Get Mystery Box with random crypto!

Addis Eyita

የቴሌግራም ቻናል አርማ addiseyita — Addis Eyita A
የቴሌግራም ቻናል አርማ addiseyita — Addis Eyita
የሰርጥ አድራሻ: @addiseyita
ምድቦች: ንግድ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 10.00K
የሰርጥ መግለጫ

የቢዝነስ ምስረታና ማስፋፊያ፣ የፋይናንስ አጠቃቀም ስልት፣ ሳይንሳዊ የቢዝነስ እቅድ ዝግጅትና የንግድ ስነልቡና ጨምሮ የተለያዩ ከቢዝነስ ጋር የተያያዙ ስልጠናዎችን እንሰጣለን።
አድራሻ:-ሜክሲኮ ኬኬር ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ.227
📞 0901842121 / 0978212121

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-06-29 09:47:07
አዲስ እይታ በንግድ እና ኢንቨስትመንት የማማከር ሥራ አገልግሎት ከሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር "አዲስ እይታ ለስኬታማ ቢዝነስ!" በሚል ርዕስ በአይነቱ ልዩ የሆነ ስልጠና አዘጋጅቷል።
የስልጠና ርዕሶች
1.የሰው ባህሪ እና የቢዝነስ ስነ-ልቦና
2.በቢዝነስ ውስጥ ስኬትን ማስቀጠል እንዴት ይቻላል
2. ቢዝነስ ለመስራት እራስን መስራት
3. የቢዝነስ አመራርና አስተዳደር 4.የማኑፋክቸሪንግ ቢዝነስ ባህሪያት
5. እራስ ላይ መስራት ለስኬታማ ቢዝነስ
ስልጠና የሚሰጡ አሰልጣኞች
-ዶ/ር ወሮታው በዛብህ
-ዶ/ር እዮብ ማሞ
-ዶ/ር ኤሊያስ በላይ
-ሳሙኤል ተ/እየሱስ
-ክብረት አካሳ
-ተመስገን ዐብይ
የስልጠናው ተሳታፊዎች
-ቢዝነስ የጀመሩ ማህበራት አባላት እና ስራ ፈጣሪ ግለሰቦች፣
-በቢዝነስ ውስጥ የሚገኝ ማንኛውም የቢዝነስ ተቋም
በዕለቱ በአዲስ እይታ አማካኝነት ቢዝነስ ጀምረው በስራ ላይ የሚገኙ የስራ ፈጣሪዎች የዕውቅና ሽልማት ይበረከትላቸዋል።
የስልጠና ቦታ:-ዓለም ሲኒማ
የስልጠና ቀንና ሰዓት:-ሰኔ 25/2014 ዓ.ምቅዳሜ ከጠዋቱ 4፡00 ጀምሮ
መግቢያ
የአዲስ እይታ መፅሐፍ
በ0978212121 ላይ ደውለው ይመዝገቡ።
3.2K views06:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-23 16:53:51
የፋይበር ግላስ ውጤቶችን የማምረት ቢዝነስ
፦ ከፍተኛ የገበያ ፍላጎት ያለበት ዘርፍ
፦ በተለያየ ዲዛይን እና ቀለም ማምረት የሚችልበት
፦ ለአበባ መትከያ እና ማስቀመጫነት፣ ሮቶ፣ ቁም ሳጥን ፣ቆርቆሮ እና ሌሎችም
፦ የሚያስፈልገው ቦታ 50ካሬ
፦ መነሻ ካፒታሉ 100,000ሺ ብር ሲሆን ይሄን ስራ ለመጀመር ወደ አዲስ እይታ ቢሮ መምጣት ብቻ በቂ ነዉ
፨ አድራሻ፦ ሜክሲኮ ኬኬር ህንጻ 2ተኛ ፎቅ
፨ ስልክ፦0978212121
4.2K views13:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-13 18:17:39 #መርህ አንድ:- ፍላጎት (Desire)

የመጀመሪያው የስኬት መርህ ፍላጎት ነው። ከልብ የመነጨ ፍላጎት። ፍላጎታችንን እንደ ዘር ልናየው እንችላለን። ፍሬ እንደሚያፈራ አምነን የምንዘራው ዘር። ነገር ግን ዛሬ ዘርተነው ዛሬውኑ ፍሬ የሚሰጠን ተክል የለም።

ፍላጎታችንም ልክ እንደ በቆሎ ወይም ማንኛውም ዘር ዛሬ ተዘርቶ በቂ ውሃ፤ በቂ ጸሃይ፤ በቂ እንክብካቤ ፤ካገኘ በኋላ በግዜው የሚያሽት ነው።

የምንፈልገውን ነገር ጥርት ባለ መልኩ ማወቁ ይጠቅመናል። ለመረጥነው ነገር ምን ያህል ፍላጎት እንዳለን ለማወቅ የምናደርጋቸውን ነገሮች መቃኘት ያስፈልገናል። ከምንም በላይ በውስጣችን ያለው የትዕግስት መጠን ፍላጎታችን ምን ያህል እንደሆነ ያስረዳናል።

ለምሳሌ ሰዓሊነት ፍላጎቱ የሆነ ሰው ባይከፈለው እንኳን ስዕል መሳሉን አያቆምም። አላማ ብለን ለመረጥነው ነገር በቀላሉ ሊገደብ የማይችል ፍላጎት ሊኖረን ይገባል። ጥልቅ ፍላጎት ማለት ወደኋላ እንዳናፈገፍግ የመመለሻውን ድልድይ እንደማቃጠል ያህል ነው።

#መርህ ሁለት:- እምነት (Faith)

እምነት አላማችን የሚገነባበት መሰረት ነው። የምንፈልገው ነገር ምንም ይሁን ምን እምነት ከሌለን ነዳጅ የሌለው መኪናን ለመንዳት እንደመሞከር ይሆንብናል። ደግነቱ እምነት በመጀመሪያ ባይኖረንም፤ በሂደት ልንገነባው የምንችለው ጥበብ ነው።

ለአእምሮአችን ቀና የሆኑ ነገሮችን በመመገብ እምነትን በሂደት ማዳበር ይቻላል። የምንፈልገውን ነገር ለማግኘት እምነት እጅግ ወሳኝ ነገር መሆኑን መዘንጋት የለብንም። ማርቲን ሉተር ኪንግ ስለ እምነት ደስ የሚል አባባል አለው ” እምነት ማለት ሙሉውን ደረጃ እስከየት እንደሚያደርሰን ባናውቅም እንኳ የመጀመሪያውን ደረጃ መውጣት ነው” ይላል።

#መርህ 3:- እራስን ማሳመን (Auto Suggestion-አውቶ ሰጀሽን)

አእምሮአችን እውነት ብሎ የሚቀበለው ነገር ደጋግመን የምንመግበውን ነው። እዚህ ላይ ይህንን በደንብ የሚያስረዳ አንድ ታሪክ ትዝ አለኝ። ታሪኩ እንዲህ ነው

ሁለት ውሾች የነበሩት አንድ ሰው ነበር። አዘውትሮ እኒህን ውሾች አደባባይ እየወሰደ እንዲደባደቡ ያደርግ ነበር። ታዲያ ተመልካቾቹ የትኛው ውሻ በእለቱ እንደሚያሸንፍ ሲጠይቁት “በደንብ የምመግበው ውሻ ነው” ሲል መለሰላቸው። ሁላችንም ውስጥ ሁለት ዉሾች አሉ የመልካም እና የክፋት፤ የልማት እና የጥፋት፤ የእውቀት እና የድንቁርና፤ የውድቀት እና የድል ውሾች። የበላይ ሆኖ የሚመራን ውሻ ዘወትር የምንመግበው ነው።

ለዚህ ነው ናፖሊዮን ሂል “አውቶ ሰጀሽን” ወይም ለራስ መልካም ነገሮችን ደጋግሞ በመንገር አእምሮአችንን ወደፈለግነው መንገድ መምራት እንደምንችል የሚነግረን። መንገር ብቻም ሳይሆን የሚያሳስበን!

#መርህ አራት:- በአንድ ነገር ላይ እራስን የተካኑ ማድረግ (ስፔሻላይዝድ ኖውሌጅ)-

ልንሰማራበት በመረጥነው ወይም ፍላጎት ባለን ሙያ ላይ የተሰማሩ ሰዎችን መተዋወቁ እና ቅርርብ መፍጠሩ ወሳኝ ነገር ነው። ጊዜያችንን የምናሳልፈው ከነማን ጋር ነው? የምናውቃቸው ሰዎች ወይም ጓደኞቻችን ለምንፈልገው ሙያ የሚያግዙን ናቸው?

ለምሳሌ:- ፕሮፌሰር ለመሆን ፍላጎት ያለው ሰው በተቻለው መጠን ዩንቨርሲቲ አካባቢ ካሉ ሰዎች ጋር ግንኙነቱን ቢያዳብር ይጠቅመዋል። ተዋናይ መሆን የሚመኝ ሰው እራሱን ከቲያትር መድረክ አካባቢ ማራቅ የለበትም። ሁላችንም የምንማረው ቀድመውን ካወቁት ነውና፤ የምንፈልገውን ነገር በቅጡ የሚያውቁ ሰዎችን ማወቁ ይጠቅመናል።

#መርህ አምስት:- ነገሮችን በህሊናችን መሳል- (Imagination)
ሁሉም ነገር ሃሳብ ነበር። ምንም ነገር እውን ሆኖ ከማየታችን በፊት በአንድ ሰው አይምሮ ውስጥ የተጠነሰሰ ሃሳብ ነበር። የምንፈልገውን ነገር እውን ሆኖ ከማየታችን በፊት በህሊናችን መሳል ትልቁ የስኬት ሚስጥር እንደሆነ ብዙዎች የተስማሙበት ነው። አላማችን ቁልጭ ብሉ በህሊናችን ከታየን ለጉዟችን ትልቅ ጉልበት አገኘን ማለት ነው። ምክንያቱም የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ እንደሚሳካ አእምሮአችን እየነገረን ነው።

#መርህ ስድስት:- እቅድ ማውጣት- (Organized planning)

እቅድ ማውጣት ጊዜን በአግባቡ እንድንጠቀም ከማድረጉም በላይ፤ በአንድ ጊዜ አንድ ደረጃ እየወጣን ጉዟችን አድካሚ እንዳይሆን ያደርግልናል። እቅድ ስናውጣ ነገሮች ሳይደራረቡብን ቀስ በቀስ ወደ ግባችን እንደርሳለን።

እቅድ ስናወጣ ግን እራሳችንን በሚያጨናንቅ እና ካልፈጸምነው የጥፋተኝነት ስሜት እንዲሰማን በሚያደርግ ሁኔታ ሳይሆን፤ ከጊዜያችን ፤ ከባህሪያችን እንዲሁም ከማንነታችን ጋር የሚስማማ እቅድ ነው ማውጣት አለብን። ምክንያቱም ሌላው ያቀደበት መንገድ ለኛ ላይስማማ እና ከግባችን ላያደርሰን ስለሚችል ነው።

#መርህ ሰባት:- ውሳኔ (Decision)

የሰው ልጅ ውድቀት አንደኛው መንስዔ የውሳኔ ማጣት ነው። አንድ ሰው ምንም ያህል እምቅ እውቀት ቢኖረው፤ ምንም ያህል የሚያስደንቅ ሃሳቦችን ማመንጨት ቢችልም ውሳኔ መወሰን ካልቻለ ግን አቅሙ ሁሉ ከውስጡ አይወጣም።

ውሳኔ በማጣት የተነሳ ብዙ ሙዚቃዎች ሳይሰሙ፤ ብዙ መጽሐፎች ሳይጻፉ፤ ብዙ ግኝቶች ሳይገኙ፤ ወደ መቃብር ይወርዳሉ።.በሁላችንም ውስጥ ለኛ ብቻ የተሰጠ ስጦታ አለ፤ ይህን ስጦታ ግን አውጠን ሌሎች እንዲያዩት ማድረግ የምንችለው ውሳኔ መወሰን ስንችል ብቻ ነው። የምንወስነው ምንድን ነው ካላችሁ፤ መልሱ የምንወስነው መሆን የምንፈልገውን ነው።

#መርህ ስምንት:- ጽናት (Persistence)

ውሳኔ ብቻውን አቅም የለውም። ውሳኔያችን ባህሩን አቋርጦ ከአላማችን ዳርቻ እንዲደርስ የሚያደርገው ሃይል ጽናት ነው። ብዙዎቻችን የተለያዩ ውሳኔዎችን እዚህና እዚህ እንወስናለን ነገር ግን ጽናት ኖሮን አንገፋበትም።

ለዚህ ነው ናፖሊዮን ሂል የውድቀት እና የስኬት ዋናው መለያ ጽናት ነው ያለው። ለምሳሌ ከመጠጥ ሱስ መላቀቅ የሚፈልግ ሰው መቶ ጊዜ ለማቆም ቢወስንም ከውሳኔው ጋር ጽናት ካልተደመረበት በቀር ውሳኔው ብቻውን ምንም ዋጋ የለውም። ስለዚህ በውስጣችን ያለውን የጽናት መጠን መፈተሹ እጅግ ወሳኝ ነገር ነው።

#መርህ ዘጠኝ:- ጥምር ሃይል (Power of the master mind)

“ሁለት ጭንቅላቶች አንድ ላይ ሲሆኑ ሶስተኛ ጭንቅላት ይወለዳል”። አንድ ሰው የራሱ የሆነ ሃሳብ ወይም ግኝት ሊኖረው ይችላል፤ ከሌሎች ሰዎች ሃሳብ ጋር ሲደመር ደግሞ ይበልጥ ይሰምራል።

በጋራ የመስራትን ልምድ ማዳበር መቻል አለብን። አብሮ መስራት መቻል ትልቅ ክህሎትም ጭምር ነው።

#መርህ አስር:- የምታደርገው ነገር ደስታን ሊስጠህ ይገባል– (Enthusiasm)

ስቲቭ ጆብስ በህይወት በነበረበት ወቅት እንዲህ ብሎ ነበር “የምንሰራውን ነገር የማንወደው ከሆነ እስከመጨረሻው ለመሄድ አንችልም፤ የሚሰራውን የማይወድ ማንኛውም ሰው ተስፋ ቢቆርጥ አይፈረድበትም”።

እውነት ነው የምንወደውን ነገር ስናደርግ በቀላሉ ተስፋ አንቆርጥም። ሙያችን እንዲሆን የምንመርጠው ነገር የምንወደው ነገር ከሆነ በዛ ነገር ላይ እውቀታችንን ለማዳበርም ሆነ ልምድ ለማግኘት ፍላጎት ይኖረናል።
5.6K views15:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-08 12:28:35
የጋርመት ዉጤቶችን የማምረት ቢዝነስ
፦ በቀላሉ ሊሰሩ እና ሊመረቱ የሚችሉ የቲሸርት፣ ሸሚዝ ፣ ቦክሰር ፣ቱታ ፣ ጂንስ እና ሌሎችም የጋርመንት ምርቶች በተለያየ ሳይዝ እና መልክ ለሁሉም ማህበረሰብ ማምረት ይችላሉ ፡፡
፦ በቀን እንደ አይነቱ ከ600-900 ፒስ ማምረት ይቻላል ፡፡
፦ የሚያስፈልገው ቦታ 100ካሬ ፦ መብራት፦3ፌዝ
፦ መነሻ ካፒታሉ 2.6 ሚሊየን ሲሆን ፤የዚህ 20 ፐርሰንት 520ሺ ያለው ሰው ይሄን ስራ ለመጀመር ወደ አዲስ እይታ ቢሮ መምጣት ብቻ በቂ ነዉ።
፨ አድራሻ፦ ሜክሲኮ ኬኬር ህንጻ 2ተኛ ፎቅ
፨ ስልክ፦0978212121
5.4K views09:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-02 18:50:16

6.0K views15:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-27 18:41:14
7.3K views15:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-24 21:08:56
የሴቶች የንጽህና መጠበቂያ( sanitary pad)የማምረት ቢዝነን
፦ የሴቶች የንጽህና መጠበቂያ በሀገራችን በበቂ ሁኔታ ያልተዳረሰ እና ከፍተኛ የገበያ ፍላጎት ያለበት ዘርፍ ነው።
፦ የተለያየ ልኬት ያላቸውን የንጽህና መጠበቂያ ፖዶችን ማምረት ይቻላል ።
፦ በቀን 4800 ፒስ ማምረት ይችላል።
፦ የሚያስፈልገው ቦታ 100ካሬ ፦ መብራት፦7KW
፦ መነሻ ካፒታሉ 2.3ሚሊየን ብር ሲሆን የዚህ 20% ያለው ሰው ይሄን ስራ ለመጀመር ወደ አዲስ እይታ ቢሮ መምጣት ብቻ በቂ ነዉ
፨ አድራሻ፦ ሜክሲኮ ኬኬር ህንጻ 2ተኛ ፎቅ
፨ ስልክ፦0978212121
7.3K views18:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-13 18:32:26

7.7K views15:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-11 10:35:21
የምግብ ዘይት የማምረት ቢዝነስ
፦ ዘይት በገቢያ ላይ በጣም ተፈላጊ እና ለት ተእለት የምንጠቀመው ነው።
፦ በቀን 6000ሊትር ዘይት ጨምቆ ማሽግ ይቻላል ይችላል
፦ የሚያስፈልገው ቦታ 200ካሬ ፦ መብራት፦40KW
፦ መነሻ ካፒታሉ 3.9ሚሊየን ብር ሲሆን የዚህ 20% ያለው ሰው ይሄን ስራ ለመጀመር ወደ አዲስ እይታ ቢሮ መምጣት ብቻ በቂ ነዉ
፨ አድራሻ፦ ሜክሲኮ ኬኬር ህንጻ 2ተኛ ፎቅ
፨ ስልክ፦0978212121
7.2K views07:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-05 16:35:54 ሃሳብን ወደ ተግባር መለወጥ!

አንድን ያመንንበት ሃሳብ ወደ ተግባር ለመለወጥና ስኬታማ ለመሆን ከፈለግን የሚከተሉት ሶስት መሰረታዊ ልምምዶች ያስፈልጉናል፡፡

1. እውቀት

ለመተግባር በፈለግነው ማንኛውም ጽንሰ-ሃሳብ አንጻር በቂ እውቀት ማዳበር በምንም ነገር ሊተካ የማይችል ልምምድ ነው፡፡ ካለእውቀት የሚጀመር ነገር ረጅም ርቀት ለመሄድ ካለመቻሉም ባሻገር አንድ እርምጃ ለመራመድ እንኳን እውቀቱን በጨበጡ ሰዎች ላይ የምንደገፍ ያደርገናል፡፡

2. እምነት

በአንድ ማከናወን በፈለግነው ነገር ላይ በቂ ወይም ለመነሻ የሚሆን እውቀት ካዳበርን በኋላ ወደፊት ለመገስገስ ከፈለግን የምንጀምረው ነገር እንደሚሰራ በሙሉ ልባችን ልናምን ይገባናል፡፡ እንደሚሳካም ሆነ ወደፊት እንደምንገሰግስ ልባችን ያላመነበትን ነገር መጀመር አስቸጋሪ ከመሆኑም በላይ፣ ቢጀመርም እንኳን ዘላቂነቱ አጠራጣሪ ነው፡፡

3. እርምጃ

ማድረግ የፈለግነውን ነገር አወቅነውም አላወቅነውም፣ እንደሚሰራ አመንንበትም አላመንበት፣ የመጨረሻው የውጤታማነት ምስጢር ያለው በዚያ ነገር ላይ እርምጃ በመውሰዳችን ላይ ነው፡፡ እርምጃና ተግባራዊነት የሌለው እውቀትም ሆነ እምነት የትም አይደርስም፡፡

በቂ እውቀት! ጽኑ እምነት! የማያዳግም እርምጃ!

(ዶ/ር ኢዮብ ማሞ)
7.9K views13:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ