ በጥቂቱ)?
→ ለሥራ ማስኬጃ የሚሆነውን 20% መዋጮ ለማዋጣት አቅሙ ለሌላችሁ ነገር ግን የባንኩን ሊዝ ፋይናንሲንግ አገልግሎት ለምትሹ በጋራ ሆናችሁ ይህንን አቅም የምትፍጥሩበትን ዕድል ማመቻቸት
→ ለበርካቶች የሥራ ዕድል መፍጠር እና
→ ልማትን በማፋጠን የልማት አጋርነቱን ማስቀጠል

በአክስዮን ለመደራጀት ምን ያስፈልግዎታል?
→ በአክስዮን ማህበር ለመደራጀት ሼር መግዛት ያስፈልግዎታል።

ለመደራጀት የሚያስፈልግዎ ትንሹ ወጪ (ገንዘብ) ወይም ድርሻ (ሼር) ስንት ነው?
→ እያንዳንዱ ሼር 1000 ብር ዋጋ ያለው ሆኖ ዝቅተኛው የሚሸጥ የሼር መጠን አምስት ወይም 5000 ብር ነው ስለሆነም ትንሹ በአክስዮን ለመደራጀት የሚያስፈልግዎት የብር መጠን 5,000 ነው።

ለአክስዮን ስለመመዝገብ
→ ሰልጣኞች በአክሲዮን ለመሥራት ራሳቸውንና ሌሎች አብረዋቸው ሊሠሩ የተዘጋጁ የአክሲዮን አባላቶቻቸውን በማስመዝገብ የዚህ ዕድል ተጠቃሚ መሆን ይችላሉ

ሰለማህበሩ እና ስለአባላቱ
→ የምታስመዘግቧቸው ሌሎች አባላቶች ሥልጠናውን ያልወሰዱ ከሆኑ በቀጣይ በሚኖሩ የሥልጠና ዙሮች መሠልጠን ይኖርባቸዋል፡፡
→በአክሲዮን ማኅበር ለመሥራት የምትመዘገቡ የአክሲዮን ባለቤቶች አብራችሁ ለመሥራት ተስማምታችሁ የቆያችሁ፣ ሕጋዊ ለመሆን በሂደት ላይ ያላችሁና በጋራ የምትጠሩበት ስም ካላችሁ ማስመዝገብ ትችላላችሁ፡፡
→በአዲስ መልክ የሚቋቋሙ ከሆነ ግን በምትመዘገቡበት ቀን የባንኩ ቅርንጫፍ ለጊዜው በሚሰጣችሁ መለያ ስም ወይም ቁጥር ትመዘገባላችሁ፡

ስለማህበሩ መሪ
→ በሚፈጠረው የአክሲዮን ማኅበር ውስጥ አስተባባሪ የሚሆኑት ሥልጠናውን ወስደው የምስክር ወረቀት ያገኙ አባላቱ ናቸው፡፡

ሌሎች ጉዳዮች
→ ተመዝጋቢዎች  ኢንቨስት የምታደርጉበትን ዘርፍ ተዘጋጅታችሁበት ለምዝገባ መቅረብ ይኖርባችኋል፣ ሼር መግዛት የምትችሉት በመረጣችሁት ዘርፍ ስለሆነ፡፡
→ እንዲሁም ምን ያህል ሼር እንደምትገዙ ቀድማችሁ እንድትዘጋጁበት ይሁን፡፡