Get Mystery Box with random crypto!

በኮልፌ ቀራንዮ በአንድ የመጋዘን ህንፃ ላይ የእሳት አደጋ መከሰቱ ተገለጸ ሐሙስ ነሐሴ 26 ቀን | Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

በኮልፌ ቀራንዮ በአንድ የመጋዘን ህንፃ ላይ የእሳት አደጋ መከሰቱ ተገለጸ

ሐሙስ ነሐሴ 26 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ በወረዳ 07 ልዩ ቦታው ቤተል ትምህርት ቤት ጀርባ በተባለ አካባቢ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ በአንድ የመጋዘን ህንፃ የእሳት አደጋ መከሰቱ ተገልጿል።

የእሳት አደጋው ዛሬ ከረፋዱ 4:40 ላይ በውስጡ የፒፒሲ፣ የአረቢያን መጅሪስ እና የስፖንጅ መጋዘን ላይ መነሳቱን ኮልፌ ቀራንዮ ወረዳ 07 ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት አስታውቀዋል።

የእሳት አደጋ መቆጣጠሪያ ሰራተኞች፣ የፀጥታ ሀይሎች እንዲሁም ነዋሪዎች እርብርብ በማድረግ እሳቱ በመቆጣጠርና በማጥፋት ላይ እንደሚገኙም ተገልጿል፡፡
_
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n